Connect with us

All posts tagged "አስቴር በዳኔ"

  • ‹አማርኛን በዓለም አቀፍ በተሸጠው እንግሊዘኛ ቋንቋ ደረጃ ማሰብ አለብን›› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹አማርኛን በዓለም አቀፍ በተሸጠው እንግሊዘኛ ቋንቋ ደረጃ ማሰብ አለብን›› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

    ነፃ ሃሳብ

    ‹አማርኛን በዓለም አቀፍ በተሸጠው እንግሊዘኛ ቋንቋ ደረጃ ማሰብ አለብን›› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

    By December 10, 2020

    ‹አማርኛን በዓለም አቀፍ  በተሸጠው እንግሊዘኛ ቋንቋ ደረጃ ማሰብ አለብን›› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹ ሀሳብን በነጻነት መግለፅ ድንጋይ ከመወርወር ያድናል››  አርቲስት አስቴር በዳኔ ኢትዮጵያዊነትን ደጋግማ ትጠራለች፣ ስለ ኢትዮጵያ ትናገራለች፣ ያመነችበትን እውነት በድፈረት ትናገራለች፣ ከኢትዮጵያዊነት ልክ የሚወርድን በድፍረት ትገስጻለች – አርቲስት አስቴር በዳኔ፡፡ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በአዲስ አበባ ስቱዲዬ የቀጥታ የዜና ስርጭት በማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ የተገኘችው አርቲስቷ ሀሳቧን አጋርታለች፡፡ ‹‹ ሀሳብን በነጻነት መግለፅ ድንጋይ ከመወርወር ያድናል፡፡ ሰው እሰማለሁ፣ አዳምጣለሁ ሀገሬ ላይ ድምፅ አለኝ፣ ሀሳቤን ያለመሸማቀቅ እገልፀላሁ የሚል ትልውድ ስንፈጥር ስለማይታፈን ወደ ድንጋይ ውርዎራ አይሄድም›› ነው ያለችው፡፡ ወደ ድንጋይ ውርወራና ወደ አመፅ የሚሄደው ተደማጭ አይደለሁም ሲል መሆኑንም ተናግራለች፡፡ የአማራ ብዘኃን መገኛኛ ድርጅትን ስትመለከት ነጻነቱ እንደሚያስገርማት የተናረችው አስቴር በዳኔ የአንድን ብሔር ስም ይዛችሁ ኢትዮጵያዊነትን ለማጉላት የምታደርጉትን ሥራ እመለከታለሁም ብላለች፡፡  መገናኛ ብዙኃኑ ኪነጥበብን በመጠቀምና እሴት በመጨመር ትልቅ ሥራ መሥራት እንደሚችልም ተናግራለች፡፡ ከአጥር በመውጣት ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ እንድትታይ የማድረግ ውለታ መዋል እንደሚገባውም አርቲስቷ ገልጻለች፡፡ ብዙ ሕዝብ የሚናገረውን ቋንቋ ማወቅ ኑሮ ያቀላል ያለችው አርቲስቷ የኢትዮጵያን ባንዲራ የጠንቋይ ነው  የሚሉትም  የሚፅፉት በሚጠሉት ቋንቋ ነው፤ ስምና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠፉት ሁሉ በሚጠሉት ቋንቋ መጻሕፍ እየጻፉ ነው የሚሸጡት ፤   የሚከበረውን ማክበር፣ ሊገሰፅ የሚገባውን ነገር በመገሰፅ ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ ለመስራት ጥረት ባደረጋችሁ ቁጥር ሁሉም የእኛ ናቸው ይላችኋል ነው ያለችው፡፡ ሁለገቡ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹ መነሻችሁ መድረሻችሁ እንዳይሆን አደራ እላለሁ›› ብለዋል፡፡ የአማራ  ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መነሻው ክልሉ ሊሆን ይችላል መዳረሻው ግን ዓለም መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡ ዓለም በትኩረት የሚያያቸው  እግር ኳስ ውድድሮች  መነሻቸው መንደር መሆኑን ያመላቱት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ዛሬ ላይ ግን ዓለም ያውቃቸዋል ነው ያሉት፡፡ ከመንደር የተነሳ ቡድን ለዓለም ሲተርፍ ከክልል የተነሳ ሚዲያ ለዓለም የማይተርፍበት ምክንያት የለምም ብለዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ጋር ትብብር ከዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር ደግሞ ፉክክር ያስፈልጋችኋል ያሉት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ማደግ የሚቻለው በትብብርና በፉክክር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ሚዲያው ዓለም በሙሉ የሚነጋገርበት ሚዲያ መሆን እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ከዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር በመፎካከር የተሻለ ተደማጭና ተመራጭ መሆን አለበትም ብለዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካከሪ ሲሆን ቋንቋውንና ባሕሉን መሸጥ እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡ ‹‹በቋንቋና በባሕል መኩራት ጥሩ ነው ፤ በአጥራችን ውስጥ ብቻ ካስቀመጥነው ግን መኩሪያ አይሆንም፤ …..አማርኛን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሸጠው እንግሊዘኛ ቋንቋ ደረጃ ማሰብ ይገባል፡፡ ›› ባሕላችንና ቋንቋችን ሌላው ሲለብሰው፣ ሲናገረውና በቤቱ ውስጥ ሲያደርገው ነው መኩራትም ብለዋል፡፡ ለራስ ብቻ መናገርና በራሱ አካባቢ ብቻ አጥሮ ማስቀመጥ ማሳደግ ሳይሆን መግደል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በዓለም ላይ ተመራጭና ተወዳደሪ መሆን የሚቻለው በሚዲያ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ የሰው ልጅ በሕሊናው የደረሰበትን ነው በአካል የሚደርስበት ሲሉም መስፋትና ማደግ እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ ሥራዎቻችን ለነገም ጭምር መሆን መቻል አለባቸው ነው ያሉት፡፡ ኢትዮጵያን አንድ የሚያደርጋት መተባበር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡(አብመድ)  

More Posts
To Top