Connect with us

ፌስቡክ በአፍሪካ ፖለቲካ ጣልቃ እየገቡ ያሉ የሩስያ አካውንቶች ማገዱ ተሰማ

ፌስቡክ በአፍሪካ ፖለቲካ ጣልቃ እየገቡ ያሉ የሩስያ አካውንቶች ማገዱ ተሰማ
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ፌስቡክ በአፍሪካ ፖለቲካ ጣልቃ እየገቡ ያሉ የሩስያ አካውንቶች ማገዱ ተሰማ

የፌስቡክ ካምፓኒ እንደገለፀው በሩስያ ባለቤትነት የሚንቀሳቀሱ ሶስት ኔትውርኮች የታገዱት ስምንት የአፍሪካ ሃገራት የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ በመግባታቸው ነው ተብሏል፡፡

ካምፓኒው ክልከላው ያስፈለገው ሩስያ በአፍሪካ ሃገራት ላይ የራሷን ፍላጎት የሚያንፀባርቁ ጉዳዮች የሚሰራጭበት ገፆች በመሆናቸውን ገልጾ፤ ጣልቃ ከገባችባቸው አገራት መካከል በሞዛምቢክ እና ማዳጋስካር ምርጫ ሂደት መግባቷም አስታውሷል፡፡

ጣልቃ የመግባት ዘመቻው ኢላማ ካደረጋቸው የአፍሪካ አገራት መካከል ማዳጋስካር፣ ሞዛምቢክ፤ ኮነጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፤ ኮዲቫር፣ ካሜሮን፣ ሱዳን እና ሊብያ ሲሆኑ ከ200 በላይ የሃሰት አካውንቶች በመክፈት በአፍሪካ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን አፍርተዋልም ነው የተባለው።

በገፁ ላይ አብዛኛው ጊዜ አለም አቀፍና ሃገራዊ የፖለቲካ ዜናዎችና የሩስያ ጉዳዮች የሚነሱበት መሆኑን ነው የፌስቡክ ሳይበር ደህንነት ሃላፊ ናትናኤል ገለይቸር የገለፁት።

ምንጭ፡-አልጀዚራ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top