Connect with us

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ወዳጅነት የበለጠ እንደሚጠናከር ገለፀች

ከኢትዮጵያ ጋር ኬንያ ያላት ወዳጅነት የበለጠ እንደሚጠናከር ገለፀች
Photo: Daily Nation

ዜና

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ወዳጅነት የበለጠ እንደሚጠናከር ገለፀች

የኬንያ መንግስት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ዘርፈ ብዙ የሽግግር ሂደት እንሚደግፍ አስታወቀ፡፡

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ማቻርያ ካማው በአገሪቱ ታዋቂ ከሆነው ሲቲዝን የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ኢትዮጵያ ሠፊ ታሪክ እና ድንቅ ባህል ያላት አገር እንደሆነች ጠቅሰዋል፡፡

አገሮች በተለያየ የታሪካቸው ሂደት በተመሳሳይ ሽግግር ውስጥ ያልፋሉ ያሉት ሚኒስተር ዴኤታው ኢትዮጵያም በተመሳሳይ ሂደት ላይ መሆኗን እና ለስኬቱ የኬንያ መንግስት ድጋፍ እንደማይለያት አረጋግጠዋል፡፡

በጋራ ድንበር አካባቢ ካሉ ህዝቦች ጋር የሚፈጠሩ አንዳንድ ችግሮች ከንግድ ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ገልፀው በሁለቱ አገሮች መሀከል ያለው ግንኙነት ፍፁም ጤነኛ ነው ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር ኬንያ ያላት ወዳጅነት የበለጠ እንደሚጠናከር የአገራቸው ፍላጐት መሆኑንም አምባሳደር ማቻሪያ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:- የኢፌዲሪ ኤምባሲ፣ ኬንያ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top