Connect with us

በሴራና በሸር የተሞላው የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ከበፊትም የነበረ ነው፤ አዲስ ክስተት አይደለም!

በሴራና በሸር የተሞላው የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ከበፊትም የነበረ ነው፤ አዲስ ክስተት አይደለም!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

በሴራና በሸር የተሞላው የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ከበፊትም የነበረ ነው፤ አዲስ ክስተት አይደለም!

በሴራና በሸር የተሞላው የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ከበፊትም የነበረ ነው፤ አዲስ ክስተት አይደለም!

(ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ)

  ዊሊያም ብሉምን(William Blum) የምታውቁት ታውቁታላችሁ። ስለዚህ ፀሐፊና ሥራዎቹ መረጃ ለሌላችሁ ካነበብኩት በጥቂቱ ላካፍላችሁ።

  ይህ ሰው በዜግነቱ አሜሪካዊ ነው፤ ከ3 ዓመታት በፊት ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው! ብሉም አሜሪካዊ ቢሆንም በሕይወት ዘመኑ  አሜሪካ በሌሎች ሀገራት በስመ ሰብዓዊ እርዳታና ዲሞክራሲ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቆ ሲቃወም የነበረ ፀሐፊ ነው። 

ብሉም ከፀሐፊነት ውጪ በIBM የኮምፒውተር ፕሮግራመርም ሆኖ ሰርቷል፤ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ውስጥ በነበረበት ወቅት የአሜሪካን የቬትናም ወረራ በፅኑ ስለመቃወሙ ይነገርለታል። አሜሪካዊ ሆኖ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የሳለ ሂሱን በተደጋጋሚ ከማቅረብ ባለፈ በርዕሰ ጉዳዩ ገራሚ መፅሐፍትን ደርሶ አስነብቧል  ።

   ዊሊያም ብሉም ከፃፋቸው መፅሐፍት ውስጥ እ.ኤ.አ.በ2005 ዓ.ም. የተፃፈው “Rogue State” መፅሐፍ አንዱ ነው። በዚህ መፅሐፉ ብሉም በሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲ ተቋሪቋሪነቷ ወደር የለኝም በማለት የምትመፃደቀውን ሀገሩን አሜሪካ እርቃኗን አስቀርቷታል ማለት ይቻላል። ይህን መፅሐፍ ያነበበ ሁሉ አሜሪካ በሌሎች ሀገራት በሰብዓዊ ጣልቃ ገብነት ሰበብ የምትፈፅመውን ግፍና በደል በግልፅ ማጤን ይችላል። 

መፅሐፉን ካነበቡት ውስጥ አንዱም ኦሳማ ቢን ላደን ነው። ቢን ላደን የብሉምን መፅሐፍ አንብቦ እንደጨረሰ ለአሜሪካኖች መልዕክት አስተላልፎ ነበር፦”እባካችሁ አሜሪካኖች ይህን የሀገራችሁ ተወላጅ ስለ መንግስታችሁ ቅሌት የፃፈውን  መፅሐፍ አንብቡት” በማለት። በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ዊሊያም ብሉም አሜሪካ በኢራቅ ላይ እርምጃ መውሰዷን የተቃወሙ መምህረን ላይ የወሰደችውን እርምጃ ለዓለም አሳውቋል፤ የሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ ዲሞክራሲያዊ መብት ካልተከበረ ሞቼ እገኛለሁ የምትለው አሜሪካ በራሷ ሀገር ውስጥ ያሉ መምህራን የኢራቅን ወረራ በተቃወሙበት ቅፅበት ምላሿ የተቃወሙትን በሙሉ ከሥራ ማባረር ነበር። 

ሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ድርጊት ቢፈፅሙ ኖሮ ለውግዘቱ የአሜሪካ መንግስትን የሚቀድማት አይኖርም ነበር። በኋላም  ድህረ-አሜሪካ ወረራን ተከትሎ ኢራቅ ውስጥ በተከሰተው ቀውስ አሜሪካ ሀፍረትን መከናነቧ አይዘነጋም፤ ወረራው ፈፅሞ መከወን የሌለበት ስለመሆኑ 44ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበረው ባራክ ኦባማ በሥልጣን ዘመኑም ሆነ ከዚያ በኋላ በግልፅ ተናግሯል…ምንም እንኳን እሱም ሥልጣኑን ከለቀቀ በኋላ የተፀፀተበትን  የሊቢያ ወረራን በመምራት ተመሳሳይ ስህተት መፈፀሙ እውን ቢሆንም!

  የዊሊያም ብሉም ሁለተኛው መፅሐፉ “Killing Hope U.S. Military and CIA Interventions Since World War II” ነው፤ ለንባብ የበቃው እ.ኤ.አ. በ2003 ዓ.ም.ነው። በዚህ መፅሐፉ ውስጥ ብሉም በተለይም በአፍሪካና ላቲን አሜሪካ ውስጥ ያሉ ሀገራት በራሳቸው ተነሳሽነት በሕዝብ በተመረጠ መንግስት ዲሞክራሲንና ልማትን ለማስፈን በሚጥሩበት ወቅት አሜሪካ እንዴት ጣልቃ እየገባች አምባገናንና ለእሷ ታዛዥ የሆኑ አሻንጉሊት መንግስታትን እየመሠረተች ተስፋቸውን እንደምታጨልም በሰፊው ያብራራል…Killing Hope..የሚለው ርዕስ የሚያመለክተው ይህንኑ ነው። በመፅሐፉ ውስጥ ሕልማቸው በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት የጨነገፈባቸው ከ50 በላይ ሀገራት ተጠቅሰዋል። 

በዚህ መፅሐፍ በምዕራፍ 54 ላይ ከኤል ሳልቫዶር ጦርነት ጋር በተያያዘ  የሀገራችን የኢትዮጵያ ስም ተጠቅሷል። የተጠቀሰችበት ምክንያት ይህ ነው፦ እ.ኤ.አ. ከ1980-1984 ባለው ጊዜ በአሜሪካ የሚደገፈውን አምባገነኑን የኤልሳልቫዶር መንግስትን የሚዋጉ ሾምቅ ተዋጊዎች ነበሩ። በዚህ ውጊያ የኒካራጓ ዜግነት ያላቸው ተዋጊዎች ሽምቅ ተዋጊዎቹን ያግዙ ነበር፤ ታዲያ በጦርነቱ መካከል አንድ ኒካራጓዊ ሽምቅ ተዋጊ ተማርኮ ቃለመጠይቅ ሲደረግለት ሥልጣናውን የወሰደው ኢትዮጵያና ኩባ ውስጥ መሆኑን ይፋ አደረገ…በመንጌ ዘመን መሆኑ ነው።ብዙውን ጊዜ  በንጉሡ የአመራር ዘመን ኢትዮጵያ መጥቶ ሥልጠና ስለመውሰዱ የሚነገረው ኔልሰን ማንዴላ ነው፤ ኒካራጓዊው ሽምቅ ተዋጊ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጠና ወስዶ ኤል ሳልቫዶር ውስጥ እንደተፋለመ የምናውቅ ስንቶቻችን እንሁን?

 በነገራችን ላይ በጦርነቱ ወቅት የአሜሪካ ሚዲያዎች አምባገነን ሥርዓትን ለመገርሰስ የሚደረገውን ትግል ለማኮላሸት ልክ እነ CNN በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ላ ላይ አንደሚያደርጉት የሐሰት ዜናዎችን ፈብርከው ያሰራጩ ነበር። ለዚህም በዋቢነት እ.ኤ.አ. በ1988 ዓ.ም. በኒው ዮርክ ታይምስ በአሜሪካ የሚደገፈውን አምባገነን መንግስትን ይቃወሙ ስለነበሩ ስለ ሽምቅ ተዋጊዎች የተዘገበው ይህን ይመስላል፦

“Villagers say guerrillas publicly executed two peasants … because they had applied for and received new voter registration cards. According to the villagers, the guerrillas placed the voting cards of [the two men] in their mouths after executing them as a warning to others not to take part in the elections.”

እንግዲህ በዚህ ዘገባ ኒው ዮርክ ታይምስ ሽምቅ ተዋጊዎቹ በኤል ሳልቫዶር መንግስት በተዘጋጀው ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርዱን የወሰዱትን ሁለት ገበሬዎችን ካርዱን አፋቸው ውስጥ እንዲከቱ ካደረጉ በኋላ እንደረሸኗቸው አድርጎ ዜና ሰርቷል። ይህ ዜና  በቀጥታ ለአሜሪካ ኮንግሬስ ከተላከ በኋላ ኮንግሬሱ ሽምቅ ተዋጊዎቹን በ“campaign of intimidation and terrorism”. ለመክሰስ ሰበብ አገኘ። እነ Times ደግሞ ዜናውን ተቀባብለው አራገቡት።

እውነታው ግን ይህ ነበር፦

“But the story, it turned out, was the invention of a Salvadorean Army propaganda specialist who had placed it in the San Salvador newspaper El Mundo. From there it was picked up by the New York Times reporter who gave the impression that he had interviewed villagers with firsthand knowledge of the incident, instead of attributing the story to the military as had El Mundo.The Times later recanted the story.  “

  በአጭሩ የኒው ዮርክ ዘገባ ምንጩ የኤል ሳልቫዶር መንግስት ነበር። ምንም እውነታ የሌለው ለፕሮፖጋንዳ ብቻ ተፈጥሮ ኤል ሙንዶ በተባለ በሀገሪቱ ጋዜጣ የተሰራጨ አሉባልታ ነበር። እንግዲህ በኒው ዮርክ ታይምስ፤ በታይምስና ከፍ ሲልም  ኮንግሬሱ ድረስ የዘለቀው ይህ ክስ ሙሉ በሙሉ የፈጠራ ወሬ ነበር። ታይምስ ቆይቶ ዜናው ፈጠራ መሆኑን ካጣራ በኋላ “አፉ በሉኝ፤ ስለ ሽምቅ ተዋጊዎቹ ያሰራጨሁት ዜና የሐሰት ነው” በማለት ንስሃ ገብቷል።

 የሰሞኑ የCNN በፎቶ የተደገፈው የ”አዲስአበባ ተከብባለች” የፈጠራ ወሬ ከኤል ሳልቫዶሩም ሳይብስ ይቀራል? CNN እንደ ታይምስ “አፉ በሉኝ” ይል ይሆን? ማነው ከባቢው? ማነው ተከባቢው? ያለው ማን ነበር?

  ለማንኛውም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መዲና በአዲስ አበባ ከተማ አሸባሪዎችንና የአሜሪካ የተለመደውን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል። USA SHOULD NEVER BE ALLOWED TO KILL OUR HOPES!

ማሳሰቢያ፦  ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለቱም መፅሐፍት በፒ ዲ ኤፍ ጎግል ላይ አለላችሁ። በርዕሱ አፈላልጋችሁ ዳዎንሎድ ማድረግ ትችላላችሁ።

ሰናይ ሰንበት

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top