Connect with us

የካንሰር በሽታ ምልክቶች…

የካንሰር በሽታ ምልክቶች…
Photo: Facebook

ዜና

የካንሰር በሽታ ምልክቶች…

የካንሰር በሽታ ምልክቶች…

ካንሰር በሀገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙዎችን እየቀጠፈ የሚገኝ አስከፊ እና ገዳይ በሽታ ነው።

ካንሰር በአንድ የተወሰነ መንስኤ ብቻ የሚከሰት ሳይሆን በብዙ የጤና ጉድለቶች ውህደት ሳቢያ የሚከሰት በሽታ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በዋናነትም በሰውነት ህዋሶች እድገት መስተጓጎል ምክንያት የሚከሰት ነው።

ሲጋራ ማጨስና የአልኮል መጠጦችን አብዝቶ መጠቀም፣ ለረጅም ጊዜ ለፀሀይ ብርሃን መጋለጥ፣ ከመርዛማ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ጋር መስራት፣ የሰውነት ዘረመል ጤናማ በሆነ መንገድ ሳይሰራ ሲቀር እንዲሁም ሰውነታችን በተለያዩ ቫይረሶች ሲጠቃ ለካንሰር በሽታ የሚያልጡ አጋጣሚዎች ናቸው።

ከካንሰር አይነቶች ውስጥም የደም ካንሰር፣ የማህፀን ካንሰር፣ የጉሮሮ ካንሰር፣ የጭንቅላት ካንሰር እንዲሁም የጡት ካንሰር ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸውን በፍጥነት ባለማወቃቸው ምክንያት ብዙ ጊዜ ለከፋ ችግር ሲዳረጉ ይስተዋላል።

በካንሰር በሽታ የተጠቁ ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊስተዋሉባቸው ይችላሉ፥

የክብደት መቀነስ

አንዱ የካንስር ምልክት ክብደት መቀነስ ነው፡፡

ካንሰር ደም ውስጥ ካለ ያለምንም ምክንያት ማለትም እንቅስቃሴ ሳናደርግ፣ የአመጋገብ ስርዓታችንን ሳንቀይር የሰውነት ክብደት ይቀንሳል ፡፡

ያልተቋረጠ ህመም

ሌላው የካንሰር በሽታ ምልክት ያልተቋረጠ ህመም ሲሆን ፥ የህመም ስሜቱም በየትኛውም የህመም ማስታገሻ መቆም የማይችል ነው፡፡

ተደጋጋሚ የራስ ምታት
ተድጋጋሚ የራስ ምታት የካንሰር በሽታ ምልክት ሲሆን፥ በተለይም በደም ካንሰር በመጀመሪያ ደረጃ የሚታይ ምልክት መሆኑን ይነገራል።

የቆዳ መቀየር
ይህ ምልክት ደግሞ ብዙ ጊዜ የቆዳ ካንሰር በያዛቸው ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፥ በተመሳሳይም ሌሎች የካንደር አይነቶች ላይም ሊስተዋል ይችላል፡፡

የቆዳ መቅላት፣ መጥቆር፣ ቢጫ መሆን ማሳከክ እንዲሁም መድማትን ያጠቃልላል።

የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሌላኛው የካንሰር ምልክት ነው፡፡

ከምግብ ጋር በተያያዘም የቆርቆሮ ምግቦች በተለይም ቲማቲም፣ የተጠበሰ ድንች (ችፕስ)፣ የገበታ ቅቤ፣ ፈንዲሻ፣ ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች እንዲሁም አልኮል መጠቀም በካንሰር የመያዝ እድላችንን ከፍ እንደሚደርገው ተመላክቷል፡፡

እብጠት
በሰውነታችን የተለያዩ አካባቢዎች እብጠት ከታየት የመጀመሪያ ደረጃ የካንሰር ደረጃ ምልክት ሊሆን ስለሚችል በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ አስፈላጊ ነው።

በተለይም እብጠቱ በሂደት እየሰፋ የሚሄድ ከሆነ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ነው የተባለው።

ምንጭ፡-hhdresearch.org

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top