Connect with us

ጭፍራ ላይ ተዝለፍልፎ የቀረው የህወሓት ጭፍራ

ጭፍራ ላይ ተዝለፍልፎ የቀረው የህወሓት ጭፍራ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጭፍራ ላይ ተዝለፍልፎ የቀረው የህወሓት ጭፍራ

ጭፍራ ላይ ተዝለፍልፎ የቀረው የህወሓት ጭፍራ

(አሳዬ ደርቤ~ ለድሬ ቲዩብ)

በአፋር በኩል የዘመተውን አሸባሪ ቡድን የሚመራው ጄኔራል ታደሰ ወረደ ጭፍራን አሻግሮ ባዬ ጊዜ፡-

ጭፍራ ማዶ ሆኜ፥ ዐይኔን ባሻግረው

ታየኝ ገመገሙ፥ አራት ኪሎ ግቢው

እንደምነሽ ሸገር፥ የድሮዋ ቤቴ

ዳግም ላስገብርሽ፥ አልቀረም መምጣቴ›› በማለት ፎከረ፡፡

በማስከተልም ከስሩ ያለው የእዋን መንደር በከባድ መሳሪያ እያስደበደበ ‹‹በትግል ዘመኔ እንዲህ ያለ ጣፋጭ ድል ዐያለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም ነበር፤ ሆኖም ግን ያልታሰበው ሆኖ የጅቡቲን አስፓልት ብቻ ሳይሆን የአራት ኪሎንም ቤተ-መንግሥት ለመቆጣጠር የምታስችለውን የጭፍራ ከተማ ከብዙ ምርኮ ጋር ተቆጣጥሬያለሁ›› የሚል ፕሮፖጋንዳውን ነዛ፡፡

ጌታቸው ረዳም ይሄንኑ ሪፖርት ተቀብሎ የፌስቡክን እና የትዊተርን መንደር በድል ዜና ሲያደምቀው አመሸ፡፡ ‹‹አዲስ አበባ ገብተን ትግሉን ለማጠናቀቅ ከአንድ ሳምንት በላይ ሊፈጅብን አይችልም›› የሚል ብሽከታውንም ነዛ፡፡

ትከሻቸው ላይ ክላሽ፣ ከንፈራቸው ስር ሲዋክ የማይታጣው የአፋር ጀግኖችም ይሄን ሲሰሙ ከብቶቻቸውንና ግመሎቻቸውን ለልጆቻቸውና ለሚስቶቻቸው አስረክበው ግመል በጥይት የሚገድለውን አረመኔ ቡድን ለመደምሰስ የሽማግሌ አባቶቻቸውን ምርቃት ተቀብለው ወደ ጭፍራ ገሰገሱ፡፡

ቦታ ቦታቸውን ከያዙ በኋላም መሟጫቸውን በጥርሳቸው ነክሰው፣ ክላሻቸውን ከትከሻቸው አውርደው እንዲህ እያሉ ወደ ጭፍራ የገባውን ወራሪ ያስጨፍሩት ጀመር፡፡

‹‹የእርዳታ ስንዴህን ፥ በክብር በሸኘን

ግመልና ፍየል ፥ አርብተን በኖርን

ይሄው ሕይወት ሆኖ፥ መቀመጫ ካጣን

ከእንግዲህ እርም ነው፥ አውድሞ መመለስ

በል ይሄን ጠጥተህ፥ አፈርህን ልበስ›› እያሉ እርሳሳቸውን ያርከፈክፉት ያዙ፡፡

ዒላማውን በማይስት የጥይት ካፊያ ውስጥ የወደቀው የሽብር ሠራዊትም፡-

ካለፈው ስህተቴ- ካለፈው ሽንፈቴ

ተምሬ ልቀር ስል- ጨካኝ ድርጅቴ

ጠርንፎኝ ነውና- ከምድርህ መምጣቴ

አፋር ወንድሜ ሆይ-

ዳግም ማረኝና- ልሂድ ወደ ቤቴ›› እያለ ቢማጸንም የአፋሮች መልስ ግን እንዲህ የሚል ነበር፡፡

‹‹ያ የሳር ጎጆ ቤት…

በከባድ መሣሪያ- መትተህ ያቃጠልከው

ከውስጡ የተኛ- ጡት ያልጣለ ሕጻን- አራስ ልጅ ነበረው፡፡

እናም እልኻለሁ…

የልጅ ደም አፍስሶ- ጎጆ ቤት ለኩሶ፤

ሃራም ነው በእኛ ዘንድ

የእጅን ሳያገኙ- መሄድ ተመልሶ፡፡››

ከአንድ ቀን ውጊያ በኋላም ጭፍራን ሳይቆጣጠር ሚሌን እና ሸገርን ተቆጣጥሬያለሁ›› ያለው የአሸባሪ ቡድን መሪ ወደ ሞስኮቭ ተሸግሮ በብርድ እንዳለቀው የናፖሊዮን ጦር በሙቀትና በጥይት የሚረግፈውን ሠራዊቱን ሲመለከት ፍርሐቱን መቆጣጠር ተስኖት ወደኋላ ይፈረጥጥ ጀመር፡፡

ፉከራው መክሸፉን የሰማው ጌታቸው ረዳም ገና በጧቱ ብረታ ብረቱን እየተጎነጨ መቀሌ ላይ በመቆዘም ላይ ሳለ ሁለት የቆርቆሮ ወፎች ሞሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካና ፕላኔት ሆቴል አካባቢ በትራቸውን አሳርፈው ወደመጡበት ሲመለሱ አየ፡፡

ድንጋጤው ካለፈለት በኋላም ‹‹የኢትዮጵያ አየር ሃይል ገበያ መሃከል ላይ በጣለው ቦንብ ሦስት ንጹሐን ተገድለዋል›› የሚል ፖስት ለጠፈ፡፡

‹‹ቦንቡ ገበያ ላይ ከተጣለ የተጎጂዎች ቁጥር እንዴት ሦስት ሰው ብቻ መሆን ቻለ?›› ተብሎ በተጠየቀ ጊዜም የሰጠው መልስ እንዲህ የሚል ነበር አሉ፡፡

‹‹አብዛኛው ሕዝባችን ወደ ወሎ ስለሄደ ገበያው ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሦስት ነበሩ›› ክክክክክ

ድል ለኢትዮጵያ!

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top