Connect with us

ባለስልጣኑ የውሃ አገልግሎት ክፍያ ባልፈጸሙ ደንበኞች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

ባለስልጣኑ የውሃ አገልግሎት ክፍያ ባልፈጸሙ ደንበኞች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው
Photo: Facebook

ዜና

ባለስልጣኑ የውሃ አገልግሎት ክፍያ ባልፈጸሙ ደንበኞች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባስልጣን 56ሺ በላይ የሚሆኑት የጋራ መኖሪያ ቤት ደንበኞች የውሃ አገልግሎት ክፍያ እየፈጸሙ አይደለም፡፡

ይህም ከ80 በመቶ በላይ ወጪውን ከውሃ ሽያጭ የሚሸፍነው ባስልጣኑ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮበታል፡፡

ባለስልጣኑ የክፍያ ስርዓቱን በማዘመን እና ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ ከሀምሌ 26/2011 ዓ.ም ጀምሮ በኢትጵያ ንግድ ባንክ በኩል ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህንን የተሳለጠ የክፍያ ስርአት በመጠቀም ደንበኞች የውሃ አገልግሎት ክፍያ እንዲፈጽሙ በተለያዩ ጊዜያት በብዙሀን መገናኛ እና ፤በቆጣሪ አንባቢዎች አማካኝነት ቢያስጠነቅቅም ከ28ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ያለባው 56ሺ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ግዴታቸውን መወጣት አልቻሉም ፡፡

ይህ ግዴታን ያለመወጣት ችግር ከ5 ወር ጀምሮ ለአመታት የቆየ መሆኑ ደግሞ በባለስልጣኑ የገቢ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል፡፡

በዚህም ምክኒያት ባስልጣኑ በሁሉም የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 17/ 2012 ዓ.ም የሚቆይ ጊዜያዊ የቅጣት መክፈያ ጣቢያ አቋቁሞ ተግባራዊ ሰራ ጀምሯል ፡፡

ውዝፍ ክፍያ ያለባቸው ደንበኞችም የአገልግሎት ክፍያውንም ሆነ 480 ብር የቅጣት ክፍያ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በመክፈል የውሃ አገልግሎቱ እንዲቀጠል ማድረግ እንደሚችሉ አስገንዝቧል፡፡(ምንጭ፡- የአ/አ ውሀና ፍሳሽ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top