Connect with us

ባለሥልጣኑ በአዲስአበባ ከተማ የመጠጥ ውሃ በፈረቃ ማደል መጀመሩን አመነ

ባለሥልጣኑ በአዲስአበባ ከተማ የመጠጥ ውሃ በፈረቃ ማደል መጀመሩን አመነ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ባለሥልጣኑ በአዲስአበባ ከተማ የመጠጥ ውሃ በፈረቃ ማደል መጀመሩን አመነ

ባለሥልጣኑ በአዲስአበባ ከተማ የመጠጥ ውሃ በፈረቃ ማደል መጀመሩን አመነ

– የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ተጨማሪ ችግር ሆኖብኛል ብሏል፣

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን  ምርቶ የሚያሰራጨው የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ከተጠቃሚው ፍላጎት ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ ፍትሃዊ የውሃ ክፍፍል እንዲኖር ለማድረግ በፈረቃ የማዳረስ ተግባሩን እየተወጣ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

የውኃ ፈረቃውን በማስመልከትም ስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ፕሮግራም አውጥተው በየወረዳው እንዲለጠፍ በማድረግ ለባለስልጣኑን ደንበኞች የማሳወቅ ስራ ይሰራሉ፡፡

ይሁን እንጂ፣ በፈረቃቸው መሠረት በሳምንት 2 ቀን ውኃ ያገኙ የነበሩ ልደታ ፍ/ቤት፣ ባልቻ ሆስፒታል፣ መልሶ ማልማት ልደታ ኮንዶሚኒየም፣ አብነት ቀበሌ 36 እና 37 በመብራት መጥፋት ምክንያት ውኃ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ችግሩ እስኪፈታ ባለስልጣኑ ውኃ በቦቴ በማዳረስ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ ባህታ አካባቢ 200 ሚ.ሚ መጠን ባለው የከባድ መስመር ላይ በደረሰ ስብራት ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ 4 ኪሎ፣ ወ.ወ.ክ.ማ፣ ኢህአዴግ ጽ/ቤት፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ቀበሌ 18 እና ቤተ መንግስት አካባቢ የውኃ እጥረት አጋጥሟል፡፡

የደረሰው ስብራት ተጠግኖ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ወደ መስመሩ የሚገባው ውሃ እስኪከማች አንድ ቀን የሚያሰፈልግ መሆኑን የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የውኃ ስርጭት ኬዝ ማናጀር አቶ ሄኖክ ኒቆዲሞስ ገልፀዋል፡፡

(ምንጭ፡-የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top