Connect with us

ግጭት ቀስቃሽ መገናኛ ብዙሃን ላይ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል የብሮድካስት ባለሥልጣን አስጠነቀቀ

ግጭት ቀስቃሽ መገናኛ ብዙሃን ላይ እስከዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል የብሮድካስት ባለሥልጣን አስጠነቀቀ
Photo: Facebook

ዜና

ግጭት ቀስቃሽ መገናኛ ብዙሃን ላይ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል የብሮድካስት ባለሥልጣን አስጠነቀቀ

ግጭት ቀስቃሽ መገናኛ ብዙሃን ላይ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል የብሮድካስት ባለሥልጣን አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የሕግ መስመር እየጣሱ ሁከትና ብጥብጥ በሚያስተጋቡ መገናኛ ብዙኃን ላይ እርምጃ አልወሰደም በሚል የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ወቅሰዋል፡፡

ባለሥልጣኑ የአገር ህልውና አደጋ ውስጥ ከመውደቁ በፊት አደብ እንዲያስገዛም የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል።

በቴሌቪዥንና ሬዲዮዎች ሥራ ክትትል 16 የሕግ ጥሰቶች እንደተገኙ በባለሥልጣኑ ሪፖርት ቢጠቀሰም፣ ጥሰቶችና ግድፈቶች እንዳልታረሙና የችግሩ ምንጭ የሆኑ መገናኛ ብዙኃን ላይም እርምጃ እንዳልተወሰደ እንደራሴዎቹ ኮንነዋል፡፡

ባለሥልጣን በበኩሉ ሚዛናዊነት የሚጎድላቸውንና ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ መረጃዎችን በማሰራጨት የተጠመዱ አሉ ላላቸው የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ማስጠንቀቂያ መስጠት እንደጀመረ አሳውቋል፡፡

በማስጠንቀቂው ቶሎ ካልተመለሱ እስከመዝጋት የሚደርሰው እርምጃ እንደሚከተል በደብዳቤ እንዲያውቁት እየተደረገ መሆኑም ለእንደራሴዎቹ ገልጿል፡፡

ለመገናኛ ብዙኃኑ የተሻለ ነፃነትና ትዕግስት እየተሰጠ ቢሆንም ጥቂት ተቋማት ነፃነታቸውን በአግባቡ እየተጠቀሙበት አይደለም ሲልም ባለሥልጣኑ ከሷል፡፡

(ምንጭ፡- አሐዱ ቴሌቪዥን)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top