Connect with us

ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር ከንቲባ ታከለ ኡማ

Photo: Facebook

ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር ከንቲባ ታከለ ኡማ

Quis autem vel eum iure reprehenderit qui in ea voluptate velit esse quam nihil molestiae consequatur.

ይኸቺን ማስተወሻ ለመጻፍ ያስገደደኝ ቀልድ መሰል መግለጫ መስማቴ ነው፡፡ የኮንደሚኒየም ዕጣ ወጥቶላቸው ከዘጠኝ ወራት በላይ ቤታቸው መግባት ያልቻሉ እና ከዛሬ ነገ ቤቱን ያስረክቡን ይሆን በሚል ተስፋ የተቀመጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ባሉበት በዚህ ወቅት ኩምክና ተጀምሮአል፡፡ የአስተዳደሩ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ዳምጠው (ኢንጂነር) በያዝነው ዓመት 500 ሺ ቤቶች ግንባታ በተለያዩ አማራጮች ለመጀመር ዝግጅት ስለማጠናቀቁ ተናግረዋል፡፡

አንደኛ ነገር ስለአዲስ ግንባታ ለማውራት በቅድሚያ ፍትሐዊ የሆነ የመኖሪያ ቤቶች ስርጭት ተከናውኗል ወይ የሚለውን መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ከዘጠኝ ወራት በፊት የወጣው የኮንደሚኒየም ዕጣ አስካሁን ዕድለኞች መረከብ አለመቻላቸው እንደአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡

ሌላው የኮንደሚኒየም ግንባታ ፕሮግራም ከጀመረበት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ባሉት 16 ዓመታት በመጀመሪያው ዙር ለተመዘገቡ ከ350 ሺ በላይ ዜጎች ቤት መገንባትና ማዳረስ አልተቻለም፡፡ በአስከዛሬው አካሄድ በዓመት 50 ሺ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል አቅም አልተፈጠረም፡፡ ዘንድሮ የምርጫ ዓመት ነውና ብድግ ተብሎ በአንድ ዓመት 500 ሺ ቤት ግንባታ እንጀምራለን የሚል ፉከራና ሽለላ ውስጥ መገባቱ ያው ለምርጫ አስቀድሞ የሚሰጥ ቀብድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡

ክብር ከንቲባ

በተለይ በኮንደሚኒየም ጉዳይ የአዲስአበባ ሕዝብ በእርስዎ ላይ ያለውን መተማመን ካነሳ ውሎ አድሯል፡፡ እንደሚያስታውሱት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም ቤቶች) ዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

እርስዎም በዚሁ ሥነሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በተለይ ለቤቶች ግንባታ ሲባል ከእርሻ ቦታቸው የለቀቁ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች ያለ ዕጣ ቤት እንዲሰጣቸው መወሰኑን ይፋ አድርገዋል። እርግጥ ነው፤ አርሶአደሮች በቂ ካሳ ካላገኙ መካስ እንዳለባቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ግን የሚካሱት በሕዝብ ገንዘብ የተሰራ ኮንደሚኒየም እያነሱ በማደል አልነበረም፡፡ መንግሥት ካሳ ያንሳል ካለ ተገቢውን ስሌት አድርጎ ለሁሉም ባለው ሐብት ልክ የሚገባውን ሊሰጥ ይችላል፡፡ በጅምላ ማደል ብሎ ነገር ስጦታ እንጂ ካሳ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ የጹሑፌ ትኩረት ይህ ባለመሆኑ ጉዳዩን እዘለዋለሁ፡፡

የጹሑፌ ትኩረት ስለዘንድሮ አዲስ ግንባታ ከማውራት አስቀድሞ በስመ ቄሮ ዱላ ይዘው አደባባይ የወጡ ጎረምሶች በዛቻ ያስቆሙትን የኮየ ፈጪ ኮንደሚኒየም ጨምሮ በመጨረሻ ዙር ዕድለኛ ለሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ቤታቸውን በክብር የሚያስረክቡት መቼ ነው የሚለውን ቢመልሱልኝ እንደውለታ እቆጥረዋለሁ፡፡ ከዚያም ስለቀጣዩ መነጋገር ይቻላል፡፡ ክቡርነትዎ ያጡትን የአዲስአበባ ሕዝብ አመኔታ ሊመልሱ የሚችሉትም የነዋሪውን ትክክለኛ ጥያቄ ፈጥነው በመመለስ ብቻ መሆኑን ላስታውስዎ እወዳለሁ፡፡

መልካሙን ሁሉ እመኝልዎታለሁ፡፡

(ጫሊ በላይነህ ነኝ)

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top