Connect with us

ቱርክና ቻይናን እያስፈራሩ-አሜሪካ ፈራሁ ብሎ መንደባለል፤

social media

ነፃ ሃሳብ

ቱርክና ቻይናን እያስፈራሩ-አሜሪካ ፈራሁ ብሎ መንደባለል፤

ቱርክና ቻይናን እያስፈራሩ-አሜሪካ ፈራሁ ብሎ መንደባለል፤
ሁሉ ያቅታችሁ እንዴት ዱርዬነት እንኳን መላው ይጠፋባችኋል?

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)
አንድ ትውልድ የሙከራችሁ ማላገጫ ሆነ፡፡ የወንበዴነት ቅዠታችሁን ለማሳካት የአንድ ትውልድ ነፍስ ገበራችሁ፡፡ ሀገር መምራት አትችሉም፤ ፖለቲካም አይሆንላችሁም፤ ሰው ሆኖ እንደ ሰው ማሰብ ርቋችኋል፤ የሚገርመው ግን ዱርዬ እንኳን መሆንን ማሳካት ሲከብዳችሁ ማየት ነው፡፡
ዱርዬ የነቃ አይገደድም ይላል፡፡ እዚህ በመግለጫ ወዮ ከኢትዮጵያ ጋር የሰራ የውጪ ሃይል አፈር ድሜ አስበላዋለሁ ብላችሁ ቱርክን ቀና ብላችሁ ታያላችሁ፣ ቻይና ላይ ማፍጠጥ ትፈልጋላችሁ ደግሞ ሩሲያ ላይ መዛት ያምራችኋል፤ እዚያ ደግሞ ሞትን አለቅን ብላችሁ ትንደባለላችሁ፡፡

ከወገኖቻችሁ መካከል ከሞሶሎኒ ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ለመውጋት የሞከሩ አሉ ታሪክ ምን ቦታ እንዳስቀመጣቸውና ሙከራቸው ምን ውጤት እንዳመጣ ታውቃላችሁ፡፡ ከእናንተ ሰፈር የእንግሊዝን ጦር እየመራና ቀለብ እየሰፈረ መቅደላ ያደረሰ አለ መጨረሻው ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ለሀገሩ የሞተ ህያው ስም አለው፡፡

ሀገሩን የገደለ የማትሞት ሀገሩን ከመውጋት ውጪ ሙከራው ሁሉ ትውልድ የሚያፍርበት ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ እስከአሁን የእናንተ ልብ የላትም፤ እንደምትሆኑት ያልሆነች ሀገር ናት፤ ቢያንስ አለምክንያት ያሰለፋችሁትና የምታስጨርሱት ወገን ያሳስባታል፡፡ እንታገልልህ ከምትሉት ከእናንተ ፋሽሽት የምትሉት ሥርዓት ስለ ትግራይ መከራ እንቅልፍ የለውም፡፡

እናንተ ድል የመሰላችሁ ሁሉ ነገ የእኛ ያላችሁት የሚያፍርበት ቅሌት ነው፡፡ እናትን ልጆቿ ፊት መድፈር እንደ ሾትዊዝ ታሪኮች ከእናንተ የሚዛመደውን ሁሉ ሲያሸማቅቁት ይኖራሉ፤ ሊጥ ሰርቆ መሮጥ አልያም ከተማ ማውድም ውጤት ድል አለመሆኑን የምታውቁት ነገ ነው፡፡

አሁን እየሆነ ያለውን ልባችሁ ያውቀዋል፤ በቀን ሦስት መግለጫ ታወጣላችሁ፤ በገፍ ያልታጠቀ ሰራዊት ወደ መሳሪያ አፈ ሙዝ ትሸኛላችሁ፡፡ ድል አድርገናል ባላችሁበት ስፍራ እንቅልፍ የሌለው ህይወት ትኖራላችሁ፡፡

ሂሳብ አወራርዳለሁ የሚለው ቅዠት በደጋፊዎቻችሁ ፊት ሊያዋርዳችሁ ነው፡፡ ዛሬ በረገፈው ቁጥር ነገ ሂሳብ እናወራርድ ብሎ የትግራይ ህዝብ ይጠይቃችኋል፡፡ ኢትዮጵያ አታላ ያዘመተችው ሰራዊት የላትም፤ የሞተው ለሀገሬ ልሙት ብሎ በእናንተ ከመገዛት ጭቆናን እንቢኝ በሚል ሞትን የመረጠ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማትፈልገው ጦርነት ስለሆነ ኪሳራዋ ሁሉ በእናንተ ከመገዛት የሚበልጥ ኪሳራ የተመረጠ ምርጫ ነው፡፡ እዚህ ቻይና ላይ እየዛቱ ቱርክን ወየውልሽ እያሉ ሩሲያን እያስፈራሩ እዚያ አለቅን ብሎ መንደባለል ግን ታሪክ ፊት የቀሺም ድራም ክብር መያዝ ነው፡፡

አዲስ አበባን ልንቆጣጠር ነው፤ ከዚህ በኋላ ውጊያው አልቋል ድርድር የለም ብሎ መግለጫ እየሰጡ መልሶ ዘር ማጥፋት ተፈጸመብን ማለት ዓለም ፊት ርቃን መቆም ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ሆኖም ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ሆና ትልቅ ስሟን ይዛ፣ ይሄንን ሁሉ አልፋ በክብር ትኖራለች፡፡
ክብር ለዚህ ዋጋ ለሚከፍሉ ጀግኖቿ፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top