Connect with us

ከሰይጣን ጋር በሚደረግ ድርድር ሲዖልን እንጂ ገነትን መፍጠር አይቻልም

ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል ትግራይ ወደ መገንጠል የተሻገረው የወራሪው ቅዠት፤ ቤተ መንግሥት ሆናችሁ ያላሳካችሁት ትግራይን መገንጠል ኮንቲነር ቤት መታሰቡም ቅዠት ነው!
Social media

ነፃ ሃሳብ

ከሰይጣን ጋር በሚደረግ ድርድር ሲዖልን እንጂ ገነትን መፍጠር አይቻልም

ከሰይጣን ጋር በሚደረግ ድርድር ሲዖልን እንጂ ገነትን መፍጠር አይቻልም
(አሳዬ ደርቤ ~ለድሬ ቲዩብ)

ከሰይጣን ጋር በሚደረግ ድርድር መሬትን ሲዖል ማድረግ ይቻል እንደሁ እንጂ ምድር ላይ አምሳለ-ገነትን መፍጠር አይቻልም፡፡ የሰው ልጅን ከፍ ሲል አጋንንት ዝቅ ሲል ህወሓት ከማድረግ ባለፈ ሰይጣንን መላዕክትም ሆነ ሰው ማድረግ አይቻልም፡፡

ይሄንንም ልዩነት ያመጣው ዋነኛ ምክንያት የሰው ልጅ ጭንቅላት (ልብ) ደግነትን እና ክፋትን፣ ጭካኔን እና ርህራሄን፣ ፍቅርን እና ጥላቻን፣ ይቅር ባይነትን እና ቂም በቀልን መቀበል የሚችል ሶፍት ዌር የተገጠመለት ሲሆን የሰይጣን አዕምሮ ግን ጥፋትን እና ክፋትን ብቻ የሚቀበል መሆኑ ነው፡፡

እንዲያም ሆኖ ግን የሰው ልጅ አዕምሮም ክፋትን ጥሎ ደግ ለመሆን አስተዳደግ ይወስነዋል፡፡ በዚህም መሠረት ሤራን እንደ ሥራ፣ ጥፋትን እንደ ልማት፣ አረመኔነትን እና ክህዴትን እንደ መክሊት ቆጥሮ ይሄኑን እየተማረና እየተገበረ የኖረ አዕምሮ በስተርጅና ዘመኑ ‹‹መልካም ሁን›› ቢሉት እሺ አይልም፡፡

ልክ እንደዚሁ ሁሉ ህወሓት የተባለ ድርጅት ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ባንዳነትን እንደ መልካም ማንነት፣ ማውደምን እንደ ማለምለም፣ ክህዴትን እንደ ብልጠት፣ ግጭት መጥመቅን እንደ ተሰጥኦ፣ ጦርነትን እንደ ትልቅ ሙያ ቆጥሮ በሌሎች ርሐብ ላይ በጥጋብ ሲንደላቀቅ፣ በሌሎች ስቃይ ላይ እልፍ ሲሳይ ሲዝቅ፣ ከአገራዊ ፍርሰትና ድክመት ላይ ብርታት ሲጎናጸፍ፣ ከግጭት ማሣ ውስጥ ሕያውነትን ሲያተርፍ የኖረ ድርጅት በመሆኑ ብላቴና ከነበረበት ጊዜ አንስቶ እስከ እርጅና ዘመኑ ሲፈጽመው የኖረውን እርኩሰት ጥሎ በጎነትን ሊላበስ የሚችል ጭንቅላት የለውም፡፡

በመሆኑም ከዚህ ድርጅት ጋር በሚደረግ ድርድር ከሆነ አገር ጋር የሚዋሰንበትን ኮሪደር መስጠት ይቻል ይሆናል፡፡ በዚያ ኮሪደር ግን ኢትዮጵያን በሚያደማበት መሣሪያና ጥይት ፈንታ ማዳበሪያና ዱቄት እንዲያስገባ ማድረግ አይቻልም፡፡

ከህውሓት ጋር በሚደረግ ድርድር ክልሉ ላይ የተቋረጠውን የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት መቀጠል ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን በሚለቀቀው ኢንተርኔት አማራንና ኦሮሞን፣ ሙስሊምን እና ክርስቲያንን፣ ሶማሌን እና አፋርን እርስ በእርስ በማስተላለቅ ፈንታ ስለ አገራዊ አንድነት እንዲሰብክም ሆነ ዘርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ግጭት እንዳይጠምቅ ማድረግ አይቻልም፡፡

ከጁንታው ጋር በሚደረግ ድርድር ወንበር ማጋራት ይቻል ይሆናል፡፡ በተሰጠው ወንበር ፈንታ የሌላውን መንበር ተመኝቶ የመፈንቅለ መንግሥት ሤራ እንዳይጠምቅ ማድረግ ግን የሚቻል አይደለም፡፡

ከትሕነግ ጋር በሚደረግ ውይይት እሱ ከሚያስተዳድረው አውራጃ ውስጥ ያለውን ሥጋት መቅረፍ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያን ሥጋትና አለመረጋጋት ግን ማሳደግ እንጂ ዝቅ ማድረግ አይቻልም፡፡

ከዚህ ድርጅት ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት አጥፊው ማተረፍ የሚወደው መንግሥት የክተት ዘመቻውን አቁሞ ወደ ወደ ችግኝ ተከላ የሚመለስበትን እድል መፍጠር ይቻለው ይሆናል፡፡ በሌላ መልኩ ግን ህውሓትን የስምምነቱ ተገዥ አድርጎ አገራዊ ችግርና መከራ እንዳያከፋፍል ማድረግ የሚቻል አይደለም፡፡

በፖለቲካዊ ድርድር ከትሕነግ ጋር ስምምነት ፈጥረው በአገር ሕልውና ላይ የሚዶልቱ፣ ሽብርን እና የእርስ በእርስ ግጭትን የሚጠምቁ፣ አገርን እያፈረሱ ቪላ የሚቀልሱ በርካታ ማፊያ አመራሮች በየክልሉ እንዲፈለፈሉ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ትሕነጎችን ከሽብር ጎዳና አውጥቶ በአገር ልማት ላይ ተሳታፊ ማድረግ የሚቻል አይሆንም፡፡

በድርድር ሥም ዘመቻውን በማጓተት ህውሓትን ለመደምሰስ ስንቁን እና ትጥቁን ይዞ የወጣው ሕዝባዊ ጦር በትግሉ ተሰላችቶ ወደ ቤቱ እንዲመለስ ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ‹‹ድርጅቴን ሳላፈርስ ወይም አገሬን ሳላፈርስ ወደ ቤቴ አልመለስም›› ብሎ የወጣውን የሽብር ሠራዊት በሰጥቶ መቀበል መርሕ ጥያቄውን ፈትቶ ከተልዕኮው ማናጠብ አይቻልም፡፡
በፖለቲካዊ ድርድር መንግሥትን እንደ ህውሓት አገር አጥፊ ማድረግ ወይም ደግሞ በሽብር ቡድኑ ጠፊ የሚሆንበትን እድል መፍጠር ይቻላል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በጠረጴዛ ውይይት ጥርሱን ሸርፎ ካደገበት የሤራ ፖለቲካ ጁንታውን ነጻ ከማውጣት ይልቅ እባብን እርግብ ማድረግ ይቀላል፡፡

እንደ አጠቃላይ ህውሓት ጋር በሚደረግ ስምምነት እንደ አገር ይቅርና እንደ ድርጅት ደብረ ጽዮንን እና ፕሬዝዳንት ሐጂ አወል አርባን፣ ተመስገን ጥሩነህን እና ጌታቸው ረዳን፣ ፕሬዝዳንት ሙሥጠፌን እና ጄኔራል ጻድቃንን አብሮ ማስኬድ የሚቻል ባለመሆኑ አጋር ድርጅት ቀይሮ በሌላ አይነት አሰላለፍ ግጭትን ማስቀጠል አንጂ የሰላም አየር የምትተነፍስ አገር እውን ማድረግ የሚቻል አይደለምና ወሎን የሚያራቁተው አሸባሪ ወደ ሸዋ እስኪመጣ በመጠበቅ ፈንታ ወደ እሱ መገስገስ ይበጃል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ!

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top