Connect with us

የኦሮሞን የታላቅ ባህል ምልክትና ታላቅ ሰው እየገደልክ ለኦሮሞ እታገላለሁ ማለት ቀልድ ነው፡፡

Social media

ነፃ ሃሳብ

የኦሮሞን የታላቅ ባህል ምልክትና ታላቅ ሰው እየገደልክ ለኦሮሞ እታገላለሁ ማለት ቀልድ ነው፡፡

የኦሮሞን የታላቅ ባህል ምልክትና ታላቅ ሰው እየገደልክ ለኦሮሞ እታገላለሁ ማለት ቀልድ ነው፡፡ ይሄ ተላላኪነት ይባላል!!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ድሬቲዩብ)
ወያኔ ትጠላው የነበረው ከእሷ ሌላ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ክብርና ባህል ነው፡፡ ለዚህ ነው ሌላው ህዝብ ምልክቴ መሪዬና ጌጤ የሚለው እንዳይኖር ያደረገችው፡፡ በኦሮሞ ባህል ከአባገዳው በላይ ምን ይኖራል? ጁንታው ግን የኦሮሞን ሀዘን ለማበርታት ኦሮሞን እታደጋለሁ የሚለው ተራ ተላላኪ ልኮ የኦሮሞን የምልክት አበባ ይቀጥፋል፡፡

የከረዩ አባ ገዳ ለምን እንዲህ ሆኑ? ከቀናት በፊት ከረዩ እኔም ለሀገሬ አለሁላት ብሎ በሚያስገርም ንቅናቄ ሆ ብሎ አደባባይ ወጣ፡፡ የከረዩ ልጆች ለኢትዮጵያ እዘምታለሁ አሉ፡፡ ሸኔ አንድ ፍሬ ልጅ ነው፤ ነፍስ አያውቅም፡፡ የላከው የሚቆጣው መስሎት “አንተ እያለህ እንዴት ይሄ ሁሉ ከረዮ ከኢትዮጵያ ጎን ይቆማል?” በሚል ቁጣ እንዳይደርስበት አቄመ፡፡ ያ ቂም ነው ታላቁን የባህል መሪ ያስገደለው፡፡

አባ ገዳ ከድር ሀዋስ ቦሩ በኦነግ ሸኔ መገደላቸውን የክልሉ መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡ ሸኔ ለኦሮሞ ቆሜያለሁ እያለ የኦሮሞን ምልክቶች በየተራ ሲቀጥፍ ቢያንስ የላከችው ጁንታ በራሷ ሰው እንደማትቀልድ ጉያዋ ሆኖ አለመማሩ ያሳዝናል፡፡ እንዴት ሰው በገዛ አባቱ፣ በገዛ ምልክቱና በገዛ እሴቱ ላይ ቃታ ይስባል?

ባለፉት አመታት መልእክተኛው ሸኔ የታዘዘውን አድርሷል፡፡ በወለጋ ብርቅ የኦሮሞ ልጆችንን ሜዳ ላይ ደማቸውን አፍስሷል፡፡ በመላው ኦሮሚያ የህዝቡ ምልክት የሚባሉትን ቀጥፏል፡፡ የኦሮሞ ልጆች የእለት ዳቦ የሚበሉባቸውን ፋብሪካዎች አንድዷል፡፡ የመቀሌ ሙታኖችን ለመታደግ የራሱን ከተሞች አውድሟል፡፡

ሸኔ የኦሮሚያ ከተሞች አልሚ እንዲፈራቸው ለማድረግ ያልሰራው የጥፋት ስራ የለም፡፡ ኦሮሞን ከሚወደው ህዝብ ዘንድ ለማጋጨት ብዙ ነፍስ አጥፍቷል፡፡ በዚህ ሁሉ ውጤት ሲያጣ አሁን ደግሞ የራሱን አባቶች መግደል ጀመረ፡፡

ሸኔ በካደ ማግስት በመግለጫ ነውሩን የሚያምን ስለሆነ የእሱ ምስክርነት ብዙም አያስፈልግም፤ እኛ ከወያኔ ጉዳይ የለንም ካለ በኋላ ነው ጋብቻ ፈጽሞ አብሮ እየጠፋ ያለው፡፡ የሚያፈጠፋው ጥፋት ግን ህመሙ ከባድ ነው፡፡ በተለይ እንዲህ የኦሮሞ ምልክት የሀገር ጌጥ የሚባሉ አባቶች ላይ ቃታ መሳብ ነውሩን መሪር ያደርገዋል፡፡

አባ ገዳው ላይ የተሳበው ቃታ፣ ሀገር ላይ እሴት ላይ ሰላም ላይ ክብር ላይ እንደተተኮሰ ይቆጠራል፡፡ ሰላም በሚያወርዱት አባቶች ላይ ሞት መፍረድ የነውሩ መጠን ግዝፈት ማሳያ ነው፡፡ ሸኔ የላከውን ለማስደሰት የተጠጋበትን ጎጆ ማቃጠል ጀምሯል፡፡ ጎጆ ውስጥ ራሱ መኖሩን አያውቅም፡፡

ከረዮዎች ትናንት ከሀገራቸው ጎን ነበሩ፤ በኢትዮጵያ የነጻነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው፣ ነገም ከሀገራቸው ጎን ይቆማሉ፡፡ ይሄ ነውር ህዝቡን ቢያበረታ እንጂ ሸኔን እንደማያስከብር መረዳት ያቃተው ነጻ አውጪ ነኝ ባይ የትህነግ ባሪያ ውጤቱን ያየዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን እናሸንፋለን፡፡ ከዚህ ቀደም የደህንነት ሹሙ መሪ እንዳሉት ሸኔ ድር ነው፡፡ ሸረሪቷ አሁን በደንብ እየተጠረገች ስለሆነ የድሩ ሴራ የትም አይደርስ፤ ሸረሪቷ ስትጠፋ ጌጥ እንኳን መሆን ሳይችል ተንጠልጥሎ ይቀራል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top