Connect with us

እንቅልፍ የማጣት ችግር ለልብ በሽታና ለጭንቅላት ደም መፍሰስ ያጋልጣል

እንቅልፍ የማጣት ችግር ለልብ በሽታና ለጭንቅላት ደም መፍሰስ ያጋልጣል
Photo: Facebook

ጤና

እንቅልፍ የማጣት ችግር ለልብ በሽታና ለጭንቅላት ደም መፍሰስ ያጋልጣል

የእንቅልፍ ችግር ያለባቸው ሰዎች ለልብ በሽታና ለጭንቅላት ደም መፍሰስ እንዲሁም ከአዕምሮ ጋር ተያያዥነት ላላቸው በሽታዎች የመጋለጥ እድል እንዳላቸው አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ፡፡

የእንቅልፍ ችግር ምልክት ባለባቸው ሰዎች ላይ ለ10 ዓመታት ክትትል የተደረገባቸው ሲሆን በዚህም 130 ሺህ 32 የጭንቅላት ደም መፍሰስ ፣ የልብ በሽታ እና ተመሳሳይ የበሽታ ምልክቶት እንደታየባቸው ተጠቁሟል፡፡

የእንቅልፍ ማጣት ችግር ሶስት አይነት ምልክቶች ያሉት ሲሆን እነዚህም የመተኛት ወይም ተኝቶ የመቆየት ችግር ፣ በጠዋት ቀድሞ መነሳት እና በቀን ውሏቸው ነገሮችን በትኩረት የመከታተል ችግሮች ናቸው፡፡

በዚህ ጥናትም የመተኛት ወይም ተኝቶ የመቆየት ችግር ያለባቸው ሰዎች ችግሩ ከሌለባቸው ሰዎች አንፃር 9 በመቶ ለጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ እና ለልብ በሽታ ይጋለጣሉ፡፡

በተመሳሳይ በእንቅልፍ ማጣት ችግር በቀን ውሏቸው ነገሮችን በትኩረት የመከታተል ችግር ያለባቸው ሰዎች ምልክቱ ከሌለባቸው ሰዎች አንፃር 13 በመቶ ከጭንቅላት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች የመጋለጥ እድል አላቸው፡፡

እንቅልፍ የማጣት ችግር ምልክት እና እነዚህ በሽታዎች ከጎልማሳዎችና ከፍተኛ የደም ግፊት ከሌለባቸው ሰዎች ጋር ከፍተኛ ግንኙነት እንዳለው ነው የተጠቆመው፡፡

ጥናቱ እንቅልፋ የማጣት ችግር ምልክት እና የሽታዎቹን ምክንያት እና ዉጤት አያሳይም ያሉት ተመራማሪዎቹ ጥናቱ ያለውን ግንኙነት ብቻ የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- news-medical

Continue Reading
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top