በእነእስክንድር ነጋ ቅሬታ ላይ የኢሳት ቦርድ የሰጠው መግለጫ !
ለ ሚመለከተው ሁሉ
የኢሳትን አሰራር ስለመግለጥ፣
ከአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት የውጭ ድጋፍ ኮሚቴ “ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት ( ባልደራስ) ሰብሳቢ በሆነው የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ አገዛዙ ለሚወስደው እርምጃ ኢሳት ሐላፊነቱን እንደሚወስድ ስለማሳወቅ” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ ተመልክተናዋል። ጉዳዩ የሕዝብ መነጋገሪያ ስለሆነና ኢሳትም የኢትዮጵያን ህዝብ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማገልገል ዋናው አላማ በመሆኑ የኢሳት ቦርድ በኖቨምበር 27 2019 ባደረገው ስብሰባ በአደባባይ ለቀረበው ቅሬታ በአደባባይ መልስ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
የቅሬታው ዋና ሃሳብ “ሰኞ” ኖቨምበር 25፣ 2019 በቀረበው የኢሳት እለታዊ ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቨርጂኒያ ሂልተን አሌክሳንደሪያ ያደረገው ንግግር ተዛብቶ መቅረቡን በመጥቀስ የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ፣ “ይህ የተሳሳተ ዘገባ የማይታረም ከሆነ በሂልተን አሌክሳንደሪያ ተሰብስቦ ውሳኔ ያሳለፈውን ህዝብ በኢሳት ቨርጂኒያ ቢሮ ተቃውሞ የምንጠራ እና ዲሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን ሌሎች ተከታታይ ጥሪዎችን እንደምናስተላልፍ ከወዲሁ እንድታውቁት እንፈልጋለን።” የሚል ነው።
ቦርዱም የቀረበውን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የሚከተለውን ማብራሪያና ውሳኔ መስጠቱን በአክብሮት ይገልጻል።
እለታዊ ዝግጅት የኢሳት ጋዜጠኞችና እነርሱ የሚጋብዙዋቸው እንግዶች በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን በነጻነት የሚገልጹበት መድረክ መሆኑ የታወቀ ነው። ዝግጅቱ የዜና፣ የርዕስ አንቀጽ ወይም የልዩ ዘገባ ዝግጅትም አይደለም። በማንኛውም ነጽ ሚዲያ የውይይት መድረኮች ላይ እንደሚታየው ዝግጅቱን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ላዳመጠ የውይይቱ ተካፋይ የሆኑ ጋዜጠኞች አስተያየት እንኳን አንድ ወጥ አይደለም። በእኛ አረዳድ ጉዳዩ የሃሳብ ልዩነትን የሚመለከት ሆኖ ነው ያገኘነው።በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ የኢሳትቦርድ ኃላፊነት በአንድ በኩል የጋዜጠኞቹን በነጻ ሃሳብ መግለጽ ማክበርና ማስከበር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የኢሳትን ለሕዝብ ተጠያቂነትና ለማንኛውም አይነት ቅሬታና ተቃውሞ ክፍትነት ማረጋገጥ ነው።
ኢሳት የሃሳብ ልዩነትንየሚያስተናግድበት ዋናው መንገድ የኢሳትን መድረክ የተለያዩ ሃሳቦችን ለሚያንጸባርቁ ሰዎች ክፍት ማድረግ ነው። ስለዚህ መረጃዬ ተዛብቶብኛል የሚል ሰውም ሆነ ማንኛውም ሃሳቡን በኢሳት ላይ መግለጥ የሚፈልግ ሰው በአካል ወይም በስልክ አስተያየቱን መስጠት ይችላል፤ ይህ ትናንት የተከተልነው፣ ዛሬ እየተከተልን ያለነውና ነገም የምንከተለው አሰራራችን ነው። ኢሳትም ሆነ የኢሳት ጋዜጠኞች ለጋዜጠኛ እስክንድር እንግዳዎች አይደሉም። በኢሳትና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መካከል ያለው የአላማ ና የትግል ግንኙነት አሁን የተጀመረ አይደለም። ሁለቱም ለሃሳብ ነጻነት ባደረጉት ትግል ዛሬ ለሚታየው አንጻራዊ ነጻነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ሃቅ ነው።
ጋዜጠኛ እስክንድር በእስር ቤት ይማቅቅ በነበረበት ጊዜ ውስጥ ኢሳት ለእስክንድር ነጻነት ያደረገው ትግል፣ ከእስር ከተፈታም በሁዋላ ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን በመስጠት እስክንድር የሚታገልለት ዲሞክራሲ ዋነኛ መገለጫ የሆነው ሃሳብን በነጻነት የመናገር መብት በአገራችን ሙሉ በሙሉ እውን እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ ሲያደርግ ቆይቷል። ጋዜጠኛ እስክንድር በጠራውና አሁን ተቃውሞ በቀረበበት የሜሪላንድ ስብሰባ እንዲሳካ እንኳን ኢሳት በእለታዊ ዝግጅቱ በየቀኑ ሲያስተዋውቅ እንደቆየም ማንም ዝግጅቶችን የተከታተለ ሰው ሁሉ የሚመሰክረው ነው። በእስክንድርና በኢሳት መካከል ያለው ግንኙነት ይህን ዓይነት ታሪክ እያለው በዚህ ሰዓት፣ “ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በመንግስት በኩል ለሚወሰደበት እርምጃ ኢሳት ተጠያቂ ይሆናል” የሚልማስጠንቀቂያ አስፈላጊ አይመስለንም።
የኢሳት ቦር