Connect with us

በቻይና የተመረተው የመከላከያ የደንብ ልብስ ወደ አገር ውስጥ መግባት ሊጀምር ነው

በቻይና የተመረተው የመከላከያ የደንብ ልብስ ወደ አገር ውስጥ መግባት ሊጀምር ነው
Photo: Facebook

ዜና

በቻይና የተመረተው የመከላከያ የደንብ ልብስ ወደ አገር ውስጥ መግባት ሊጀምር ነው

በቻይና የተመረተው የመከላከያ የደንብ ልብስ ወደ አገር ውስጥ መግባት ሊጀምር ነው

• ከዚህ ቀደም አለመዳ ጨርቃጨርቅ የደንብ ልብሱን ያቀርብ ነበር

የአገር መከላከያ ሠራዊት አዲስ የደንብ ልብስ በአንድ ወር ውስጥ የመጀመሪያው ጭነት ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ እና ከሦስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚረከብ አስታወቀ።

አምስት ወራት በፈጀ ሒደት ዓለማቀፍ ጨረታ በማውጣት እና ከ 15 የማያንሱ ድርጅቶችን በማወዳደር የተዘጋጀው የደንብ ልብስ፣ የምድር እና የአየር ኃይልን የውጊያ እና የክብረ በዓላት ልብሶችን ከነመጫሚያው ያሟላ ነው። ይህ ግዢ የባህር ኃይልን የማያካትት ሲሆን በመዋቀር ላይ የሚገኘው የባህር ኃይል በቀጣይ እንደሚዘጋጅለት ለማወቅ ተችሏል።

ጨረታውን ያሸነፈው የቻይና ድርጅትም ከመከላከያ ጋር ውል በማሰር ልብሶቹን ማዘጋጀት የጀመረ ሲሆን፣ የመከላከያ ሚኒስቴርም የምርት ሒደቱን በቅርብ እየተከታተለ እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል። የደንብ ልብሶቹን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የዋለው ጨርቅ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥራት ከፍ ያለ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ የተናገሩት የሠራዊቱ የኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ፣ ልብሶቹ ተሠርተው በሚጠናቀቁበት ጊዜም ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ምርቶች ላይ ናሙና ተወስዶ የጥራት ፍተሻ እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

ሜጀር ጄነራል መሐመድ ጨምረው፣ ኤታማጆር ሹሙ እና ምክትል ኤታማጆር ሹሙ በተደጋጋሚ ለብሰውት የሚታዩት የውጊያ ልብስ አዲሱ ዲዛይን መሆኑን አረጋግጠዋል። እንደ ኀላፊው ገለጻም ልብሱ በተደጋጋሚ ተለብሶ እና ተሞክሮ ጥራቱ ሊረጋገጥ ችሏል።

በምርት ሒደት ከኹለት ጊዜ በላይ ባለሞያዎች እየተላኩ ናሙና በመውሰድ እና በዓለማቀፍ ላቦራቶሪ በማስገምገም ጥራቱን መከታተላቸውንም አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ሰምታለች። የአንድ የደንብ ልብስ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም፣ አሁን የሚገባው የደንብ ልብስ ከቀደመው የ 20 በመቶ ጭማሪ እንዳለው አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።

በተመሳሳይም ከዚህ ቀደም ሠራዊቱ የደንብ ልብሱን ገዝቶ የሚጠቀም የነበረ ሲሆን፣ ይህንን የደንብ ልብስ ግን መንግሥት ሙሉ ወጪውን በመሸፈን በዓመት ከአንድ ቅያሪ ጋር እንደሚሰጥ አዲስ ማለዳ ከታማኝ ምንጮቿ ተረድታለች።

ከአየር ጸባይ እና ከመልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ጥናት እንዲሁም የመስክ ሙከራ የተደረገበት ይህ ልብስ፣ የዲዛይን ፓተርኑ እስከዛሬ ከነበረው ዘመኑ ወዳፈራው ተለውጧል።

ሜጀር ጄነራል መሐመድ እንዳሉት፣ የሠራዊቱ የደንብ ልብስ ከሚቀየርባቸው ምክንያቶች መካከል ልብሱ ለሕገወጥ ተግባር ሲባል በተለያዩ ሰዎች እጅ በመግባቱ ነው። አክለውም የደንብ ልብሱ የሚቀየርበት መመሪያ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ አወጋገዱ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ አገር ውስጥ ይመረት የነበረ ሲሆን፣ ከአንድ ዓመት በፊት በውጪ ተዘጋጅቶ መጥቷል። በዓመት ከሚሰጠው ኹለት የደንብ ልብስም አንዱን አባላቱ እንዲገዙ የሚደረግ ሲሆን፣ ጡረታ በሚወጡ ጊዜም በገንዘባቸው የሚገዙትን ልብስ ለማስመለስ አስቸጋሪ እንደነበርም ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተናግረዋል። አዲስ ማለዳ ባደረገችው ማጣራትም በትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ኤፈርት) ባለቤትነት የሚተዳደረው እና ከአድዋ ከተማ ሰባት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሰራዊቱን የደንብ ልብስ ያቀርብ ነበር። ፋብሪካው በድህረ ገጹ ላይ የወታደር ልብሶችን እንዲያመርትም ይገልፃል።

ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ሒደት የኢትዮጵያም ሆነ የዓለማቀፍ የጉምሩክ ሥነ ስርአቶች እንዲሁም የመርከብ ጭነት ሒደቶች ካላዘገዩት፣ በተባለው ጊዜ ቅያሬው እንደሚገባደድ ኀላፊው ተናግረዋል።

ከደንብ ልብስ ባሻገርም የሠራዊቱን የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ለማሻሻል የሕግ ሥራዎች ተጠናቀዋል ሲሉ ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተናግረዋል።(ምንጭ፡- አዲስ ማለዳ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top