Connect with us

ትህነግና ትግራይ፤የሚረግጥ ባልን መምረጥ ምርጫ ነው፤ ባሌ እናቴን ይርገጣት ማለት ደግሞ ቅብጠት!

ትህነግና ትግራይ፤የሚረግጥ ባልን መምረጥ ምርጫ ነው፤ ባሌ እናቴን ይርገጣት ማለት ደግሞ ቅብጠት!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ትህነግና ትግራይ፤የሚረግጥ ባልን መምረጥ ምርጫ ነው፤ ባሌ እናቴን ይርገጣት ማለት ደግሞ ቅብጠት!

ትህነግና ትግራይ፤የሚረግጥ ባልን መምረጥ ምርጫ ነው፤ ባሌ እናቴን ይርገጣት ማለት ደግሞ ቅብጠት!

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)

ህወሃትና ትግራይ አንድ ነው የሚሉም ሆኑ ህወሃትና ትግራይ ምን አንድ አደረጋቸው ባዮች መነሻቸው ልክ ነው፡፡ በትግራይ ቁጥሩ ምንም ይሁን ከአድዋ መራሹ ጸረ ኢትዮጵያ ልብ የራቀ ብዙ ቁጥር ያለው ህዝብ አለ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እጅግ የሚበዛው በትርክቱ ወድቆ የህወሃትን ማታገያ አንስቶ ያለ ህወሃት ሞቴ በሚል የሚሰለፍ ነው፡፡

የማዕከላዊ መንግስቱና የትግራይ ክልልን ግጭት ወደ ሃይል እርምጃ ሲገባ የደገፍነው ህወሃትን ማፍቀር ወንጀል ሆኖ አይደለም፤ በህወሃት ፍቅር አብዶ የሀገር ዳር ድንበር ጠባቂ ሲታረድ ወንጀሉን ልክ ነው ማለት ነው፡፡

የህወሃት የማታገያ ስልቶች የታወቁ ናቸው፡፡ አማራን ጠላት አድርገው የተነሱ የባንዳ ልጆች ቁልፉን የድርጅቱ ዓላማ ነደፉ፡፡ ሌላው ለነጻነት በሚል የዋህ ስሜት ተከተላቸው፡፡ ብዙ ትውልድ ተከታትሎ በጸረ አማራ ትርክት ተሰራ፡፡

አክሱም ጽዮን ጋቢና ካባ ለብሰው የሚያነግሱት ህወሃታውያን በደቡብና ኦርቶዶክሳውያን በሚያንሱባቸው አካባቢዎች ኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ ጠላትና ወራሪ መሆኗን በሰነድ በተደገፈ ስልጠና ሰጡበት፡፡

አፍሪቃ የምትኮራበትን ፊደል ጠሉት፡፡ የኢትዮጵያን ገናና ታሪክም አንቋሸሹ ሌላው ቢቀር ዛሬ አፈር ልሰን ተነሳንበት ያሉት የአሉላን ስም እንደ ሸዋ ሳያከብሩት፣ እንደ ጎንደር ሳያነግሱት፣ እንደ ጎጃም ሳይደምቁበት፣ እንደ ኢትዮጵያ ክብር ሳያደርጉት የኖረ ስም ነው፡፡

ታሪክ መዝዞ መነታረክ ረብ የለውም፡፡ በአባቶቻቸው ጥፋት ተሸማቀው የጥፋት ስልት ሀገራቸው ላይ የነደፉ ነጻ አውጪ ነን ባይ ቅኝ ገዢዎች ያሰለፉት መንጋ ዛሬ ወደ ቀበሮ አፍ እንደገባ በግ ይቆጠራል፡፡

ችግሩ የትህነግና የህወሃት ወዳጅነት መስመር ሲያልፍ ነው፡፡ አብይ አዲ እንዳሻት መሆን የምትችለው ህወሃት ለምን ጋምቤላን አትዘርፍም፤ ለምን ጎንደርን አትወርስም? የኦሮሞን ቡናና ወርቅ መሸጥ አለባት፤ የአፋር ጨው የራሷ ነው፤ ህገ ወጥ የደቡብ ሙዝ አስመጪና  ላኪ መሆን አለባት የሚለውን ነው የማያግባባን፤ ስላላግባባን፤ አልተግባባንም፡፡

ትግራይ የሚጠፈጥፋትን፣ የሚያቀውሳትን፣ ለታሪኳ የማይመጥንን፣ ክብሯን የሚያዋርደውን ባል መምረጥም አብራ መኖርም ትችላለች፡፡ ጠባችን ባሌ እናቴን ካልደበደበ ስትል ነው፡፡ ነገሩ እንደዚያ ነውና፤

ጌታቸው ረዳ ትናንት እሳትና ጭድ እያለ በአደባባይ ሳይቀር በሚያወራው ሴራና ደባ ዛሬ ትግራይን ከኢትዮጵያ ሊበጥስ ብዙ መከራ ያያል፡፡ ያንን ማገዝም ማክሸፍም የትግራዋይ ሃላፊነት ነው፡፡

ግን የማይቻለውን አውቀን ከኖርን መቻቻሉ አይከብድም፡፡ የትግራዩ ነጻ አውጪ ትህነግ የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑ ሊያውም ዘለዓለማዊ ጠላትነቱ ላይቀር ታትሟል፡፡ ላይጠፋ በደማቅ የታሪክ ቀለም ተጽፏል፡፡ ይሄንን እኛ ኢትዮጵያውያን የታሪካችን መጥፎ ጠባሳ አድርገን ስናስበው እንኖራለን፡፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ትግራይን ለቆ ወጥቷል፡፡ በአበደ የትህነግና ትግራይ ፍቅር ውስጥ በሀገር ፍቅር ስሜት ያልተገባ ሞት መሞት የለበትም፡፡ የብዙሃኑ ምርጫ ሊከበር ይገባል፡፡ ያ ምርጫ ደግሞ ትግራይ በትህነግ ፍቅር አብዳ ትህነግን መደገፏ ነው፡፡ ቀጥሎ የሚሆነው አንድና አንድ ጉዳይ የትግራይን ፍላጎት ላከበሩት ኢትዮጵያውያን ትግራይም የኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ማክበር ነው፡፡ ያ ፍላጎት ህወሃትን ዳግም በኢትዮጵያ ምድር አለማየት ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top