Connect with us

ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች

የእያንዳንዱ ትህነግ ስኬት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደሆነው ሁሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህይወት ግብ ደግሞ ኢትዮጵያን ማዳን ነው፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች

ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች

 ( እስሌማን ዓባይ)

“አየር መቃወሚያ አዘጋጅተን ብንጠብቃቸውም  የኢፌድሪ ጄቶችን ለመምታት ራቁብን” ሲል ለሮይተርስ የተናገረው የህወሃት ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳ ነው።ጌታቸው ረዳ የጀነራል ይልማ መርዳሳ ንስሮችን አያውቃቸውም። ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ሌላ ሊጠቁመው የፈለገ ነገር አለ ከተባለም ንስሮቹን ማወቅ የጀመረው ቀድሞ ሳይሆን ማድቀቅና መውቀጣቸውን ከተመለከተ በኋላ ነው ማለት ነው። ጌቾ ንስሮችን በርግጥም አያውቃቸውም።

ለነገሩ ጌቾ እንኳን ጄቶቹን በምኒስትርነት የመራት ኢትዮጵያን ቢያውቃት ኖሮ ይህን ሁሉ ባላየና ባላሳየንም ነበር። ከረፈደ…ሆኖ እንጂ ጌቾ ምን ይዞ ማንን እንደሚዋጋ ቀዳሚ የቤት ስራውን ሰርቶ ቢሆን ኖሮ አያዋጣኝም ብሎ በተቀመጠም ነበር።

ኢትዮጵያ አየር ኃይል ሄልኮፕተሮች፣ ድሮኖችና ሌሎች በራራ ይዞታዎችን አቆይተናቸው ጄቶችን ብቻ ከይፋዊ ወታደራዊ ድረገፆች ላይ ብንመለከት F-16V፣ MiG-23፣ SU-27፣ SU-30፣ J10C ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚህ ባለፈም በ2020 እኤአ ለመረከብ ቀድሞ የተፈረመበት Mig35 እና ከአመት በፊት የታዘዘው Su-57 ሲጠቀሱ ከሚስጥራዊ ሞዴሎችም ጋር ታሳቢ ማድረግ የአገራችን ስትራቴጂክ ሐብት ጋር ድብቅ አቅምንም መገንዘብ ግድ የሚል ነው።

እስቲ አንዱን ጄት ብቻ እንመልከት። በመቀሌና በዙሪያው ድብደባ ስለመፈፀሙ በአለማቀፍ የዜና አውታሮች የተጠቀሰውን ራሺያ-ሰራሽ ጄት ብቻ እንመልከተው።

SU-27 ወይም Flanker መጠሪያዎቹ ናቸው። የአየር ላይ የበላይ ተዋጊ በሚል ድፍን አለም ያውቀዋል። የጦር ጄቱ ዋና ዲዛይነር የሆኑት ሚካኤል ሲሞኖቭ የ 20ኛው ክፍለ ዘመን ምርጡ የአየር-የበላይነት መድረክን እንዲቆናጠጥ አድርገው እንደቀረፁት ይገለፃል። ጥንድ ቱርቦፋን ሞተሮቹ ኃያል ጉልበት ለግሰውት፣ ዲዛይኑ ደግሞ አስደማሚ ቅልጥፍናን አላብሶታል፤ ከድምጽ ፍጥነት እጥፍ በላይ ተወንጫፊ አድርጎታልም። በ18,000 ሜትር ከፍታ ላይ ግልጋሎት የሚሰጥ ሲሆን ከ3,000 ኪሜ በላይ ያልተገደበ በረራ የማድረግ አቅም አለው።

SU-27 ዘመናዊ የመሳሪያ ትጥቅ ተሸካሚ ሲሆን በራዳር የሚመሩ ኢንፍራሬድ ሆሚንግ ሚሳይሎች (“ሙቀት አነፍናፊ”) ከአየር ወደ አየር ሚሳኤሎች እንዲሁም፣ ከአየር ወደ መሬት ተተኳሽ ሮኬቶች፣ መደበኛ ቦምቦች እና ሌሎችንም ትጥቆችን በአስር ክፍሎቹ ላይ አንከብክቦ የሚዘምት ሲሆን፤ ከአየር ወደ አየር ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን፤ R-27R1 ራዳር ሆሚንግ እና R-27T1 መካከለኛ ርቀት ሚሳይሎች በዚሁ ዝርዝር ውስጥ ይካትታሉ። ኢንፍራሬድ ሆሚንግ እና ተተኳሹ ከ500M እስከ 60KM ድረስ መምታት ሲችሉ፤ ለቅርብ ርቀት ከአየር ወደ አየር ኢላማዎችን ደግሞ ከኢንፍራሬድ ሆሚንግ ጋር ከ300ሜትር እስከ 20KM አነፍንፎ ያወድማል።

ከአየር ወደ ምድር ኢላማዎቹ ባለ100kg, 250kg,  500kg, 25kg, እና ሌሎች 7 አይነት ተተኳሾችን ይይዛል።

ሱ-27 የመከላከል ርምጃ ለመውሰድ ዘመነኛ ኤሌክትሮኒክስ ጃመር፣ ወደፊትና ወደ ኋላ አቅጣጫዎች የሚቃኝ የቡድንና ለራሱ መጠበቂያ የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለታል። የኢንፍራሬድ ማጭበርበሪያ Jammer ማሰራጫና ሌሎች ባለብዙ ሞድ ጃመሮችም በተመሳሳይ…።

የSU-27 ራዳር ቴክኖሎጂ 3m² አንግል ላይ ለሚገኙ ኢላማዎች ከ100 ኪሜ ርቀት በላይ መቃኘትና ማጥቃት ያስችለዋል። ወደፊትና ወደ ኋላ አቅጣጫዎች ደግሞ 40KM ድረስ ዒላማው እንደሚገኝበት የእይታ አንግል አስሶ የማጥቃት ግዴታውን መወጣት ያስችሉታል።

ስጋቶችን ማነፍነፍና መጠነ ስጋታቸውን መገመት በራሱ የሚወጣው ብቃቱ ሲሆን መምታት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለኢላማዎቹ ቅደም ተከተል ያስቀምጥና፣ 10 ኢላማዎችን በአንድ ጊዜ ማውደም ብቃቱ ነው።

የሬዲዮ መገናኛ ቴክኖሎጂው በቡድን አጋር አውሮፕላኖችና ከምድር የሚገኙ ጣቢያዎቹ ጋር በ VHF/UHF ሞገድ ይገናኛል። ይኸውም እስከ 1,500 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ መረጃ መለዋወጥ ያስችለዋል።

ታዲያ ጌቾ ይህን እንዴት ነበር ለመምታት ያሰበው? የነሱ የነበሩ ሚሳይሎች ቀድመው ተመተዋል። አሁን የያዙት አየር መቃወሚያ በርካታ አስርት አመታት ያስቆጠሩ የአማፂ መሳሪያዎች ናቸው። የተሻለ የሚባለው ደጋግመው በፎቶ የሚያሳዩት ከሰው ትከሻ ላይ የሚተኮስ Manpad ሚሳይል ነው። Stinger ይባላል። ውድ ነው። አቅራቢዋ አሜሪካ ናት። ይሁንና እሱ Stinger ከ 5KM በላይ መጓዝ አይችልም።

SU-27 ሆዬ 100KM ላይ ኢላማውን አረጋግጦ ሚሳይልና ቦምቦቹን አራግፎለት ተመልሷል። በዚህ ቅፅበት የጌቾ ሰዎች ፍንዳታ እና እሳትን እንጂ SU-27 መምጣቱንም ማወቅ አይችሉም። ጌቾ ፍንዳታውን በተመለከተ ቅፅበት ጄቱ ሚሳይሉን ካስወነጨፈበት የ 100KM ርቀት አፍንጫውን ወደ ደብረ ዘይት መልሶ ከድምፅ ሁለት እጥፍ በላይ ተወንጭፎ ወደ ጦር ሰፈሩ ለማረፍ የሚቃረብ ይሆናል።

አዎ..! ጌታቸው ረዳ የጀነራል ይልማ መርዳሳ ንሥሮችን አያውቃቸውም..!

   የዓባይ፡ልጅ – Esleman Abay

ማስታወሻ;- መረጃው ሚስጢራዊ ጉዳዮች አልተካተቱበትም። ሙሉ መረጃዎቹ በዬስልካችን/GOOGLE ላይ ሚሊቴሪ ዌብሳይቶች በይፋ ያሰቀመጧቸው ናቸው።

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top