Connect with us

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-
ሙሼ ሰሙ

ነፃ ሃሳብ

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-

(ሙሼ ሰሙ)

ዜጎች ሰርቶ የመብላት መብታቸውና ሕልውናቸውን የማስቀጠል መብታቸው በመመርያ የማይጣስና የማይገሰስ ነው።

የመንግስት አንዱና ዋነኛው ተግባር ዜጎች ሰርተው የሚኖሩበት ሁኔታዎች ማመቻቸትና እድል መፍጠር ነው፡፡ መንግስት ‘ራሱ የስራ እድል መፍጠርም ሆነ በግል ዘርፉ አማካኝነት ስራን ማመቻቸት ካልቻለ፣ ዜጎች ለእርዳታ ተቀባይነትና ለማህበራዊ ቀውስ እንዳይዳረጉ ሲባል ኢ- መደበኛ ስራዎችን ቢቻል ከታክስ ነጻ በማድረግ ወይም በጣም በዝቅተኛ ታክስ ሰርተው የመኖር “እድል” ሊነፍጋቸው አይገባም፡፡

ይህ ደግሞ ከጎረቤቶቻችን ጀምሮ በብዙ ሀገሮች የተለመደ ነው።

Reserve Army of labour ከሚባለው ሁልቆ መሳፍርት የሌለው ስራ አጥ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን በላይ ለሆኑ ዜጎቿ የስራ እድል መፍጠር ይጠበቅባታል፡፡

እንደሚታወቀው ግን ሀገራችን እንኳን አዲስ የስራ ፈላጊውን ይቅርና ለነባሩ ስር አጥም በቂ የስራ እድል  ማፍጠር የቻለች ሀገር አይደለችም፡፡

ይህ ነባራዊ ሀቅ ባፈጠጠባትና ባገጠጠበት ሀገር ተቆጥረው በገደብ እንዲገቡ በሕግ የተፈቀዱ አልባሳትና ቁሳቁሶችን እጅግ ፈታኝ በሆነ መንገድ ጥሪት አብቃቅተው ትንሽ ትርፍ ለማግኘት ከሚበላ፣ ከሚጠጣና ከትራንስፖርት ቆጥበውና ተዳብለው እያደሩ ቤተሰቦቻቸውን ዳቦ ለማብላት የሚታገሉ በተለምዶ የሻንጣ ሰራተኛ የሚባሉ ኢ-መደበኛ ለፍቶ አዳሪዎችን፣ በዚህ ፈታኝ ጊዜ ስራቸውን ማገድ ስራ አጥነትን በማባባስ ማህበራዊ ቀውስንና ሁከት ከመቀስቀስ ውጭ ምን ትርፍ እንዳለው ለመገመት አዳጋች ነው፡፡ ዜጎች እኩል ናቸው በሚባልበት ሀገር ስሞታቸው በልዮነት የተሰማላቸው አስመጭዎችስ በተለይ የውጭ ምንዛሪ የማግኘት፣ የማስመጣትና ዝቅተኛ ታክስ የመቀረጥ ሞኖፖሊ እንዴት ሊኖራቸው ቻለ?

መንግስት እነዚህን አነስተኛና ጥቃቅን እቃዎችን በመቅረጥ ከሚያገኘው ገቢ ይልቅ ኢ- መደበኛው ስራ ከሚፈጥረው የስራ እድል፣ ከስራ እድሉ ከሚገኘው ግብርና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚሰበስበው ገንዘብ ወዘተ ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑ በየትኛው ጥናት ተፈትሾና ሚዛን ደፍቶ መንግስትን ጎድቷል፣ በዝብዟል እንዳስባለ ግራ የሚያጋባ ነው ? መንግስት ማለት ሕዝብ መሆኑንስ እንዴት ተረሳ? የተራበ፣ በማህበራዊ ቀውስ የተመታ፣ በድህነት ክብሩን ያጣ ተመጽዋች ዜጋ የሞላበት ሀገርና መንግስት ላይ የሚካሄደው ዓይን ያወጣ ተጽእኖ ምን እንደሆነ በግልጽ እየታየ እንደዚህ ዓይነት አካሄድ መከተል ለምን ተመረጠ? እድሜው ለስራ ከደረሰው ከከተማ ነዋሪ ውስጥ 50 % ስራ አጥ ሆኖ እያለ በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ስራ የፈጠረ ዘርፍን ማሻሻልና ማጎልበት እየተቻለ ያለ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት በማገድ ተጨማሪ ዜጎችን ስራ አጥና ምጽዋተኛ በማድረግ ወዴት ለመድረስ ይታሰባል ? አፋጣኝ መልስ የሚሻ ጉዳይ ነው?!

በዚህ ፈታኝ በሆነና ስራ በተዳከመበት፣ ኢኮኖሚው በተናጋበት፣ ኑሮ በተወደደበት፣ እቃ በጠፋበት፣ የአጉዋ ተጠቃሚና ሌሎች ሰራተኞችን ከስራ በማፈናቀል ሁለንተናዊ ቀውስ ለመፍጠር ሴራ በሚሸረብበትና መንግስት የሕዝብን ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ በሚሻበት ወቅት በድንገት ይህንን ዓይነት ውሳኔ መወሰን ሕዝባዊነቱና ለመንግስት ተቆርቋሪነቱስ ምኑ ላይ ይሆን ?

እስኪ መለስ ብለን ደግሞ ገቢዎች በዚህ ደረጃ የተማረረበትና ዜጎችን አምርሮ የተቆጣበት የሻንጣ ስራ ተጠቃሚዎች እነማን እንደሆኑ እንፈትሽ ?

-ዋነኛው የአየር መንገድ ሲሆን አንዱና ከፍተኛ ገቢ    በሻንጣ ስራ የተሰማሩ ዜጎችን ማመላለሱ ነው፡፡

-ቀጥሎ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎች አሉ

-የሻንጣ ሸቀጥ አስመጭው ዜጋ (ተመላላሽ)

-ሸቀጡን የሚረከበው ሱቅና በሱቁ ውስጥ የተቀጠረው፣ ሱቅ በደረቴውና የመንገድ ዳር ነጋዴ …

-የሻንጣ ስራውን ለመከወን በስደት የሚገኙ ዜጎች

-የሻንጣ ነጋዴዎችን የሚያመላልሱ ታክሲዎች

-ሱቅ አከራዮች

-የጉምሩክ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ወዘተ ናቸው፡፡

እንግዲህ ከአየር መንገድ ውጭ እነዚህ ሁሉ  ዜጎች የመንግስትን እጅ ሳይጠብቁ ከእጅ ወደ አፍ ቢሆንም ሆዳቸውን ለማሸነፍ የሚታትሩ ዜጎች ናቸው።  ክልከላው አስፈላጊ ከሆነ እነዚህ ዜጎች ሕልውናቸውን ለማስቀጠል አማራጩ ምንድን ነው?!

የሻንጣ ስራ ለምን የስራ እድል ሊሆን ቻለ? የሻንጣ ኢ-መደበኛ ስራ የግድ የስራ እድል የሆነበት ምክንያት ጉምሩክ የገቢ ቀረጥን በመሰብሰብ ዙርያ ከሚታማበት ሙስና ይጀምራል። ቀጥሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እጦት፣ የቫት ደረሰኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች ተጽእኖ፣ ነጋ ጠባ ብለው ዋጋ የሚቆልሉና እየተመሳጠሩ የገቢም ሆነ የትርፍ ግብር የማይከፍሉ አስመጭዎች ውድድሩን ከንቱ ማድረጋቸውና ውዳቂና ርካሽ ሸቀጥ ያለ አማራጭ በገፍ የሚግበሰብሱና የግብይት ስርዓቱን በሞኖፖሊ የተቆጣጠሩ አስመጭዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ምሳሌያዊ ንጽጽር። ዛሬ ፋና ላይ እንደሰማሁት ከሆነ በጣት የሚቆጠሩ አስመጭና አከፋፋይ ነጋዴዎች ከ32 ነጥብ 5 ቢሊየን (የተደረሰበት ነው እንግዲህ) ብር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ደረሰኝ ባለመቁረጥና ሀሰተኛ ደረሰኝ በመስጠት ግብይት በመፈጸማቸው ተከሰው 8 ሚሊየን ብር ብቻ አስተዳደራዊ ቅጣት ተቀጥዋል፡፡ ይህ ገንዘብ የሀገሪቱ በጀት 6 በመቶ ሲሆን የሕዳሴን ግድብን 1/3 ገደማ ይሸፍናል።

ንጽጽሩን እንቀጥል። ሀገሪቱ ውስጥ የሚመላለሱ የኢ-መደበኛ የሻንጣ ነጋዴዎች እንዲያስገቡ በቁጥር የሚፈቀድላቸው 29 አነስተኛና ጥቃቅን ሸቀጥና አልባሳት አይደለም፤ በዚህ ሰንሰለት ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ሃይሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የሚያስገቡት ገቢ ቢደመር መንግስት በሕገ ወጥ ነጋዴዎች ያጣውን  32 ነጥብ 5 ቢሊየን 10 በመቶ አያክልም፡፡ ጥቂቶች 325 ቢሊየን ብር በሕገ ወጥ መንገድ ግብይት ፈጽመው 8 ሚሊየን ብር ይቀጣሉ፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቀጠሩ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ኢ- መደበኛ ስራ ሰርተዋል በሚል ያውም ሕገ ወጥ ሳይሆኑ በአንድ መስርያ ቤት መመሪያ በሕገ ወጥነት ይፈረጃሉ፣ ተግባራችሁ በሕግ ያስጠይቃል ይባላሉ።

በዜጎች መካከል እንደዚህ ዓይነት ልዩነት እየፈጠሩ በፍርደ ገምድልነት ማህበራዊ ቀውስ ማስፋፋትና ቤተሰብ መበተን? በየትኛው የሕገ መንግስቱና ሕግጋቶቹ ላይ ለየትኛው ባለስልጣንና ሹመኛ የተሰጠ ስልጣን ይሆን?! ስራ ለመፍጠር አቅምና ብቃት የሌለው ሀይል የብዙዎች እንጀራ የሆነውን ኢ- መደበኛ ስራን ለማፍረስና ያለ ቅድመ ዝግጅትና አማራጭ ቤተሰብ ለመበተን የሞራል ልዕልናውንስ ከየት አገኘው?!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top