Connect with us

ግብፃዊዩ የፖለቲካ ተንታኝ ለፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ ያስተላለፈው መልዕክት

ግብፃዊዩ የፖለቲካ ተንታኝ ኢማድ አልብሔይሪ ለፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ ያስተላለፈው መልዕክት
ሱሌማን አብደላ

ነፃ ሃሳብ

ግብፃዊዩ የፖለቲካ ተንታኝ ለፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ ያስተላለፈው መልዕክት

ግብፃዊዩ የፖለቲካ ተንታኝ ለፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ ያስተላለፈው መልዕክት

ግብፃዊዩ የፖለቲካ ተንታኝ ኢማድ አልብሔይሪ ለፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ሲሲ ያስተላለፈው መልዕክት

***

ፕሬዚዳንት ሲሲ ሆይ ከነጮች ጋር ሆነሀ ለማረድ የገዘገዝካት ኢትዮጵያ አትምርህም

ሲሲ ሆይ በቀደዱልህ ቦይ መፍሰስህን አቁም። ዋጋ ያስከፍላል፣ አውሮፓና አሜሪካ አብይ አህመድን ከስልጣኑ አውርደው በሌላ መተካት የፈለጉበት ምክንያት ግልፅ ነው። ባጭር አነጋጋር አብይ አሕመድ ለነጮቹ ፍላጎት አልገዛም አልታዘዝም በማለቱ ነው ።

ለዚህ ነው እነሱ በሩቅ ሁነው ከውስጥ የቅርብ ጠላት ያበጁለት። እነሱ የፈጠሯቸውን ጥላቶች ተጠቅመው አሰቡበት አልደረሱም። አንተም ከነሱ ጋር አብረህ ቢላዋኻን ስለህ ተነሳህበት። ገዝግዘህም አቆሰልከው። ግን አልሞተም  ነጮቹ ከኢትዮጵያ ሩቅ ናቸው። አብይ እነሱን መጉዳት አይችልም። ግብፅና ሱዳን ግን በጣም ቅርብ ነን። ነጮቹ በኢትዮጵያ ላይ የሞከሩት መንገድ ልክ አልነበረም፣ እነሱም አምነው፣ የሄድንበት መንገድ ልክ ስላልነበረ አብይ ሆይ እንወያይ እያሉ እየለፈለፉ ነው።

ሲሲ ሆይ አንተስ ምን ሊበቃህ ነው..?

እንደነሱ አንተም እንወያይ ልትል ነው..?  

ሠውየው እኮ አብይ አሕመድ ሚባል  የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነው። አንተ ከነጮች ጋር አብረህ አስተኝተህ በቢላዋ ጉሮሮውን ቆርጠህ ልትገድለው አስበህ ያቆሰልከው ሰው ነው። አንተ ከነሱ ጋር አብረህ ያቆሰልከውን የቁስሉን ህመም  በደንብ  ያውቀዋል። አሁን ትንሽ ቢቀረው እንጅ ቁስሉ እየደረቀለት ነው። ከበፊቱ በበለጠ አምሮበት በጀግንነት በክብርና  በላቀ የህዝብ ፍቅር ታጅቦ ወደቦታው ተመልሷል።

ነገ ግን እሱ በምላሹ  ጉሮሯችንን ሊያንቀን ነው ። አንተስ ምን ልታደርግ አሰብክ. ?

የዱሮውን ነጠላ ዜማ ልትከፍትልን ነው ..? የመለድከው ቀያይ መስመር ልታሰምርልን ይሆን ..? አንተና ሚኒስተሮችህ ሀገር ላገር እየዞራችሁ በጋዜጠኞች ፊት

      የግብፅ ታሪካዊ ውሃ ……. አይነካም

    ሁሉን አቀፍ ስምምነት ….. ያስፈልጋል   

   ከሦስተኛ ሙሌቱ በፊት ህጋዊና አስገዳጅ ……. ስምምነት ላይ መድረስ አለብን ልትሉን ይሆን .?

ከዛስ ደሞ ኢትዮጵያ ይህንን ተቀብላ እንድትስማማ አለማቀፉ ማህበረሰብ ጫና

እንዲያደርግባት መግለጫ ትሰጡ ይሆን

ከዛም የተባበሩት መንግስት ድርጅት የአውሮፓ ህብረት ያደራድረን ልትሉ ይሆን ?

ተሰታችሁኮ ያልቅም ይሄንን ብላችሁ አልበቃ

ሲላችሁ ፤ « ኢትዮጵያን በኬኒያና ኡጋንዳ በኩል ከበናታል».! ወዳጆቿን ጅቡቲና ሶማሊያን ይዘናቸዋል። ከሱዳንና ከደ/ሱዳን ጋር ውይይት እያደረግን ነው ልትሉን ይሆን .? እናተ አትሉም አይባልም።  እንደለመዳችሁት ትሉናላችሁ።

የናተ ይሄ ሁሉ ማለት ለኢትዮጵያ ምኗም አደለም። እኛ ይሄንን እያልን ስንጮህ ኢትዮጵያ ግድቡን ጀምራ ገንብታ ውሃ ቆጥራበታለች። እኛ ይሄንን እያልን ስንጮህ ኢትዩጵያ የመጀመሪያና ሁለተኛውን ውሃ ሙሊት ሞልታለች።

ፕሬዚዳንት ሲሲ ሆይ በቀደዱለት ቦይ መፍሰስ ፣ ነገንና ከነገወዲያን አስቦ አለመጓዝ ትርፉ ፀፀት ነው ። ሳይረፍድ በግዜ ሌላ መላ ፈልግ ።

ሱሌማን አብደላ

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top