Connect with us

ወርሃ መጋቢት ሲዘክር ፤ ታላቁ ትንቅንቅ!

ወርሃ መጋቢት ሲዘክር ፤ ታላቁ ትንቅንቅ!
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ወርሃ መጋቢት ሲዘክር ፤ ታላቁ ትንቅንቅ!

አሮጌው ስርዓት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነበር፡፡ የደከሙት እና መንገጫገጭ የሚታይበት የስርዓቱ የቁጥጥር እና ክትትል ስርዓት ለከፍተኛ ጥቃት መጋለጡን በማመን ብዙ የፊት መስመር አመራር ላይ ከፍተኛ ስጋት አንጃቧል፡፡ በመላው ሃገሪቱ ራምፓንት የሆነ ተቃውሞ እንደተቀጣጠለ ነው፡፡ የመንግስት የእዝ ሰንሰለት በእጅጉ ላልቶ በጥቂት ታማኞች ላይ ብቻ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ለዚህ እንደ መፍትሄ የተወሰደ አንድ ሰው ነበር! ሽፈራው ሽጉጤ! ከወራት በፊት በመስከረም አካባቢ የከሸፈው ተሃድሶ የሚባል አሮጌውን ስርዓት የማስቀጠል ሙከራ በሁሉም ብሄራዊ ድርጅቶች እንደቀጠለ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የተመረጠው አካሄድ የተሃድሶ ግምገማው ለሌሎች ብሄራዊ ድርጅቶችም ክፍት እንዲሆን በማድረግ አንዱ ብሄራዊ ድርጅት በሌላው ብሄራዊ ድርጅት ስብሰባ ላይ ተወካዮችን እንዲልክ ማድረግ ነበር፡፡ በትግራይ ሰማዕታት አዳራሽ በተደረገው የህወሓት ግምገማ ላይ ከደኢህዴን የድርጅቱ ም/ሊቀመንበርና የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የነበሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዲወከሉ ተደርጓል፡፡

በግምገማው አንድ እንኳን ሰው በሌብነት መጠቆም ባልቻለበት ፤ የዐየር ወለድ ግምገማ ሂደት(በካድሬ ቋንቋ እንደ አየር ወለድ እየተከረባበትክ የችግር መዐት አውርተህ ግን አንድም ሰው ላይ ሌባ ነው ወይም ችግር አለበትብለህ መውጣት ሳትችል ነው) SAME OLD BORING EPRDF STYLE በዚህ ግምገማ ማጠቃለያ ላይ በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የተጋባዥ እንግዶች አስተያየት መስጫ ወቅት ደረሰ፡፡ አቶ ሽፈራው ከብዙ አስደማሚ አሞጋሽ ተናጋሪች በኋላ እድሉ ደረሳቸው፡፡

የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው የመሳሰሉትን የአድናቆት ጎርፍ ካዘነቡ በኋላ” በእርግጠኝነት ነው የምነግራችሁ! በመላ ሃገሪቱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሃይሎች ቢሸነፉ እንኳን፤ ትግራይ የአብዮቱ የመጨረሻ ምሽግ (the last line of defense) ትሆናለች፡፡ እኛም ለትግሉ አብረናችሁ እቀላቀላለን! ”

በዚህ ንግግር አዳራሹ ውስጥ የማያቋርጥ ጭብጨባ አስተጋባ! እልልታው ቀለጠ! ከያቅጣጫው የነበሩ አይኖች ሁሉ ወደ ሽፈራው አማተሩ…….

ሰውየው ግን አልቆመም…..ነገር ግን አትጨነቁ፤ እየመጣ ያለውን ጠላትም ቢሆን ፤ በግምገማ ሰበብ ሊያልፍ መስመራችን ሊበርዝ የተነሳውን ሰርጎ ገብ የገባበት ገብተን አከርካሪውን እንሰብረዋለን! አለ ቤቱ እንደ ኤሌክትሪክ በሚነዝር ጩኽትና ተስፋ ተቀጣጠለ……ሰውየው ይሄንን ሲያደርግ የቀጣይ የሃገሪቱ ወንበርን እያሰበ እንደነበር ያወቁ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ….

ሽፈራውም በህወሃት ካድሬዎች ልብ ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ…. በእርግጥ በህወሃት የድርጅት በአል ላይ እንደ ብዙ ነባር አመራር ማን የበለጠ ታማኝ ነው በሚለው ትርክት አስደሳች ንግግር በማድረግ ቢታወቅም የዚህን ቀን ያህል ግን የተቀመረ ጨዋታ ህይወቱን ሙሉ ተጫውቶ አያውቅም፡፡

ወርሃ መጋቢት  የምርጫው ፉክክር በእጅጉ ግሎ ነበር…….ውስጥ ለውስጥ ይናጣል፡፡ በዚህ ሂደት ደኢህዴን ባልታሰበ ሁኔታ ታህሳስ ላይ የአመራር ለውጥ ለማድረግ ወሰነ! በመለው ሃገር የተቀጣተለውን አመፅ የሚመጥን አመራር እንዲመጣ እድሉን መክፈት አለብን የሚል አቋም ወሰደ፡፡ ሽፈራውም የዚህ ውሳኔ አካል ነበር፡፡ ህወሃት እንደተለመደው በዚ ሰአት እኛ አንወዳደርም የሚለው አቋሙ እንዳለ ሆኖ፡፡ ኦዲፒ ያልታሰበ የአሰላለፍ ለውጥ በማድረግ የትግሉን ሂደት እንዲጦዝ አደረገው፡፡ብአዴን ከኦዲፒ ጋር በመመካከር እየሰራ ቢሆንም ጥቂቶች በዚህ ሰአት እኛ ወደፊት መምጣት አለብን የሚል ግፊት ያደርጉ ነበር፡፡
እለተ ምርጫ እና የህወሃት ስልት፡፡

የተሰራው ስሌት በእጅጉ ቀላል ነበር፡፡ ሃይል መበተን ወይም በትግል ስሙ ቆረጣ ማካሄድ ነው፡፡ በዚህም በውስጥ ስምምነት በማድረግ ቀድሞ በመጨረስ ሽፈራውን በእጩነት ማቅረብ ነበር፤ ከዚያም ከብአዴን ዋናውን ሰውዬ እንዲወዳደር(እንዲጠቆም) ማድረግ፡፡ ስለዚህ የብአዴን ድምፅ በሙሉ ወይም ባብላጫ ወደ ትልቁ ሰውዬ ሲሄድ፤ የደኢህዴን አብላጫ እና የህወሃት ሙሉ ድምፅ በሙሉ ወደ ሽፈራው፤ የኦዲፒ ድምፅ ወዴትም ቢሄድ ኢሬለቫንት ማድረግ ነበር፡፡ ቀላል እና የሚሰራ የሚመስል ስልት፡፡

አለቀ በመጨረሻም ለረጅም ሰአታት በተደረገው ትንቅንቅ ፤ የብአዴኑ ሰውዬ እና ብአዴኖች በሙሉ ባይባልም ማርሹን አዞሩት፤ ትልቁ ሰውዬ ራሱን ከውድድር አገለለ፤ ጭራሹኑ ከህወሃት ደብሪፅ በብአዴኖች ተጠቆመ፡፡ ደመቀ የሜዳው ንጉስ ሆነ! ደኢህዴን በታሪክ አጋጣሚ ታላቅ ውሳኔ ወሰነ፡፡ እናም ተስፈኛው ሰውዬ በ50ዎቹ ድምፅ ማለት በሚገመት ሁኔታ መላውን የህወሓት እና ጥቂት የሱ ወዳጆች ተጨምረውበት ጥሩ ተሸናፊ መሆን ሳይችል እያዘነ ወደቤቱ ገባ፡፡ በአብይ ፆም አብይ በኢትዮጵያ ምድር ተወለደ፡፡ ሰውየው ጠዋት ቃር ቃር እያለው ወደ ኢህአዴግ ፅ/ቤት መኪናውን እያሽከረከረ በመሄድ………ከዚያ ወንበሩ ላይ ቁና ተነፈሰ…..ኡፍፍፍፍ………..

ግን ሰውየው ደቡብ ኮርያም ኮርያ ምን ያደርጋል??…..መቀሌ አትናፍቀውምን??
@የብልፅግና ዘመን

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top