Connect with us

የጥርስ ንፅህናን መጠበቅ ለልባችን ጤንነት ይጠቅማል- ጥናት

የጥርስ ንፅህናን መጠበቅ ለልባችን ጤንነት ይጠቅማል- ጥናት
Photo: Facebook

ዜና

የጥርስ ንፅህናን መጠበቅ ለልባችን ጤንነት ይጠቅማል- ጥናት

ከሰሞኑ የወጣ አንድ አዲስ ጥናት የጥርስ ንጽህናን መጠበቅ በተለይም በቀን እስከ 3 ጊዜ ድረስ ማጽዳት (መቦረሽ) ለልባችን ጤንነት ጠቀሜታ እንዳለው አመላክቷል።

እንደ ተመራማሪዎች ገለጻ፥ በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች በጤናችን ላይ በርካታ እክሎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶችም በአፍ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች የጣፊያ ካንሰርን ጨምሮ ለሌሎች የካንሰር አይነቶች ይዳርጉናል ያሉ ሲሆን፥ ሌሎች ጥናቶች ደግሞ የአፍ ንፅህናን አለመጠበቅ ለመተንፈሻ አካል የጤና እክል ይዳርጋል የሚሉ ውጤቶችን ማቅረባቸው አይዘነጋም።

ከዚህ ቀደም የተሰሩትን ጥናቶች ጨምሮ አሁን ላይ አዲስ የተሰራው ጥናትም በአፍ ጤንነት እና በልብ ጤንነት መካከል ያለውን ግንኙነት ያመላክታሉ።

እንደ ጥናቱ ውጤት በአፍ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች በልባችን ላይ ድንገተኛ የልብ ምት መቆም እና ልባችን በተገቢው መልኩ ለሰውነታችን ደም ያለመርጨት የጤና እክል ሊያጋልጡት ይችላሉ።

ስለሆነም የአፍ ውስጥ ጤንነትን በአግባቡ መጠበቅ ለልባችን ጤንነት ወሳኝ መሆኑን ነው ተመራማሪዎቹ የሚናገሩት።

ለዚህ ደግሞ በየእለቱ በተደጋጋሚ ጥርሳችንን ማጽዳት (መቦረሽ) በልባችን ላይ ሊደርስ የሚችል የጤና እክልን የመቀነስ አቅሙ ትልቅ ነው ብለዋል።

በጥናቱ እንደተለየውም በቀን እስከ 3 ጊዜ ድረስ የአፋቸውን ውስጥ ንጽህና የሚጠብቁ እና ጥርሳቸውን የሚቦርሹ ሰዎች ለልብ የጤና እክል የመጋለጥ እድላቸው ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር በ12 በመቶ ቀንሶ ታይቷል።

ምንጭ፦ www.medicalnewstoday.com

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top