Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍም ደረጃውን እንዳስጠበቀ መቆየቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍም ደረጃውን እንዳስጠበቀ መቆየቱን አስታወቀ
Photo: Fortune

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍም ደረጃውን እንዳስጠበቀ መቆየቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዘንድሮ የአውሮላን አደጋ፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ቢፈታተኑትም የአፍሪካ ትልቁ እና ትርፋማ አየር መንገድ በመሆን ደረጃውን እንዳጠበቀ መቆየቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አስታወቁ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው የዓለማችን ታላላቅ ኮርፖሬሽኖችና የምጣኔ ሀብት መሪዎች በተገኙበት የ2019 የፎርቹን ዓለማቀፍ መድረክ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

አየር መንገዱ የ15 ዓመታት ስትራተጂያዊ የእድገት እቅድ አካል በሆነው ራእይ 2025 መካከለኛ የትግበራ ዘመን ላይ እንደሚገኝ እና ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ አምስት እጥፍ እድገት ማስመዝገቡን በመድረኩ ላይ አስታውቀዋል፡፡

“የኢትዮጵያ አየር መንገድ 40 ብቻ ከነበሩት አውሮፕላኖቹ አሁን 121 ደርሷል፤ ዛሬ በመላው ዓለም በሚገኙ 5 አህጉራት ወደ 125 አለማቀፍ መዳረሻዎች መብረር ችለናል…” ሲሉ አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡

የቦይንግ ማክስ ኤት አውሮፕላን ላይ ካጋጠመው አደጋ ጋር በተያያዘም ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በመነጋገር አደጋው በተከሰተበት አካባቢ መታሰቢያ ሀውልት ለማስቀመጥ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚጠቅሙ እንደ ሆስፒታል፣ መንገድ እና የመሳሰሉትን መሰረተ ልማቶች ለመስራ መታሰቡን ገልፀዋል፡፡

በጠቅላላው 30 አይሮፕላኖችን ከቦይንግ ለመግዛት ትዕዛዝ የተሰጠ ቢሆንም አውሮፕላኖቹን ለመረከብ አሁንም ውሳኔ ላይ አለመደረሱን እና አጠቃላይ በአውሮፕላኖቹን ላይ የተሰሩ ማስተካከያዎችን እንዲሁም በአይሮፕላኖቹ ላይ የታዩት ችግሮች ሁሉም መፈታታቸውን እርግጠኛ መሆን እንደሚያስፍልግ ገልጸዋል፡፡

አይሮፕላኖቹን ለማብረር የመጨረሻዎቹ ነው የምንሆነው ያሉት አቶ ተወልደ 110 በመቶ በአውሮፕላኖቹ እርግጠኛ መሆን እንፈልጋለንም ሲሉ አክለዋል፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top