Connect with us

ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን በጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ ጊዜያዊ የክፍያ ጣቢያ ሊከፍት ነው

ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን በጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ ጊዜያዊ የክፍያ ጣቢያ ሊከፍት ነው
Photo: Facebook

ዜና

ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን በጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ ጊዜያዊ የክፍያ ጣቢያ ሊከፍት ነው

~አብዛኞች ደንበኞቹ በውዝፍ ዕዳ ተዘፍቀዋል፣

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የተቋሙ ደንበኞች የተገለገሉበትን ውዝፍ ሂሳብ እንዲከፍሉ በተለያዩ የህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በማስታወቂያ ሲያስነግር እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ቀድሞ በለሁሉ ይፈፀም የነበረውን የአከፋፈል ሂደት በማሻሻል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እና ከሶስት በላይ አማራጮች ባሉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት መስጠጥ ቢጀምርም ችግሩ ሙሉ ለሙሉ ሊቀረፍ አልቻለም፡፡

ከጥቂት የህብረተሰብ ክፍሎች በቀር የተጠራቀመ አብዛኞቹ ውዝፍ ዕዳቸውን ባለመክፈላቸው ባለስልጣኑ መሰብሰብ ያለበትን ገቢ አልሰበሰበም፡፡

በመሆኑም ባለስልጣኑ ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 17/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከውኃ ደንበኞች ንዑስ የስራ ሂደት የተውጣጣ ባለሙያዎችን ያዋቀረ ግብረ ኃይል አቋቁሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ በሁሉም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጊዜያዊ የክፍያ ጣቢያ ከፍቷል፡፡

በመሆኑም የባለስልጣኑ የውኃ ደንበኞች በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት የተጠራቀመ ውዝፍ ዕዳቸውን በአግባቡ እንዲፈፅሙ እያሳሰበ ይኼን ዕድል በማይጠቀሙ ደንበኞች ላይ ቆጣሪ ከማንሳት ጀምሮ ተገቢውን ህጋዊ ዕርምጃ የሚወስድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

(ምንጭ:- የአ/አ ውሀና ፍሳሽ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top