Connect with us

ወርቅ ቢነጥቁት ዳቦ ጋግሮ ለማብላት የማይሳሳ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት

ወርቅ ቢነጥቁት ዳቦ ጋግሮ ለማብላት የማይሳሳ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት፤
Photo: Social Media | ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ

ኢኮኖሚ

ወርቅ ቢነጥቁት ዳቦ ጋግሮ ለማብላት የማይሳሳ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት

ወርቅ ቢነጥቁት ዳቦ ጋግሮ ለማብላት የማይሳሳ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት፤
ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ እናመሰግናለን፡፡
******
ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ 

እንደ ሼህ መሐመድ ስሙ ያልተብጠለጠለ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት የለም፡፡ ነብይ በሀገሩ አይከበርም እንዲል መጽሐፉ በአውሮፓ ስማቸው የገነነው ኢትዮጵያዊ በሀገራቸው ሰርቶ ማግኘት ባልተለመደበት ከባድ ምዕራፍ ሀገሬን ብለው መጡ፡፡

ሜድሮክ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ትልቁን የስራ እድል የፈጠረና ግዙፍ ኢንቨትመንትን በኢትዮጵያ ምድር ቀድሞ የገባ የግል ዘርፍ ነው፡፡ በተሰማራባቸው ዘርፎች ሁሉ በሌላ ባለሀብት ያልተደገሙ ግዙፍ ልማቶችን እውን አድርጓል፡፡

ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚነጠሉ ሰው አለመሆናቸውን የግብጽ ጋዜጦች በታሰሩበት ወቅት ባወጡት ዘገባ ተገንዝበናል፡፡ ሰውዬውን ከእኛ ይልቅ ለእኛ ስላላቸው ፋይዳ ሌሎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ “የህዳሴው ግድብ የዶላር ምንጭ ወህኒ ወረዱ” የሚለው ዘገባ ይሄንን ይመሰክራል፡፡

ክቡር ዶክተር ሼህ መሐመድ አንድ ግለሰብ አይደሉም፡፡ አንዲት ከተማን ባለስታዲየም ያደረገ ባለሃብት ማን ነው? እዚህ ሀገር ሰርቋል የሚባለውና ዘርፏል በሚል ስሙ የሚነሳው ባለሃብት ብዙ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ዘረፈ ያልተባለ ባለሃብት በሌለበት ሀገር ሼሁ ዘርፈዋል መባሉ አይገርምም፡፡ ግን ዘርፎም ሰርቶም ከመንግስት በላይ እንደ እሳቸው ማን ሰራ?

ሚሌኒየም አዳራሽ ለጊዜው ብለው ሰርተውት ዛሬም ድረስ የሀገር ዐይን የሚባል የስብሰባ አዳራሽ ሆኖ እየኖረ ነው፡፡ አልፎም በዚህ ጨለማ ወቅት ሆስፒታል ለመሆን በቅቷል፡፡ እርሻውም ኢንዱስትሪውም ሰውዬው ሲይዙት ይገዝፋል፡፡ እስቲ ደርባ ሲሚኒቶን እናስበው ያስመረቁት ዕለት የናረ የሲሚኒቶ ዋጋ መሬት ያወረዱ ሰው እኮ ናቸው፡፡

ግብር ከፋዩ ወርቅ ዘርፈዋል ተብለው የወርቅ ማዕድናቸውን ቢነጠቁም አኩርፈው ፊታቸውን አላዞሩም፡፡ ለኮሮናው ወረርሺኝ ፈጥነው በመድረስ የለገሱት የሀገሩ ባለሃብት ሁሉ ከለገሰው ድምር ያነሰ ነው፡፡

ሰውዬው ወርቅ ሲነጥቋቸው ዳቦ ጋግሬ ወገኔን ለማብላት እንቅፋት ሆነብኝ ሳይሉ የችግር ቀን ደራሽ ሆነዋል፡፡ የለውጥ ሃይሉ ግዙፍ ፕሮጀክት ሀገር በጥሪታቸው ከቀየሩት ኢትዮጵያዊ ባለሃብት ኪስ ማምለጥ አልቻለም፡፡ ለዚህ ነው ለሼሁ ረዥም እድሜ የምንመኘው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top