Connect with us

ወላይታ ላይ ጅብ ባደረሰው ጉዳት ሦስት ሕጻናት ሞቱ

ወላይታ ላይ ጅብ ባደረሰው ጉዳት ሦስት ሕጻናት ሞቱ
Photo: Facebook

ዜና

ወላይታ ላይ ጅብ ባደረሰው ጉዳት ሦስት ሕጻናት ሞቱ

በወላይታ ዞን ጅብ የሦስት ሕጻናትን ሕይወት አጠፋ

በወላይታ ዞን ጅብ ባደረሰው ጉዳት የሦስት ሕጻናት ሕይወት ሲጠፋ በሌላ አንድ የሁለት ዓመት ልጅ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰ።

የወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ እንዳስታወቀው በህጻናቱ ላይ የሞትና የአካል ጉዳት የደረሰው በወረዳው “ኮዶ ጋውሊያ” በተባለ የገጠር ቀበሌ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አሳቻ ሰዓታት ጠብቆ የመጣ ጅብ ባደረሰው ጥቃት ነው።

ጅቡ ባደረሰው ጥቃት ሦስት ህጻናት ሕይወታቸውን ሲያጡ በአንዲት የሁለት ዓመት ልጅ ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ስምኦን ጣዲሶ ተናግረዋል።

በቀጣይ ጅቡ መሰል ጥቃቶችን እንዳያደርስ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበል እርምጃ እንደሚወሰድ አመልክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top