Connect with us

እንደ ጎጃም እስክስታ በሚንቀጠቀጥ ድምጽ ኮንቴነር ውስጥ ሆኖ የሚዝተው ዶክተር ደጺ

እንደ ጎጃም እስክስታ በሚንቀጠቀጥ ድምጽ ኮንቴነር ውስጥ ሆኖ የሚዝተው ዶክተር ደጺ

ነፃ ሃሳብ

እንደ ጎጃም እስክስታ በሚንቀጠቀጥ ድምጽ ኮንቴነር ውስጥ ሆኖ የሚዝተው ዶክተር ደጺ

እንደ ጎጃም እስክስታ በሚንቀጠቀጥ ድምጽ ኮንቴነር ውስጥ ሆኖ የሚዝተው ዶክተር ደጺ

(አሳዬ ደርቤ- ለድሬ ቲዩብ)

አንዱ የህወሓት ወታደር ልብን የምትሰውረውን ጭስ ነፍቶ እየተዋጋ ሳለ በመከላከያ ሠራዊታችን ይማረካል፡፡ ትጥቁን አስረክቦ እንደሱ ከተማረኩ ጥቂት እድለኛ ጓዶቹ ጋር ቁጭ ብሎ ሳለም፣ ድንገት ከመቀመጫው ተነስቶ የማረኩትን የሠራዊት አባላት እንዲህ አላቸው፡፡

‹‹በሁሉም አቅጣጫ ስለከበብኳችሁ መሳሪያችሁን ጥላችሁ እጅ ስጡ››

 ዶክተር ደብረ ጽዮንም ከሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ላይ ያቺን እጽ ጢጥ ያደረገ ይመስል ድምጹ እንደ ጎጃም እስክስታ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ንግግሩም እርስ በእርሱ የሚጣረስና ፈገግታን የሚለግስ ነበረ፡፡ ለማስረጃም ያህል፡-

መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም አድርጎ ጦሩን ከመቀሌ ሲያወጣ ‹‹የተኩስ አቁሙን አንቀበልም›› በሚል እብሪት መከላከያ ሠራዊቱን ተከትሎ በአፋርና በአማራ ክልሎች ላይ ወረራ መፈጸሙን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያስታውሰው ሐቅ ቢሆንም፣ ዶክተር ደብረ ጽዮን ግን የማስታወስ ችሎታውን የሚነጥቅ አደጋ የደረሰበት ይመስል ሰሜን እዝን ወግቶ ጦርነቱን መጀመሩንና በተኩስ አቁሙ ላይ ተሳልቆ ወረራ መፈጸሙን ክዶ ‹‹ወደዚህ ጦርነት የገባነው መንግሥት የሰላም ጥሪያችንን ሊቀበል ባለመቻሉ ነው›› እያለ ሲናዘዝ ይሰማል፡፡

በማስከተል ደግሞ በመጀመሪያው ዙር ጦርነት ‹‹የትምክህት ሃይሎችን እንቀብራለን›› በሚል ፉከራ፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ ‹‹የአማራ ልሂቃን ላይ የምናወራርደው ሒሳብ አለን›› በሚል ሽለላ አማራ ክልል ላይ ጥቃትና ወረራ የፈጸመው….. የማይካድራን የቆቦን እና የጪናን ንጹሐን የጨፈጨፈው…. ጠላቴ የሚለውን ሕዝብ እንደ ጠላቱ የሚቆጥር ድርጅት ፈልጎ ከኦነግ ጋር ጥምረት የፈጠረው…… ደብረ ታቦርን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የመድፍ አረር ሲጥል የነበረው…. እራሱ ህውሓት ሆኖ ሳለ የሽብር ቡድኑ ፕሬዝዳንት ግን ‹‹ይህ ጦርነት አማራንና ትግራይን ለማጨፋጨፍ ሆን ብሎ የተለኮሰ ነው›› በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ የሽብር ቡድኑ በሰሜን ወሎ፣ በጎንደር የፈጸመውን ውድመት ደቡብ ወሎ ላይ (ደሴና ኮምቦልቻ) መድገም ሲያስብ ከመከላከያ ሠራዊቱ ባለፈ ያልታሰበ ሕዝባዊ ጦር አጋጥሞት በየትኛውም ግንባር ያልታዬ እልቂትና ሽንፈት ማስተናገዱ የሚታወቅ ቢሆንም የማሰብ ቀርቶ የማንበብ ችሎታውን የተነጠቀው ዶከተር ደብረ ጽዮን ግን በንባብ የሰጠው መግለጫ ‘ድል ከጨበጠ’ እንጂ ‘የሽንፈት ጽዋን ከጨለጠ’ አካል የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ በመሆኑም የድሮን ጥቃት ሽሽት የሚያቃጥል ኮንቴነር ውስጥ ተቀምጦ ‹‹ሥልጣን ላይ ያሉት ሃይሎች አገር ለቅቀው ወደ ሌላ አገር ቢሄዱ እንኳን አያመልጡንም›› እያለ ይዝታል፡፡

የሽብር ቡድን መሪ መሆኑን እረስቶ እንደ አገር መሪ ለክልሎችና ለብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆን ለመከላከያ ሠራዊቱም ጭምር  ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ወረራ ፈጽሞ በከባድ መሳሪያ ቅንቡላ የሚያሸብረውን የወሎን ሕዝብ ‹‹ቤትህ ውስጥ አርፈህ ቁጭ በልልን›› ብሎ ከለመነው በኋላ፣ ዝቅ ብሎ ደግሞ ‹‹ከተማህን አጽድተህ ለዘረፋ ምቹ አድርግልን›› በሚል ትዕዛዝ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ውጊያ እንዲገጥም ያሳስበዋል፡፡

ለአማራ ሕዝብ ‹‹ይህ ውጊያ የዐቢይ እንጂ የህልውና አይደለም›› ብሎ ከተነናገረ በኋላ ለመከላከያ ሠራዊቱ ደግሞ ‹‹ይህ ጦርነት የጥቂቶች ህልውና ማስቀጠያ እንጂ አገርን የሚመለከት ስላልሆነ ለትምክህት ሃይሎች ብለህ ሕይወትህን ከምትሰዋ ውጊያው ማለቁን አውቀህ እጅህን ስጥ ወይም አምልጥ›› የሚል የጅል ምክር ይለግሳል፡፡

‹‹ውጊያው በእኛ አሸናፊነት አልቋል፤ የዐቢይ መንግሥትም አብቅቶለታል›› ብሎ ከተናገረ በኋላ ደግሞ ‹‹የዚህ ጦርነት መነሻ ፖለቲካዊ ስለሆነ መፍትሔውም ፖለቲካዊ ነው›› ይልና ካንኮታኮተው የዐቢይ አስተዳደር ጋር ድርድር የሚያደርግበትን መንገድ ያመቻቹለት ዘንድ ብሔር ብሔረሰቦችን ይለምናቸዋል፡፡

 እንዳጠቃላይ ግን የደብረ ጽዮን እርስ በእርሱ የሚጣረስ ብሎም ኢትዮጵያን እርስ በእርስ ለማጫረስ የሚሞክረው የጅል መግለጫ በስንኝ ሲገለጽ እንዲህ የሚል ነው፡፡

አንተ የአማራ ሕዝብ

ለዐቢይ ስልጣን ብለህ ፥ በከንቱ ከምታልቅ

ፋኖን መልስና፥ ለእኛ ታጣቂዎች፥ ከተማህን ልቀቅ

ሠራዊቱም ብትሆን

ለትምክህት ሃይል ብለህ ፥ ነፍስህን ከምትሰጥ

ወይ ተማረክልን ፥ ወይም ሸሽተህ አምልጥ

እናንት የኢትዮጵያ ፥ ብሔረሰብ ሁሉ

መንግሥትን ጣሉና ፥ እኛን ተቀበሉ

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top