በጭንቅላት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ተከትሎ የሚከሰት ሞትን ሊቀንስ ይችላል የተባለ መድሃኒት መገኘቱን የብሪታኒያ ዶክተሮች አስታውቀዋል።
እንደ ዶክተሮቹ ገለፃ መድሃኒቱ በጭንቅላት ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ በውስጥ የሚከሰተውን የደም መፍሰስ ማስቆም የሚችል መሆኑን ነው የገለፁት።
“ትራኔግዛሚክ አሲድ (Tranexamic acid)” የሚል መጠሪያ ያለው መድሃኒቱ በጭንቅላታችን ውስጥ አሊያም በአእምሯችን ዙሪያ የሚከሰቱ የደም መፍሰሶችን በቀላሉ ሊያስቆም የሚችለው መድሃኒት መጠሪያ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በላንሴት መጽሄት ላይ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በመድሃኒቱ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥናት የተካሄደ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይም በጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው 12 ሺህ ሰዎች መሳተፋቸው ተነግሯል።
በዚህም በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት ለደረሰበት ሰው በአስቸኳይ መድሃኒቱን እንዲወስድ በማድረግ ብቻ የሚከሰት ሞትን ማስቆም እንደሚቻል ጥናቱ አመላክቷል።
መድሃኒቱ አደጋውን ሙሉ በሙሉ አያድንም ነገር ግን በጉዳት ውቅት በጭንቅላት የውስጠኛው ክፍል ላይ በትንሹ ጀምሮ የከፋ ጉዳት የሚያደርሰውን ወደ ውስጥ መድማት ማቆም ይችላል ብሏል ጥናቱ።
ትራኔግዛሚክ አሲድ በአሁኑ ወቅትም በደረት አሊያም በሆዳችን ውስጥ የሚከሰት መድማትን እንዲሁም በእናቶች ከወሊድ በኋላ የሚያጋጥም የደም መፍሰስን ለማስቆም ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኝ መድሃኒት መሆኑም ተመላክቷል።
መድሃኒቱ በተመጣጣኝ ዋጋ በገበያ ላይ የሚገኝ እንደመሆኑም በየዓመቱ በጭንቅላት ላይ በሚደርስ ጉዳት ሳቢያ በሺህዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሞትን ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
ምንጭ፦ www.bbc.com
–