Connect with us

እንደ ሸህ ሑሴን ንግርት በመገለጥ ላይ የሚገኘው የጌታቸው ረዳ ትንቢት

እንደ ሸህ ሑሴን ንግርት በመገለጥ ላይ የሚገኘው የጌታቸው ረዳ ትንቢት
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

እንደ ሸህ ሑሴን ንግርት በመገለጥ ላይ የሚገኘው የጌታቸው ረዳ ትንቢት

እንደ ሸህ ሑሴን ንግርት በመገለጥ ላይ የሚገኘው የጌታቸው ረዳ ትንቢት

(አሳዬ ደርቤ~  ለድሬ ቲዩብ)

ያለፉትን አራት ወራቶች ሲገመገሙ፡-

ጭፍራን እና ሜሌን ተቆጣጠር ተብሎ የተላከው የአሸባሪው ህወሓት ጦር በወረረው የአፋር መሬት ላይ መቀበር እንጂ ወደ መቀሌ ተመልሶ መኖር አልተቻለውም፡፡

የሱዳንን ኮሪደር ማስከፈት የሚል ተልዕኮ ይዞ ከትግራይና ከሱዳን እየተነሳ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲከፍት የነበረው የጁንታው ሠራዊትም በእንበር ተጋዳላይና በኡዛዛ አሌና እየጨፈረ ከገባ በኋላ መቃብሩ ውስጥ መግባት እንጂ ኮሪደሩን ማስከፈት አልተሳካለትም፡፡

‹‹ጎንደርን አስገብሬ ወደ ባሕር ዳርና ጎጃም አመራለሁ›› የሚል ሕልም ይዞ ወደ ደብረ ታቦር አቅጣጫ ካመራው አሸባሪ መሃከልም እኩሉ በደባርቅ መብረቅ ተጠራርጎ ሲደመሰስ፣ እኩሌታው ደግሞ በድምጽ ፍጥነት ወደ ኋላ ለመመለስ ተገድዷል፡፡

እንደ አጠቃላይም በ17 ግንባሮች ጥቃት ከፍቶ የሞትና የሽንፈት ጽዋን የተጎነጨው አሸባሪ የወረራ ሕልሙን አሳክቶ መዝረፍና መጨፍጨፍ የቻለው በቂ ዝግጅት ባልተደረገበት በወሎ ግንባር ብቻ ሲሆን ይሄንኑም ወረራ እውን ለማድረግ ከተራው ሠራዊት ባለፈ በርካታ የጦር መሪዎቹን እና አጋዚ የተባለ ክፍለ ጦሩን መገበር ግድ ብሎታል፡፡

በዚህም ትግል ሃይሉን የጨረሰው የሽብር ሠራዊት ወደ ሸዋ ከመገስገስ ይልቅ ወደ ኋላ የመመለስ ፍላጎት ቢኖረውም በራያ ጀግኖች የመመለሻ መንገዱ ስለተቆረጠበት ብሎም የአድዋ አለቆቹ ‹‹አዲስ አበባ መድረስ ካልቻልክ መደምሰስ እንጂ ወደ መቀሌ መመለስ አትችልም›› ብለው ስለገሰጹት ኦነግ ሸኔ ከሚባል የትግል (የሲዖል) አጋሩ ጋር በሸዋ ሮቢትና በተለያዩ የወሎ አካባቢዎች እየተዘዋወረ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ሲያደርስ ነበረ፡፡

አሁን ላይ ታዲያ ብዙዎች በጉጉት ሲጠባበቁት የነበረውና ኢትዮጵያን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የሚያሸጋግረው ነጋሪት በመጎሰሙ የጌታቸው ረዳ ትንቢት በገሃድ ተገልጦ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡ ኣይተ ጌታቸው ረዳ ባንድ ወቅት ‹‹ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ቢሆን እንወርዳለን›› ብሎ በተነበየው መሠረት ታጣቂውንም ሆነ አመራሩን ወደ እንጦሮጦስ የመላክ ሥነ- ሥርዓቱ ተጀምሯል፡፡ በአንድ ቀን ዘመቻም ወራሪውን ሃይል በማጽዳት ወሳኟን የጋሼና ከተማን ጨምሮ ላሊበላን፣ ሸዋ-ሮቢትን እና ሌሎች አካባቢዎችንም ጭምር ነጻ ማውጣት ተችሏል፡፡ ምንም እንኳን አሸባሪው ቡድን ወረራ ፈጽሞ ለወራት በቆየባቸው አካባቢዎች የጨፈጨፋቸውን ዜጎች ሕይወት ከሞት ማስነሳትና የዘረፈውን ንብረት መተካት የማይቻል ቢሆንም አውዳሚውን የሽብር መንጋ የመደቆስ ድግሱ ግን በሁሉም ግንባሮች እየተከናወነ ነው፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ ከሁለት ቀን በፊት እኩለ ሌሊት ላይ ወደ መቀሌ አምርታ ጌታቸው ረዳን የቀሰቀሰችውና ትዊተር ላይ ስታስለፈልፈው ያደረችው ድሮን ወደ እንጦሮጦስ የሸኘቻቸው የትሕነግ አመራሮች ሥማቸው ባይገለጽም ሳግ በሚተናነቀው ድምጽ ‹‹ኦቦሳንጆ ነው ለዚህ ጉዳት የዳረገን›› የሚል ሙሾ ተበራክቷል፡፡ ለወትሮው የአሸባሪው ይዞታዎች በጦር ጄት ሲደበደቡ በቅጽበት ውስጥ ከተጎዳው ጋር ያልተጎዳውንም ጨምረው የሚዘግቡት የጁንታው ሚዲያዎችም በዚህ ጉዳት ዙሪያ ተደብቀው እንዲያነቡ እንጂ በይፋ እንዲዘግቡ አልተፈቀደላቸውም፡፡ ይሄም ሁኔታ የድሮኗ ዒላማ በአሸባሪው ደጋፊዎችና ታጣቂዎች ልብ ውስጥ ትልቅ ስብራት በሚያስከትል አመራር ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሚገልጽ ነው፡፡

ጠቅለል ስናደርገው ለባለፉት ሦስት ወራቶች በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ወረራ የፈጸመው አሸባሪ የወሎን ምድር ተቆጣጥሮ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ ቢችልም በዚያው ልክ ደግሞ በርካታ አመራሩን እና ሠራዊቱን ወደ እንጦሮጦስ ለመሸኘት ተገድዷል፡፡ ባሁኑ ሰዓትም የውጊያ አቅሙን ሸዋ ሮቢት ላይ ጨርሶ የሚዲያ ትግል የጀመረው አሸባሪ፡-

በጥራጊ ክምር

ሕዳር ወሩ ታጥኖ፥  ጭሱ ሲመስል ጉም

ያኔ ነው ወራሪው

ወሎን በልቶ ኽዶ፥ ሸዋ የሚካተም›› የሚለው የሼህ ሑሴን ጂብሪል ተፈጻሚ ሆኖበት በመርገፍ ላይ ይገኛል፡፡

በጥቃት እየተንገበገበ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ የሰነበተው እንዲሁም አሸባሪውንና አጋሮቹን እንደ ድርጅት ለማክሰም ከሚያስችል የማጥቃት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያስገባውን ትእዛዝ ሲጠባበቅ የነበረው የወገን ጦር ደግሞ ከመጠቃት ወደ ማጥቃት ተሸጋግሮ እንዲህ በሚል አቋም የጌታቸው ረዳን ትንቢት በማሳካት ላይ ይገኛል፡፡

ዜጋ ለመጨረስ ፥ አገር ለመደምሰስ

መድረስ ካማራችሁ ፥ እንጦሮጦስ ድረስ

ያውና መሸኛው፥ መካተሚያ እርሳሱ

ከጥልቁ ግቡና፥ መጥታችሁ አፍርሱ››

ዘላለማዊ ድል ለአገራችን!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top