Connect with us

ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈጸም

ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈጸም
Photo: K140

ነፃ ሃሳብ

ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈጸም

ወጣቶች ወይንም ታዳጊዎች ለጋብቻ ከመድረሳቸው በፊት ምን ያህል የሚሆኑት ለግብረስጋ ግነኙነት ተጋላጭ ይሆናሉ የሚለውን የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች በተለያዩ የኦሮሚያ መስተዳድሮች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና በአዲግራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመ ለከቱትብ ክናጋራችሁ ወደድን፡፡ በዚህ እትም በአምቦ ዩኒቨርሲቲና በአዲግራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጥናት አድራጊዎቹ ያገኙትን መረጃ በጥቅሉ እናስነብባችሁዋለን፡፡

በአለም ላይ ያሉ ወጣቶች ቁጥር ወደ 1.8 ቢሊየን ማለትም የአለምን ሕዝብ ቁጥር 27% ያህል ሲሆኑ ከዚህም ወደ አራት አምስተኛው የሚሆኑት የሚገኙት በታዳጊ አገራት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በወጣቶች ላይ የሚታየው የስሜት እና የአካል እንዲሁም ስለወሲብ ያላቸው ፍላጎት ወይ ንም ስሜት ለውጥ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ለብዙዎች ወጣቶች በግልጽ ሊረዱት የማ ይችሉትን የህይወት አጋጣሚ ሊጋፈጡ የሚገደዱበት ሁኔታ ነው:: ለምሳሌም የመጀመሪ ያውን የወሲብ ግንኙነት የፈጸሙበትን ቀን፤ ጋብቻ፤ እርግዝና እና የወንድ ወይንም የሴት ጉዋደኛ ያፈሩበት ወቅት ስለሚሆን የህይወት ገጽታቸው ተቀይሮ የሚያገኙበት ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች በሚከሰቱበት ጊዜ በወጣቶቹ ዘንድ ከአሁን ቀደም ጭርሱንም ግንዛቤ ያልነበራቸው እና ትኩረት ያልተሰጣቸው የስነተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ይከሰታሉ፡፡ በአለም ዙሪያ ወጣቶች ከጋብቻ በፊት ወሲብ የመፈጸማቸው ጉዳይ በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመራና አሳሳቢ እየሆነ በመምጣት ላይ ነው፡፡ ለዚህም ነው የወጣቶች የወሲብ ድርጊት ውጤቱ ከፍተኛ የሆነ ውን የህብረተሰብ ጤና ትኩረት እንዲያገኝ አስፈላጊ የሚያደርገው፡፡ የወሲብ ድርጊት አንዱ የተፈጥሮ ፍላጎትና ድርጊ ቱም እንደፈላጊዎቹ ሁኔታ ቢወሰንም የማይቀር ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ ይሁን እንጂ መቼ፤ በየትኛው እድሜ ፤በምን ዝግጅት መፈጸም አለበት የሚለው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡

ወጣቶች ወይንም ታዳጊዎች አእምሮአቸው እና አካላቸው ገና ሳይበስል እድሜአቸው ለጋብቻ ሳይደርስ በስሜት ተነሳስተው የሚፈጽሙት ወሲባዊ ግንኙነት ምንም ጥንቃቄ የማይደረግለት ስለሆነ ሁልጊዜም ለአደጋ የመጋለጥን ሁኔታ ያሳያል፡፡

በልጅነት እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ ወሲብ መፈጸም፤
አልኮሆል እና የተለያዩ ሱስ አስያዥ እጾችን መጠቀም፤
ላልተፈለገ እርግዝና መጋለጥን፤
ጥንቃቄ የጎደለው ጽንስ ማቋረጥ፤
ኤች አይቪን ጨምሮ በግብረስጋ ግንኙነት ለሚተላለፍ በሽታ መጋለጥ፤
ምንም መሰረት የሌለው እና ቀጣይነት የሌለው ትዳርን መመስረት፤
በትናንሽ ወይንም በጉልበት ስራዎች ላይ መሰማራት፤
ትምህርትን መማርን ማቋረጥ…ወዘተ

ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች መሰል ችግሮች በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የገቡትም ይሁን በዩኒቨርሲቲዎች በመማር ላይ የሚገኙት ወጣቶች ከጋብቻ በፊት ወሲብ በመፈጸም ምክንያት የሚሆናቸው ነገር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ይህንን መረጃም አብረዋቸው ከሚማሩ ጉዋደኞቻቸው ጋር ይለዋወጡታል፡፡

ወሲባዊ ጤንነት ወሲብ ለሚፈጽሙ ሰዎች በጎ በሆነ መንገድ መቅረብንና የተፈጠሩ ችግሮች ቢኖሩ እንኩዋን በትክክል መረዳትን በተከተለ መንገድ የባለጉዳዩን ባህርይ እና ጤንነት ለማስተ ካከል ይረዳል፡፡ የወሲባው ጤንነት ችግሮች የሚባሉት በአለም ላይ በተለይም በአፍሪካ ወጣቶ ችን ለሞት፤ ለአካል ጉዳት፤እና ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጡ አስከፊ ድርጊቶች ናቸው::

በኢትዮጵያ ከወሲብ ጋር በተያያዘ የሚነሳው የጤና ችግር እድሜያቸው ትልቅ ከሆኑ እና ከወ ንዶች ጋር ሲነጻጸር በታዳጊዎችና በሴቶች ዙሪያ ከፍተኛ ነው ሊባል የሚችል ነው ጥናቱ እንደ ሚያስረዳው፡፡ በእርግጥ የጤናው ችግር እንደደረሰ ለመፍታት የሚወሰደው እርምጃ በጊዜው የሚኖረውን ደህንነት እንዲሁም በወደፊት ሕይወት ላይ የሚኖረውን ጤንነትና በተሟላ ጤን ነት የመቀጠል ሁኔታ ይወስነዋል፡፡

በልጅነት ወይንም ለጋብቻ ከመድረስ በፊት የሚፈጸም ወሲባዊ ግንኙነት ምንም ጥንቃቄ የማይ ደረግለት ከመሆኑ የተነሳ ከላይ እንደተገለጸው ላልተፈለገ እርግዝና ፤በድብቅ ለሚካሄዱ ጽንስ የማቋረጥ ተግባር እንዲሁም ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እና በወሲብ ግንኙነት ምክንያት ለሚተላለፉ የቫይረስ ሕመሞች ስለሚያጋልጥ ውጤቱ ከፍተኛ ሕመም እንዲሁም ሞት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ሴት ልጆች በተለይም ልጃገረዶች ገና በታዳጊነት እድሜያቸው እያሉ ልጅ ለመውለድ ስለሚገደዱ ተያይዞ ለሚከሰት የጤና ችግር ብሎም ሞት ይጋለጣሉ፡፡

በኢትዮጵያ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ የብዙ እናቶች ማለትም ካሉት የእናቶች ሞት ምክንያቶች 10 % ለሚሆነው ሞት ምክንያት ነው፡፡ ሁኔታው በአካል ላላደጉ ወይንም አቅም ለሌላቸው ልጆች ደግሞ ይበልጡኑ ከባድ ነው፡፡

የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚነስቴር እንዳወጣው መረጃ ወደ 70 % የሚሆኑ ሴቶች በትክክል ላልተፈጸመ ጽንስ ማቋረጥ ሕክምና ፈልገው ወደ ጤና ተቋማት የቀረቡ ሴቶች እድሜያቸው ከ24/አመት በታች ሲሆን ሁኔታውም በኢትዮጵያ ለእናቶች ሞት ምክንያት ከሚባሉት ሕመ ሞች መካከል ነው፡፡ በሁለቱም ትምህርት ተቋማት እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ታዳጊዎቹ ወሲብ መፈጸምን ሲጀምሩ ኮንዶም መጠቀምን ወይንም የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ተጠቃሚዎች አልነበ ሩም:: ይህ ደግሞ በቀጥታ የሚመለከተው ልጆቹን ብቻ ሳይሆን የወላጆችን የሕይወት ዘመን ልምድ ወይንም እውቀት እና ከልጆች ጋር ግልጽ የሆነ ውይይት ወይንም ግንኙነት አለመኖሩን ነው፡፡

ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት በኤችአይቪ አይድስ ቫይረስ በመያዝ ከፍተኛ ተጠቂ ከሚ ባሉት መካከል ሲሆኑ በአለም ላይ ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኝ 33.3 ሚሊዮን ሰዎች መካ ከል 22.5 ሚሊዮን የሚሆኑት የሚገኙበት ነው፡፡ ኤችአይቪ በአለም ላይ 3ኛው ወጣቶችን ለሞት የሚዳርግ ነው፡፡ በአፍሪካ ግን በአንደኛ ደረጃ ታዳጊዎችን የሚገድል ሲሆን እድሜያቸ ውም ከ15-29 የሚሆኑ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ በ2011 በ (EDHS), በተደረገው ዳሰሳ እንደተረጋገ ጠው 1.5 % የሚሆኑ እድሜያቸው ከ15-19 አመት የሚደርስ ታዳጊ ወጣቶች በቫይረሱ መያዛቸው ንና በዚሁ እድሜ ያሉ ብዙ ሴቶችም ቫይረሱ በደማቸው መኖር ያለመኖሩን ለማረጋገጥ ከወ ንዶች በበለጠ ወደ ሕክምና ተቋማት መሄዳቸውን መረጃው ያሳያል:: ለዚህም እንደዋና ምክ ንያት ከተጠቀሱት ነገሮች አንዱ እድሜያቸው ለጋብቻ ሳይደርስ በልጅነት ወሲብ መፈጸማቸው እና በአንድ ሳይወሰኑም ድርጊቱን መፈጸማቸው ነው፡፡

ታዳጊዎች ገና በልጅነት እድሜያቸው የግብረስጋ ግንኙነት እንዲፈጽሙ የሚያበረታቱዋቸው እና ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩላቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በትምህርት ምክንያት ከወላጆች እርቀው አካባቢ ቀይረው መሄዳቸው ይገኝበታል፡፡
ታዳጊዎች ብሔራዊ ፈተናቸውን አልፈው ከአካባቢያቸው እራቅ ወደ አለ ዩኒቨርሲቲ ሲመደቡ ውሎ አዳራቸው በአብዛኛው በእድሜ ተመሳሳይ ከሆኑ ወጣቶች ጋር ነው፡፡

ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ውጪ በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በአንድ ላይ መገናኘታቸው የልምድ ልውውጥን ለማድረግ ችግርን ለመጋራት አንዱ በአንዱ የመሳብን ባጠቃላይም በጎውንም ይሁን ክፉውን ልምድ ለመቀባበል መንገዶች ምቹ ይሆንላቸዋል፡፡

በተለይም ቀደም ሲል በከፍተኛ ቁጥ ጥር ስር ሆነው ትምህርታቸውን ይማሩ የነበሩ ከሆኑ በእንደዚህ ያለው ወቅት ከወላጅ የቅርብ እይታ ስለሚርቁ ነጻነት ያገኙ ስለሚመስላቸው በሚያዩዋቸው እንግዳ ባህርያት መመሰጥ ሊታ ይባቸው ይችላል፡፡
ስለዚህም ደካማ የሆነ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ ገጽታ፤ የአካባቢው እንግዳነት፤ጎ ጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፤ ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያን አለመጠቀም የመሳሰሉት ነገሮች በስፋት ይስተዋ ልባቸዋል፡፡

ምንጭ:-  አዲስ አድማስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top