Connect with us

ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርቱን ሊያቋርጥ ነው

ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርቱን ሊያቋርጥ ነው
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርቱን ሊያቋርጥ ነው

ቦይንግ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርቱን ከጥር ጀምሮ በጊዜያዊነት ሊያቋርጥ መሆኑን ገልጿል።

ከሁለት አሥርተ ዓመታት በላይ በላይ የቆየው ቦይንግ ከሁለት ከባድ የአውሮፕላኖን አደጋዎች በኋላ አውሮፕላኖቹ ከበረራ ታግደው ነበር፡፡

12 ሺህ ሰራተኞች ያሉት ኩባንያው ከ737 ማክስ ጋር በተያያዘ ሰራተኞቹን እንደማይቀንስ አስታውቃል፡፡

ሆኖም የኩባንያው ምርት ማቆሙ የእቃ አቅራቢ ድርጅቶችን እና አጠቃላይ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል።

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተመልሶ በዚህ ዓመት መጨረሻ ይበራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ፤ የአሜሪካ አቪየሽን ተቆጣጣሪ ግን አውሮፕላኑ እንዲህ በፍጥነት ተመልሶ አየር ላይ እንዲወጣ ፈቃድ እንደማይሰጠው አስታውቋል።

ቦይንግ”737 ማክስ ደህንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ ወደ በረራ እንዲመለስ ማድረግ ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ተርታ ነው” ብሏል።

737 ማክስ አውሮፕላን ከበረራ በመታገዱ ብቻ 9 ቢሊየን ዶላር ያስወጣው ሲሆን የአክሲዮን ድርሻው በ4 በመቶ ቀንሶ ታይቷል።

በኢንዶኔዥያ እና ኢትዮጵያ በተከሰቱት ሁለት አደጋዎች የ346 ሰዎችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፤ ሮይተርስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top