Connect with us

ኢትዮ ቴሌኮም የ47 የSMS አጫጭር መረጃ አቅራቢ ድርጅቶችን ፍቃድ አቋረጠ

EthioTelecom Logo
Photo: EthioTelecom

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮ ቴሌኮም የ47 የSMS አጫጭር መረጃ አቅራቢ ድርጅቶችን ፍቃድ አቋረጠ

ደንበኞች ከፍቃዳቸው ውጭ አጫጭር መረጃዎች እንደሚላክላቸው እና አገልግሎቱን ማቋረጥ ሲፈልጉም ማቋረጥ አለመቻላቸዉ

የቴሌኮም መሰረት ልማትን በመጠቀም የስፖርት፣ የመዝናኛ፣ ትምህርታዊ እና ሌሎች ይዘት ያላቸውን መረጃዎችን ለሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር እያቀረበ የሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም የ47ቱን አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ወ/ሮ ጨረር አክሊሉ እንደገለፁት አግልግሎቱ የተቋረጠው ደንበኞች ከፍቃዳቸው ውጭ አጫጭር መረጃዎች እንደሚላክላቸው እና አገልግሎቱን ማቋረጥ ሲፈልጉም ማቋረጥ አለመቻላቸዉን በተደጋጋሚ ለኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታ በመቅቡ ነው ብለዋል፡፡

ደንበኞች ያነሱትን የቴክኒክና የአስተዳደር ችግሮች እየፈታ መምጣቱን የገለፁት ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተሯ አሁን ወደ አዲስ ስርዓት መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ደንበኞች በፈለጉ ጊዜ አገልግሎቱን ማቆም እንደሚችሉ ኩባንያዎቹ አገልግሎቱን ለሚፈልግ የቴሌ ደንበኞች ብቻ እንዲልኩ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበርም ገልፀዋል፡፡

እርምጃው የተወሰደባቸው ድርጅቶች የቴሌ ደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማደረግ የአጫጭር መረጃ ለማቅብ በተቀመተው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለመመዝገብ ባልመጡት ላይ መሆኑንም ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው፡፡

በአሁን ሰዓት 310 የአጫጭር የመረጃና የማስታወቂያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ይገኛሉ፡:

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top