Connect with us

እውነት ነው ወራሪው ከአማራ ህይወት፣ መሬት፣ ንብረት እና ክብር እንጂ ሌላ ጠብ የለውም!

እውነት ነው ወራሪው ከአማራ ህይወት፣ መሬት፣ ንብረት እና ክብር እንጂ ሌላ ጠብ የለውም!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

እውነት ነው ወራሪው ከአማራ ህይወት፣ መሬት፣ ንብረት እና ክብር እንጂ ሌላ ጠብ የለውም!

እውነት ነው ወራሪው ከአማራ ህይወት፣ መሬት፣ ንብረት እና ክብር እንጂ ሌላ ጠብ የለውም!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ለድሬቲዩብ)

ቢያንስ አብረን አንድ ሀገር በመኖራችን በአንድ ላይ የምስራቅ አፍሪካ ህዝብ በመባላችን ምድባችን የሁላችንም የሰው ልጅ በመባሉ እናፍራለን፡፡ ሰው እንዴት በዚህስ ደረጃ እጅ እግር የሌለው ይሆናል?

ወራሪዋ በቀን ሰባት ጊዜ ከምታወጣው መግለጫ አንዱን አነበብኩት፤ መግለጫው አማራና የአማራን ህዝባዊ ሃይል ይማጸናል፡፡ ጉዳዩ እንግዲህ እንለፍበት መሆኑ ነው፡፡ የገረመኝ ግን ይሄንን ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዴት ሞኝ አድርገው ቆጥረውታል?

መግለጫው ከአማራ ጋር ጠብ የለኝም ይላል፤ እውነት ነው ወራሪዋ ከአማራ ህይወት ጋር እንጂ በግል ከአማራ ጋር ጠብ የላትም፡፡ የአማራን ነፍስ ማጥፋት ትፈልጋለች እንጂ አማራን አትጠላም፡፡ ከአማራ ንብረት ጋር እንጂ ከራሱ ከአማራ ጋር ምንም የላትም፡፡ ልትዘርፈው ስለምትፈልግ እንጂ አትጠላውም፡፡

እንዲህ አይነት ነውር ክብሩ የሆነ ሀሳብ ሰምተንም አይተንም አናውቅም፡፡ እግራቸው በረገጠበት ቦታ ሁሉ በዚያ የሆነውን መከራ ስቃይና ስቆቃ ያየነው የሰማነው በታሪክ አይደለም፡፡ ጭና የሆነው በአይናችን ነው፤ ማይካድራን አንብበበን ወይም ፊልም አይተን አይደለም፤ አጋምሳ ስለሆነው ሰው ነግሮን አይደለም፡፡

እርግጥ ነው፤  ድርጅቷ አስተዳደጓ ነው፡፡ ምላሷ ከረዘመ፣ ብዙ ከቀባጠረች፣ የውሸት አይነቷ ግራ ካጋባ የምትገባበት አጥታ ለመሆኑ ብዙ ታሪክ እናውቃለን፡፡ ግን የትናንትናው መግለጫ እኛ ከአማራ ምንም ጉዳይ የለንም ሲል አሳቀኝ፤

ለነገሩ መግለጫ ማውጣቱ እና ለዘራፊ በየቀኑ መልስ መስጠቱ አንዳች ረብ የለውም እንጂ እኛም እኮ ከወራሪው የግል ጠብ የለንም፡፡ እየሆነው ያለነው ገዳይ እጣ ፈንታ እንዳይኖረው መሞት መርጠን ነው፣ ሌላ ማጀት ገብቶ እንዳያግዝ ለመጠበቅ ነው፣ ሀገር አጥፊ እንዲጠፋ ነው፡፡ እንጂማ ወራሪዋን መች ጠላናት በህይወት መኖር የለባትም አልን እንጂ፤

ቢያንስ በአፋርና በአማራ ላይ ያንን ሁሉ ነገር ያደረገ አሁንም ብዙ ማድረግ ተመኝቶ እንቅልፍ አጥቶ በየመንደሩ የሚረግፍ ወራሪ እንዲህ ያለ መግለጫ ሲያወጣ አብረን ኖረናል፤ ነጥቀንው ብንበላም አብረን በልተናል፤ ገድዬው ቢሆንም አብረን ለቅሶ ውለናል፤ ባል ብነጥቅም ሰርግ ተካፍለናል ብሎ ለዚህ ህዝብ ማዘን የለበትም? ይሄ ህዝብ በሳቅ መሞት አለበት? በሰሩት የሚያፍረው አንሶ በመግለጫም ይፈር?

አሁን ኪሳራው ምንም ቢሆን ኢትዮጵያ ግን እንደምታሸንፍ አውቀዋል፡፡ ነገ የትም ሜዳ በገበሩት ህይወት እና በሀሰት ባማለሉት የትግራይ ህዝብ ልጆቻችንስ የሚል ጥያቄ መግቢያ ያሳጣቸዋል፤ ለነገሩ ሰው እየማገዱ ያሉት አንድ በአንድ ወደ እሳቱ ገብተው እያለቁ ነው፤ ለምን እንዲህ አደረጋችሁ ቢባል መልስ የሚሰጥ አውራ እየጠፋ መሆኑን አይተናል፡፡

ግን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፡፡ ለጊዜው ግን በመግለጫ ብዛት አልቻለቻችሁም፤ በውሸት ደግሞ የዓለም ሀገራት ሁሉ ቢገጥሟችሁ አሸናፊ ናችሁ፡፡ በመግለጫችሁ ቀልድነት ግን ከማፈር ወደ መሳቅ ስላሻገራችሁን እናመሰግናለን፤

ድል ለኢትዮጵያ!!

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top