Connect with us

የመርሳት ችግርን የሚቀንስ መድሃኒት ይፋ ሆነ

የመርሳት ችግርን የሚቀንስ መድሃኒት ይፋ ሆነ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የመርሳት ችግርን የሚቀንስ መድሃኒት ይፋ ሆነ

የአሜሪካ የመድሃኒት ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመርሳት በሽታን የሚቀንስ መድሃኒት ማዘጋጁቱን ይፋ አደረገ፡፡

ኩባያው ይህንን መድሃኒት በአሁን ወቅት ለገበያ ለማቅረብ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የገለፀ ሲሆን ለዚህ ከአሜሪካ ተቆጣጣሪ አካል ማረጋገጫ እየጠበቀ ይገኛል፡፡

በአሁን ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ የመርሳት በሽታን ለመቀነስ የሚያስችል መድሃኒት የማይገኝ ሲሆን ያለው ቢሆንም በሽታው በምልክት ደረጃ ላይ እያለ ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡

አዱካኑማብ የሚል ስያሜን ያገኘው ይህ መድሃኒት አጠቃላይ የወረቀተ ስራ በፈረንጆቹ 2020 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድሃኒቱ በቀጣይ አንድና ሁለት አመት ውስጥ ማረጋገጫውን ያገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ስኬታማ ከሆነም ኩባንያው በምርምሩ ወቅት ለተመዘገቡ ህሙማን ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

ከፍተኛ መጠን ያለው የመርሳት መድሃኒት መውሰድ በተለይ በበሽታው የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህሙማን የማስታወስ ችሎታቸውን እና የየዕለት የህይወት ክህሎታቸውን እንዳይቀንሳ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top