Connect with us

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ በአፍረካ ካሉ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ በአፍረካ ካሉ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ
Photo: Facebook

ዜና

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ በአፍረካ ካሉ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ በአፍረካ ካሉ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኖ መመረጡን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ይህንን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሰት በ1950 ዓ.ም የተቋቋመው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመሰረት የመቀበል አቅሙ 33 ተማሪዎችን ብቻ የነበረ ሲሆን አሁን የቅበላ አቅሙን እስከ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) አድርሷል ብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት 13 ካምፓሶች፣10 ኮሌጆች፣ 2 የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩቶች፣ 12 የምርምር ኢንስቲቲዩቶች እና 2 የማስተማሪያና የከፍተኛ ህክምና መስጫ ሆስፒታሎችን (የእንስሳትና የሰው) በመያዝ በተለያዩ የትምህርት መርሃ-ግብሮች በ73 የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ-ግብር፣ በ345 የድህረ-ምረቃ መርሃ ግብሮች፣ በ90 የጥናትና ምርምር መስኮች የዶክትሬት መርሃ ግብሮችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ይህ ቁጥር በጤና ሳይንስ ዘርፍ በልዩ ልዩ እውቀቶች የተለየ ጥናት እያደረጉ ያሉትን ተመራማሪዎች ሳያካትት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2014 እ.ኤ.አ ከአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች 18ኛ ደረጃ፣ በ2015 እ.ኤ.አ ከአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች የ16ኛ ደረጃ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ማለትም በ2019 እ.ኤ.አ ከአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች በ10ኛ ደረጃ ሆኖ ሊመዘገብ ችሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመማርና የማስተማሩ፤ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግሩ እና የማህበረሰብ አገልግሎቱ የተሻለ ሆኖ የማየት ስንቅ ሰንቆ ለበለጠ ጥራትና ውጤት ተግቶና ተናቦ እንደሚሰራ የገለፀ ሲሆን ለኢትዮጵያ ሰላም ዕድገትና ብልጽግና ተመኝቷል፡፡

ምንጭ:- ኢ.ፕ.ድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top