Connect with us

የዋጋ ግሽበቱ በዜጎችና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እያሳደረ ነው ተባለ

የዋጋ ግሽበቱ በዜጎችና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እያሳደረ ነው ተባለ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የዋጋ ግሽበቱ በዜጎችና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እያሳደረ ነው ተባለ

የዋጋ ግሽበቱ በነጠላ አሃዝ ሊገደብ ባለማቻሉ በዜጎች እና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

ቋሚ ኮሚቴው ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ/ም የገንዘብ ሚኒስትር እና የተጠሪ ተቋማትን የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት በአገሪቱ የሚስተዋለው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት በነጠላ አሀዝ ሊገደብ ባለመቻሉና በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት በዜጎች እና በክፍለ- ኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅኖ እያሳደረ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው በአዲሱ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም፣ በዋጋ ግሽበቱ እና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ዙሪያ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት በተጠሪ ተቋማት የመዋቅር መሻሻያ እየተደረገ እንደሆነ እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በጥንቃቄ እየሰራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የዋጋ ግሽበትን በተመለከተ ሚኒስትሩ የተረጋጋ ዋጋ እንዲኖር የፊስካል ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ማድረግ የመንግስት ተቀዳሚ እርምጃ እንደሆነ አንስተው በማዕከላዊ ስታትስቲክስ መረጃ መሰረት በ2012 ዓ/ም በመስከረም ወር አጠቃላይ የ12 ወራት እድገት 13.6 በመቶ ሲሆን ባለፉት ወራቶች ተጨማሪ እድገት በማሳየቱ የምግብ ነክ ፍጆታዎች 15.6 በመቶ እንዲሁም ምግብ ነክ ባልሆኑ እቃዎች 11.2 በመቶ የዋጋ ንረት እንደታ የባቸው አስረድተዋል፡፡

ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ግሽበቱ እንዳይባባስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጀት እየሰራ ሲሆን የምግብ ነክ ዋጋን ለማረጋጋት 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ከውጭ አገር ተገዝቶ በስርጭት ላይ እንደሚገኝ ነው ሚነስትሩ የገለጹት፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top