Connect with us

ቲማቲም መመገብ የወንድ ዘር ፍሬን ጥራት ለማሻሻል ይረዳል-ጥናት

ቲማቲም መመገብ የወንድ ዘር ፍሬን ጥራት ለማሻሻል ይረዳል-ጥናት
Photo: Facebook

ጤና

ቲማቲም መመገብ የወንድ ዘር ፍሬን ጥራት ለማሻሻል ይረዳል-ጥናት

ቲማቲም መመገብ የወንድ ዘር ፍሬን ጥራት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን አንድ ጥናት አመላክቷል።

በወንዶች ላይ የሚከሰት የወንድ ዘር ፍሬ ጥራት መቀነስ ለመሃንነት የሚዳርግ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ ።

ለዚህም ችግር መፈጠር ምክንያም ተመራማሪዎች የተለያዩ መንስኤዎችን ያነሳሉ።

የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ፣ የአዕምሮ ጭንቀት፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴወዎችን አለማዘውተር፣ የውስጥ ሱሪ አለባበስ ሁኔታ እና የመሳሰሉት ችግሮች የወንድ ልጅን የዘር ፍሬ ጤናማነት የሚቀንሱ መንስኤዎች ናቸው።

ሰሞኑን ይፋ የተደገ አንድ ጥናት እንዳመላከተው ቲማቲም መመገብ የወንድ ዘር ፍሬን ጤና ለመጠበቅ ፍቱን መድሃኒት መሆኑን አመላክቷል።

በጥናቱ ቲማቲም በውስጡ የወንድ ዘር ፍሬን ጥራት ለማሻሻል የሚያስችል ላይኮፔን የተሰኘ ንጥረ ነገር ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ስለሆነም አንድ ጤናማ ወንድ በቀን ሁለት የሾርባ ማንኪያ መጠን ያለው ቲማቲምን ቢመገብ በሰውነቱ ውስጥ ያለውን የዘር ፍሬ ጥራት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑ ተመላክቷል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top