Connect with us

በ30ዎቹ የዕድሜ ላይ የሚከሰት የደም ግፊት ለአዕምሮ ጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል -ጥናት

30ዎቹ የዕድሜ ላይ የሚከሰት የደም ግፊት ለአዕምሮ ጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል -ጥናት
BBC

ጤና

በ30ዎቹ የዕድሜ ላይ የሚከሰት የደም ግፊት ለአዕምሮ ጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል -ጥናት

በ30 ዎቹ የዕድሜ ክልል አጋማሽ ላይ የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት ለአዕምሮ ጤና ችግር ሊያጋልጥ የሚችል መሆኑን አንድ ጥናት አመላከተ።

ላንሴት ኒውሮሎጂ በተባለው መጽሔት ላይ የወጣው አዲስ ጥናት እንዳመላከተው በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል አጋማሽ ላይ የሚከሰት የደም ግፊት በኋለኛው ዕድሜያችን ላይ አዕምሯችን ለከፍተኛ የጤና ችግር ይዳርጋል።

ጥናቱ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1946 በተወለዱ 500 ሰዎች ላይ የተካሄደው መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ጥናቱ የተካሄደበት ዋና አለማም ከፍተኛ የደም ግፊት በየትኛው የእድሜ ክልል ላይ ቢከሰት ወደ ፊት የአዕምሮ ጤናን ለጉዳት ይዳርጋል የሚለውን ለመለየት መሆኑ ተገልጿል።

ጥናቱን ያካሄዱት ተመራማሪዎች ለናሙና በመረጧቸው የጥናቱ ተሳታፊዎችን ላይ እንዳረጋገጡት በተጠቀሰው ዕድሜ ክልል ላይ በከፍተኛ ደም ግፊት የተያዙ ሰዎች በኋለኛው ዕድሜያቸው ወቅት ለከፍተኛ የአዕምሮ ጤና ችግር ተዳርገዋል።

በ30 ዎቹ እድሜ ክልል አጋመሽ ላይ የሚከሰተው የደም ግፊትም በአዕምሮ ላይ ያሉ የደም ቧንቧዎችንና ነርቮችን በማዳከም የአዕምሮ ጤናን ችግር ላይ የሚጥል መሆኑ ተጠቁሟል።

ስለሆነም በ30 ዎቹ እድሜ ክልል አጋማሽ ላይ የሚገኙ ሰዎች የሰውነታቸውን የደም ግፊት መጠን ተለክቶ በማወቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው በጥናቱ ተመላክቷል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top