Connect with us

All posts tagged "የአዲስአበባ ፖሊስ"

  • የአዲስአበባ ፖሊስ ሕዝቡ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ መከረ የአዲስአበባ ፖሊስ ሕዝቡ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ መከረ

    ዜና

    የአዲስአበባ ፖሊስ ሕዝቡ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ መከረ

    By March 22, 2021

    የአዲስአበባ ፖሊስ ሕዝቡ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን እንዲጠብቅ መከረ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የህበረተሰቡን በጋራ አብሮ የመኖር እሴቶችን የሚያናጉ ሀሠተኛ መረጃዎች እየተሠራጨ ነው። የሀገራችን ሠላም አንቅልፍ የሚነሳቸው ፀረ ሠላም ሀይሎች ብሄርን ከብሄር ለመጋጨት በአዲስ አበባ ብሄርን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ሊፈፀም ነው የሚል ሀሠተኛ መረጃ እያሰራጩ ይገኛል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተላለፈው ሃሰተኛ መረጃ የአዲስ አበባ ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ ነገር ግን የፖሊስ መታወቂያ የሌላቸው ጸጉረ ልውጥ ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ ብሔር እና ሃይማኖት በመመዝገብ ላይ ናቸው። እነዚህ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጸጉረ ልውጦች በተወሰኑ ብሔሮችን እና ሃይማኖቶችን ለይተው ለማጥቃት እየተንቃሰቀሱ ነወ የሚሉ እና በነዋሪው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ሃሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ  መሆኑን ኮሚሽኑ ደርሶበታል፡፡ በፀረ ሠላም ሀይሎች አየተሠራጨ ያለው ሀሠተኛ መረጃ ህብረተሰብን ለማደናገጥ እና ለማሸበር እንዲሁም ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት እንዲሁም በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ስጋት ለመፍጠር ሆን ተብሎ ታቅዶና ታስቦ እየተሰራጫ ያለ ሀሰተኛ መረጃ ነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ በስፋት የተሰራጨ በመሆኑ በሰዎች የእለት ከእለት እንቅስቃሴም ላይ አሉታዊ የስነ ልቦና ጫና እያሳደረ ነው፡፡ በመሆኑ ከተገቢው አካል መረጃ ሳይጠይቁና ሳያረጋግጡ ሀሰተኛ መረጃ የሚሰራጩ እንዲሁም መረጃን ተቀብለው የሚያናፈውሱ አካላት ከህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቦ ከተማዋ ላይ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ ምርመራ በማጣራት በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራን እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት መደበኛ ተግባራቸውን በአግባቡ እየተወጡ እንደሚገኙ እና ነዋሪውም የእለት ተእለት ተግባሩን እያከናወነ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡ ህብረተሰቡ በፀረ- ሰላም ኃይሎች የሚናፈሱ መረጃዎች ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን በመረዳት ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮ እንዲቀጥል እና የከተማዋን ፀጥታ አስመልክቶ የሚተላለፉ መረጃዎችን በተመለከተ ከተገቢው አካል የሚለቀቁ መረጃዎች ሊከታተል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ህብረተሰቡ  ለጸጥታ ስራ እያበረከተ የለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪውን እያቀረበ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት ሆነ አጠራጣሪ ጉዳይ ሲገጥመው ጥቆማ ለመስጠት ነፃ የስልክ መስመር 991ወይም 01-11-11-01-11መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል ።(አ/አ ፖሊስ...

More Posts
To Top