Connect with us

ለጥሩ የአፍ ውስጥ እንክብካቤ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል…

ለጥሩ የአፍ ውስጥ እንክብካቤ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል…
Photo: Facebook

ጤና

ለጥሩ የአፍ ውስጥ እንክብካቤ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል…

የአፍ ውስጥ በሽታዎች እንደ ጥርስ መበስበስና የድድ በሽታ በሰፊው የሚከሰት ቢሆንም መከላከል ይቻላል።

በአፍ ውስጥ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች አንዱ ደግሞ፥ የአፍ ውስጥ ንጽህናን መጠበቅ መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህ በተጨማሪም መደበኛ የጥርስ ምርመራ ማድረግ እና አጋላጭ ሁኔታዎችን በመከላከል ጥሩ የአፍ እና አጠቃላይ ጤንነትም መጠበቅ እንደምንችል ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ለጥሩ የአፍ ውስጥ እንክብካቤ…

• በየቀኑ ሁለት ጊዜ ለሁለት ደቂቃዎች ፍሎራይድ ባለው የጥርስ ሳሙና በክብ ቅርጽ በማሽከርከር በእጅ ወይም በኤሌክትሪክ የጥርስ ብሩሽ መቦረሽ የጥርስ የመበስበስ እና የድድ በሽታ ለመቀነስ ይረዳል።

• የጥርስ ሳሙናዎ 1000-1500 (ፒ.ፒ.ኤፍ ) ፍሎራይድ መያዙን ከመግዛትዎ በፊት ያረጋግጡ።

• ጥርስ እንደተቦረሸ ወዲያውኑ በውሃ አለመለቅለቅ፤ ከዚህ ይልቅ በአፍ ውስጥ የበዛውን ሳሙና ብቻ መጥፋት፤ይህም በጥርስ ሳሙና ውስጥ የተከማቸዉን ፍሎራይድ እንዳይታጠብ ያደርጋል።

• ጥርስ መቦረሽ በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ፍሎራይድ ያለው የአፍ መታጠቢያ ፈሳሽ መጠቀምና አስኳር ነፃ የሆነ ማስቲካ ማኘክ የጥርስ መበስበስ ለመከላከል ሊረዳ ይችላል።

• መደበኛ የሆነ በጥርሶች መካከል ጽዳት በጥርሶች መሀል የተሰገሰጉ ምግቦችን ለማውጣት ይረዳል ይህም የድድ በሽታንና መጥፎ የአፍ ጠረን መከሰትን ሊቀንስ ይችላል።

• የሚጠቀሙትን የስኳር መጠንዎን በቀን ወደ 6 ማንኪያ ይገድቡ፤ በየቀኑ ጣፋጭ ምግቦችን በብዛት መጠቀም ያስወግዱ።

• ትንባሆ አለመጠቀም፣ አልኮልም መጥኖ መጠቀም፦ ትንባሆ እና አልኮል ለአፍ ውስጥ ካንሰር መጋለጥን፣ የጥርሶች ቀለም መበላሸትን፣ የጥርስ መቦርቦርን እና መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጣም ይችላል።

• መውደቅ እና አካላዊ ግንኙነትን በሚያካትት ስፖርት እና ጨዋታዎች ወቅት በባለሙያ የተሠራ የጥርስ መከላከያ መጠቀም።

• የጥርስ ሐኪም ጋር በየጊዜው መከታተልና ምክር መቀበል።

ምንጭ :-ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top