Connect with us

ሶስት ኩላሊቶች እንዳሏት የተነገራት ቻይናዊት አንዱን ለመለገስ እንደምትፈልግ ተናገረች

ሶስት ኩላሊቶች እንዳሏት የተነገራት ቻይናዊት አንዱን ለመለገስ እንደምትፈልግ ተናገረች
Photo: Facebook

ጤና

ሶስት ኩላሊቶች እንዳሏት የተነገራት ቻይናዊት አንዱን ለመለገስ እንደምትፈልግ ተናገረች

አንዲት ቻይናዊት ሴት ሦስት ኩላሊት እንዳሏት ዶክተሮች ማረጋገጣቸዉና እንስቷም አንዱን ለሎሎች ለመለገስ እንደምትፈልግ መናገሯኝ ግሎባል ታይምስ ዘግቧ፡፡

ነዋሪነቷን በቻይና ጃንግ ሺ ግዛት ዉስጥ ሲንይ በተባለ ከተማ ያደረገችዉ ይህቸዉ እንስት ከመደበኛ በላይ ቶሎቶ ሽንት

ጤናማ ከሚባለው የሽንት መምጫ ጊዜ በበለጠ በተደጋጋሚ ሽንት የመሽናት ፍላጎትን ይታይባና ከፍተኛ የህመም ስሜት ይሰማት ነበር “መተኛት የምችለዉ በየቀኑ ለአምስት ወይም ስድስት ሰዓታት ብቻ ነበር” በማለት ትናገራለች፡፡

ዶክተሮች እንደሚሉት ከሆነ ይህች ታማሚ ያጋጠማት ሁኔታ ከ1500 ሰዎች በአንድ ሰዉ የማጋጥም እድል እንዳለዉ ያስረዳሉ፡፡ ክስተቱም በፅንስ ወቅት የሚያጋጥም እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የበሽታው ውስብስብ ችግሮች ካላስከተለ በቀላሉ በመድኃኒት እና ደም በመተካት ሊታከም ይችላል ሲሉ ሀኪሞቹ አክለዉ ገልፀዋል፡፡

አንደዘገባዉ ከሆነ ሴትዮዋ በተደረገላት ሀክምና መዳን መቻሏ ተዘግቧ፡፡

በአንድ ግለሰብ ላይ ከሁለት በላይ ኩላሊቶች ሲጋጥሙና የህመም ስሜት ከፈጠሩ ሐኪሞች ብዙውን ጊዜ የቀዶ ጥገና ሕክምና እንዲደረግ ይመክራሉ ፡፡

አንዳንድ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አንደሚገልፁት ከሆነ ተመሳሳይ ሁኔታዎች በቤተሰባቸዉ ዉስጥ እንዳጋጠመና በህይወታቸዉ ላይም ምንም አይነት ጉዳት እንዳላስከተለ ይናገራሉ፡፡ ሲና ወየቦ የተባለች ግለሰብ አያቴ 70 ዓመት ሲሆነው ሦስት ኩላሊቶች እንዳሉት አዉቆ ነበር ብላለች፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top