Connect with us

የእያንዳንዱ ትህነግ ስኬት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደሆነው ሁሉ…..

የእያንዳንዱ ትህነግ ስኬት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደሆነው ሁሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህይወት ግብ ደግሞ ኢትዮጵያን ማዳን ነው፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የእያንዳንዱ ትህነግ ስኬት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደሆነው ሁሉ…..

የእያንዳንዱ ትህነግ ስኬት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደሆነው ሁሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የህይወት ግብ ደግሞ ኢትዮጵያን ማዳን ነው፤

ይልቅ የራሄል ዮሐንስን “የአየር ኃይሉ ጀግና” ሙዚቃ ለአየር ኃይሉ ጋብዙልን?!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ትህነግ መሬት ላይ ነበረች መሬት ያወረዳትና መሬት ያንከራተታት የስልጣን ዘመኗ ከመሬት ያልተላቀቀ ፍቅር፣ ዝርፊያና አስገድዶ ደፈራ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን አየር ላይም ልጆች አሏት፡፡ እየሆነ ያለውን ነገር ስናስብ የራሔል ዮሐንስን የአየር ኃይሉ ጀግና የሚለውን ሙዚቃ ለአየር ኃይላችን እየጋበዝን ነው፡፡

እያንዳንዱ ትህነግ ስኬቱን ኢትዮጵያን ማፍረስ አድርጓል፡፡ ፕሮፖጋንዳቸው እንኳን ከሚታየው የሚቃረን ተራ የምድር ወንበዴዎች ናቸው፡፡ ያማ ባይሆን ኖሮ ወሎን እያወደሙ ጠቤ ከአብይ አህመድ ነው ብለው ባልቀለዱ ነበር፡፡

ይሄ ጦርነት ባርነትን አልፈልግም ያለ ሃይል ቢያደርገው ልባችንን በከፈለ፣ በጉልበት አልገዛም የሚል ሃይል እንቢኝ ብሎ ቢሺፍትም ባልገረመን፤ ግን አይደለም ትህነግ ባርነት አልፈልግም ብላ ሳይሆን ባሪያ ላድርጋችሁ ከሚል እብሪት ነው ጦር የሰበቀችው፡፡

ትህነግ በጉልበት አልገዛም ብላ ሳይሆን በጉልበት መቶ አመት ገዝቼ መቶ ቦታ ኢትዮጵያን ከፍዬ የዓለም መጫወቻ አድርጌ እከብራለሁ ብላ በመቃዠት ነው ጦር የሰበቀችው፡፡ ጌታቸው ረዳ እንደሚለው የትግራይ እናትን ለመታደግ አይደለም የአማራና የአፋር እናትን ለመግደል ነው፡፡ የትግራይ ሴቶችን ለመጠበቅ አይደለም የአማራና የአፋር ሴቶችን ለመድፈር ነው፡፡ አለም ያየው ገና ነገ ጉድ የሚሰማው እውነትም ይሄው ነው፡፡

እንኳን በየቀኑ በአየር በምድር እያለቁበት ቀርቶ ድል እንኳን ቢያደርጉበት ይሄ ዓላማ ቆሻሻ ነው፡፡ የቆሸሸ ዓላማ ታላቅና ንጹህ ሀገር ድል አድርጎ አያውቅም፡፡ እርግጥ ነው እያንዳንዱ ትህነግ አሁን ማየት የሚፈልገው የኢትዮጵያን ውርደት ሞትና መከራ ነው፡፡ ለዚህም ካገኘው እየተዋዋለ ከአሳደደው እየተማማለ ከገደለው ቀለበት እያሰረ እድሉን መሞከር ቀጥሏል፡፡

ግን ተቃራኒው ነገር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያ ዘብ ከመቆም ውጪ ሌላ የህይወት ግብ የሌለው መሆኑ ነው፡፡ መቶ ሚሊዮን ህዝብ ጥጋብ ባሰከረው ጥቂት አረመኔ ድል አይደረግም፡፡ እውነት ሲወጣ አልያም እልቂቱን ሲደምር የትግራይ ወጣት ለምን ብሎ የሚጠይቅበት ቀን አይርቅም ያኔ የጦርነቱ ባለቤቶችና መሪዎች ምን ዓላማ እንደነበራቸው ይታያል፡፡

የትግራይ ህዝብ ግን ቢያንስ ኮምቦልቻ እያስፈራራ ትግራይ ጓዙን እና ትጥቁን ከአየር ጥቃት ማዳን ያልቻለውን ቀልደኛ እስከመቼ ሊለው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ለብልጽግና አይደለም እየተዋጋች ያለችው፤ ኢትዮጵያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አልያም ለካቢኔያቸው አይደለም ለመሞት የተዘጋጀችው፤ ኢትዮጵያ ለፍትሕ ነው፡፡ ለነጻነት ነው፡፡ በአደባባይ ሲዖል ወርጄ አጠፋሻለሁ ላላትና በህይወት ኖሮ ስትጠፋ ለማየት ስለታቃረብኩ ደስታዬ ወደር የለውም ብሎ ለሚቀባጥረው ትህነግ ምኞት መክሰም ነው የምትዋጋው፡፡

ይሄ ዘመነ ደርግ አይደለም፤ ትህነግ የብሔር መብት ብላ ልታታልል አትችልም፤ ከብሔር መብት መከበር አልፋ የብሔር አባት ነኝ ወደሚል ጭቆና በገባችበት ድሪቶ ፖለቲካ ሳቢያ የከሰረችበት ውጤት ያመጣው ጦርነት ነው፡፡ ትህነግ ወራሪ ሃይሉን እያስጨረሰ ያለው ተንቤንን ጠብቅ ብሎ አይደለም፤ አልያም መቀሌን ለመታደግ አይደለም፤ ወሎን እዘርፋለሁ አፋርን እገድላለሁ ኢትዮጵያን አጠፋለሁ በሚል ዓለም አፉን የዘጋበት ተግባር ፈጽሞ ነው፡፡ እናም የአየር ሃይሉ ጀግና እያልን መዝፈናችንን ቀጥለናል፡፡ 

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top