Connect with us

በድንገተኛ ናዳ የጣርማ በር መንገድ ተዘጋ

በድንገተኛ ናዳ የጣርማ በር መንገድ ተዘጋ
Photo: Facebook

ዜና

በድንገተኛ ናዳ የጣርማ በር መንገድ ተዘጋ

በድንገተኛ ናዳ ምክንያት የተዘጋውን የጣርማበር መንገድ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው።

በአካባቢው በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ሳብያ ጣርማበር አካባቢ የመሬት ናዳ ተከስቶ መንገዱን በመዝጋቱ ትራንስፖርቱ ተቋርጧል። በአሁን ሰአት የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ቦታው ላይ ማሽኖችን አሰማርቶ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

ከሁለት ሰአታት በኋላም የተዘጋውን መንገድ ክፍት እንደሚደረግና መደበኛ የትራንስፖርቱ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ይገልጻል።

አሽከርካሪዎችም መንገዱ እስኪከፈት በትእግስት እንዲጠባበቁ የባለስልጣኑ መ/ቤት ትብብራችሁን ይጠይቃል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top