Connect with us

የድረሱልን ጥሪ!… ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

የድረሱልን ጥሪ!... ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የድረሱልን ጥሪ!… ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

የድረሱልን ጥሪ!… ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

ሁላችንም እንደምናውቀው በክልላችን በ3ዞኖች በ8ወረዳዎች በ23ቀበሌዎች የበረሃአንበጣ መንጋ ተከስቶ በመኸር ሰብል ልማታችን ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
.
የበረሃ አንበጣ መንጋው ከየመንና ሶማሌ ላንድ ተነስቶ በአፋር ክልል አድርጎ ወደ ክልላችን ገብቷል።ማለትም በአፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር፣ ሰሜንወሎ እና ደቡብወሎ ዞን አስተዳደሮች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
.
የተዛመተውን የበረሃ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ዘርፈ ብዙ ስራ እየተሰራ ነው። ይኸውም በተደረገው አሰሳ እስካሁን በ7,932 ሄክታር መሬት ላይ የአንበጣ መንጋው የተከሰተ ሲሆን በ3204.5 ሄክታር ማሣ ላይ የመከላከል ሰራው እየተሰራ ይገኛል። የመከላከል ስራውም በዋነኛነት በሰው ሃይል ጉልበትና በአውሮኘላን በኬሚካል ርጭት የታገዘ ሲሆን 1165 ሊትር ኬሚካል እስካሁን ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ይህ የበረሃ አንበጣ መንጋን የመከላከል ስራው ሀሉንም የሕብረተሰብ ክፍል በማስተባበር እየተሰራ ሲሆን በአንበጣ መንጋ የተወረሩ አካባቢዎችን የማስለቀቅ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላው አካባቢ እየተሸጋገረ ሲሆን በክልሉ ውስጥ ሌሎች ያልተከሰተባቸው አካባቢዎችም አስቀድመው ለመከላከል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

በመሆኑም ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይህን ክስተት የወቅቱ አጅንዳ አድርገው ህብረተሰቡን በማነቃነቅ የተከሰተውን የአንበጣን መንጋ ለመከላከል መረባረብ አለብን።

በተለይም የበረሃ የአንበጣ መንጋው የስርጭት መጠኑንና የሚያስትለውን ጉዳት ማስቆም የሚቻለው የበረሃ የአንበጣ መንጋው ተፈልፍሎ የሚወጣበት አፋር በረሃ ውስጥ በመሆኑ የፌዴራሉ ግብርና ሚንስቴር አፋጣኝ የአውሮፕላን ኬሚካል ርጭት እንዲያደርግና የአንበጣውን ዑደት ህይወት እንዲቋረጥ ለማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም አሁን ያለውና በሚቀጥሉት ወራት የሚኖረው የአየር ፀባይ ለአንበጣ ዕድገት ምቹ ስለሆነ መዘናጋት ሳይፈጠር በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተጀመረው የአንበጣ ክስተት አሰሳ፣ የመከላከልና ህብረተሰቡን በማስተባበርና በማሳተፍ የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ እያልን የአንበጣ መንጋው ከሀገራችን ጨርሶ እስከሚጠፋ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን በመገንዘብ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራችን ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

ይህ የበረሃ አንበጣ ሊያስከትል የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ችግር በመረዳት ሁሉም የህበረተሰብ ክፍል ባለው አቅም ሁሉ ርብርብ እንዲያደርግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

<<ሁላችንም በመተባበር ግብርናችን የገጠመውን ችግር እንታደገዋለን>>

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top