Connect with us

ፊታችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

ፊታችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?
Photo: Facebook

ጤና

ፊታችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

ፊታችን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን በተለያዩ መንገዶች ማስወገድ ይቻላል።

ፈታችን ላይ የሚወጡ እነዚህ አላስፈላጊ ነገሮች ለቆዳችን ጤና ጠንቅ ከመሆናቸው ባሻገር ውበታችን እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡

እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለማስወገድም በቀጣይ የተዘረዘሩትን ማስወገጃ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ከፊታችን ላይ ማስወገድ እንችላለን፡፡

ቫይታሚን ሲ

ቫይታሚን ሲ ፊትን ከአላስፈላጊ ጥቁር ነጠብጣቦች ለመከላከል አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ቫይታሚን ሲ ማለትም ፍራፍሬዎችን መመገብም ሆነ ከፍራፍሬ ውህድ የተሰሩ የተለያዩ ውጤቶችን በመጠቀም ያማረና ፅዱ ቆዳ እንዲኖረን በእጅጉ ያግዘናል፡፡

ኮጂክ አሲድ

ኮጂክ አሲድ ቆዳን ከማንፃቱ ባሻገር ቆዳችንን ከፀሃይ ለመከላከል ያስችላል ፤ በእንጉዳይ የበለፀገ በመሆኑም ለቆዳ ተስማሚ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ኮጂክ አሲድን በተለያ መንገድ በገበያ ላይ ማግኘት እንችላለን፤ ለምሳሌ በዱቄት፣በክሬም፣በመድሃኒት መልኩ ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን።

አኩሪ አተር

ሌላው የጠቆረ ቆዳን ለመከላከል የሚጠቅሙን ከአኩሪ አተር የተሰሩ የተለያዩ መከለከያ መንገዶች እናገኛለን።

ይህም ጥቁር ቆዳን በማንጻት ያማረ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ያግዘናል፡፡

ጠዋት እና ማታም የጠቆረ ቆዳችንን በመቀባት ማስወገድ እንችላለን።

አዚሊክ አሲድ

-አዚሊክ አሲድ ገብስ፣አጃ እና ስንዴ ከምሳሰሉ ጥራጥሬዎች የሚገኝ ሲሆን፥ ቆዳችን ከጥቁር ነጠብጣብ የፀዳ እና ያማረ እንዲሆን ይረዳናል፡፡

በተጨማሪም ፊታችን ላይ ከሚወጡ ጥቁር ጠባሳዎች ከማጥፋት ባሻገር ፊታችን ላይ ሉትን ባክቴሪያዎችን ያስወግድልናል ፡፡

ይህንንም በቀን ሁልት ጊዜ በመጠቀም ለውጡን ማየት እንችላለን፡፡

የፀሃይ መከላከያ ክሬም(sun ceame)

የፀሃይ መከላከያ ክሬም ፊታችን ያማረ እንዲሆን ከሚረዱን መንገዶች አንዱ ሲሆን፥ ቆዳችንን ከሚጎዱ ነገሮችም ይከላከላል ፡፡

ክሬሙን ሁልጊዜ በመጠቀምም ፊታችን ከመሸብሸብ ብሎም ከጥቁር ነጠብጣቦች መጠበቅ እንችላለን፡፡

ምንጭ ፦http://www.buzznoble.com

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top