Connect with us

ዶ/ር ዐብይ በመጪው ማክሰኞ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ይቀበላሉ

ዶ/ር ዐብይ በመጪው ማክሰኞ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ይቀበላሉ
PHOTO: Nobel Peace Center

ዜና

ዶ/ር ዐብይ በመጪው ማክሰኞ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ይቀበላሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማትን በመጪው ማክሰኞ ኖርዌይ ኦስሎ በመገኘት ይቀበላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው መስከረም 30 በኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው።

ይህንንም ተከትሎ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል ኮሚቴ የሠላም ሽልማቱ ይበረከታል ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በኖርዌይ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልቤርግ እና ከንጉስ ሃራልድ 5ኛ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን የሀገሪቱን ፓርላማም ይጎበኛሉ ተብሏል።

በሽልማቱ ዕለትም በኦስሎ ከተማ የስብሰባ አዳራሽ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።

ዶክተር ዐብይ ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ትብብር ላደረጉት ጥረት በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለዓመታት የዘለቀው የድንበር የይገባኛል ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ተነሳሽነትን በመውሰዳቸው የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ እንዳደረጋቸው ኮሚቴው መግለፁ የሚታወስ ነው።

በተጨማሪም ሁሉም ባለድርሻ አካለት በኢትዮጵያ፣ በምስራቅና በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ ላደረጉት አስተዋፀኦ እውቅና ለመስጠትም እንደተመረጡ ኮሚቴው ገልጿል።

ኮሚቴው በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማምጣት ቃል መግባታቸውን በማስታወስ፥ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመቀበል ሀገራቱ አስመራ ላይ የሠላም ስምምነት እንዲፈራረሙ ማስቻላቸውን ነው ያነሳው።

ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሰላም ስምምነት በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሻክሮ የነበረው የጅቡቲና ኤርትራ ግንኙነት እንዲስተካል ሚና እንደነበራቸው አስታውሷል።

የኖቤል ኮሚቴው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለረጅም አመታት የነበረው ውጥረት እንዲፈታ ተነሳሽነት ሲወስዱ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ሀሳቡን በበጎ መልኩ ተቀብለዋል ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሃላፊነት ከመጡ በኋላ በርካታ ለውጦችን በመካሄድ የሀገሪቱ ዜጎች ለተሻለ ህይወት ተስፋ እንዲያደርጉ አድርገዋል ብሏል ኮሚቴው።(ምንጭ፡-ፋና)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top