Connect with us

ባትዋጉ ቢያንስ ያልሆነ ነገር አታውጉ፤

Social media

ነፃ ሃሳብ

ባትዋጉ ቢያንስ ያልሆነ ነገር አታውጉ፤

ባትዋጉ ቢያንስ ያልሆነ ነገር አታውጉ፤
ስልጡኝ ነኝ ካልክ ቲውተር ግባና ሀገር ታደግ!!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
ይሄ ጦርነት አንድም የከበደው ሀገሩን የደገፈ እየመሰለው ጠላት እየመራ የሚያስገባ መንገድ ጠቋሚው በዝቶ ነው፡፡ ፌስ ቡክ ይዞ ግንባር መምራት የሚፈልግ ሞኝ የቱ ጋር ምን ያህል ሃይል እንዳለን ሲጮህ ይውላል፡፡ ጠላት ያለ ሰላይ ከሰካራም አክቲቪስት የፌስ ቡክ ገጽ የቱ ግንባር እንደሚከብደው ቀድሞ ይረዳል፡፡

አንዳንዱ ማኅበራዊ ሚዲያውን ለታላቅ ዓላማ ተጠቅሞ ዓለም ፊት ሀገር ቀና እንድትል ሌት ተቀን በሙያው ይዘምታል፤ አንዳንዱ የዘመተ ተስፋ ለማስቆረጥ የስታሊንን ዜና ያራግባል፡፡

እውነት ለመናገር እንደ በላይ ማናዬ፣ በለጠ ካሳ፣ ጌታቸው ሽፈራሁና ውብሸት ሙላት ያሉትን ጨምሮ ብዙ ወንድሞቻችን በቲውተር አካውንት ሲፋለሙ እውነት ሲያጋልጡ ይውላሉ፡፡ እነ ደረጄ ገርፋ ቱሉ፣ ናትናኤል መኮንን እና ሙክታሮቪች ያለ እረፍት የወያኔን ሀሰት ሲያጋልጡ እዚህ መንደር ደግሞ የወያኔን እውነት ተቀብሎ ከወንድሞቹ ጋር ካልተባላሁ የሚል ሞኝ እያየን ነው፡፡

ከቀናት በፊት አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን “ያስቸገረን አክቲቪስቱ ነው፤ የሰማውን መረጃ ይናገራል፤ እኛ ጠዋት እንዘምታለን ስንል እሱ ምሽት ሲነጋ ጉዳችሁ ይፈላል ብሎ መረጃ ያቀብላል፤ ኦፕሬሽኑ ይከሽፋል፡፡” ሲሉ መናገራቸውን እዚሁ መንደር አንዱ ጽፎት ስንቀባበለው ከርመናል፡፡
መዋጋት ያባት ነው፡፡ ሀገር እኮ ክተት ብላ ጥሪ አቅርባለች ራስን ማዳን በመክተት እንጂ በመወሽከት አይሆንም፡፡ መዋጋት እንኳን ባይቻል ያልሆነ ነገር አለማውጋትም አንድ አስተዋጽኦ ነው፡፡

የመረጃ ምንጩ ስታሊን የሆነ ፌስቡከር ትግራይ ሚዲያ ሀውስን እያየ መንግስት እከሌን አስያዘ ብሎ ወታደር ሊያሽሟጥጥ ይቃጠዋል፡፡ ወታደርማ ሀገሬን ብሎ ከቤቱ ወጥቷል፡፡ ወገኔን ብሎ በየሜዳው እየወደቀ በየሜዳው እየተፋለመ ነው፡፡

እነሱ አሁን በብዙ መልኩ ጦርነት ከፍተዋል፡፡ መቶ ሺህዎቻቸው ያሉት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነው፡፡ በአንተና በስምህ አካውንት ከፍተዋል፡፡ ኦሮሞ መስለው አማራ መስለው ሲዳማ መስለው ሱማሌና አፋር መስለው አጀንዳ ይሰጡሃል፤ ያንን ይዘህ ከቤትህ ሳትወጣ ሀገር የሚያምስ ወሬ ታተራምሳለህ፡፡ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ የህግ ባለሙያው ውብሸት ሙላት ጀግና ከሆንክ ትህነግ የሰራችውን ወንጀልና አረመኔያዊ ድርጊት በማኅበራዊ ሚዲያ ለዓለም አድርስ ጦርነቱን ግንባር ላለው ተወው ብሏል፡፡

ወታደር የሚያስፈልገው ስንቅና ትጥቅ ነው፡፡ ወሬ ግንባር ላለ እና ሀገሬን ላለ ወገን ጦር ቢሸሽም ቢፋለምም አንዳች የሚረባው ነገር አይደለም፡፡ ይልቁንም እዚህ ቦታ ሃይል የለም እያሉ መረጃ በመስጠት ጠላት የመምራቱ አሳፋሪ ያላዋቂነት በቃ ካልተባለ መጨረሻው ሀገር ማጥፋት ነው፡፡

እነሱ ድል ተመተው ድል ማድረግን ይስባካሉ፤ በሰፈራቸው አልያም በፓርቲያቸው ወይም በአላማቸው ምክንያት ልዩነታቸውን በጦርነት ሰዓት አደባባይ ይዘው አይመጡም፤ የጋራ ሀገር እንገንባ የሚል እንዴት ሀገር ላፍርስ ከሚል ያነሰ ሚና ይጫወታል?

ጉዳዩን ደጋግሞ ማሰብና ማጤን ያስፈልጋል፤ ረባሾች ዝም ካሉ ለኢትዮጵያ እንደዘመቱ እንቆጥረዋለን፤ እውቀት የለሽ ለሀገር እና ለወገን ተቆርቋሪነት ወገንን መከራ ውስጥ ከመክተት ውጪ ትርፍ የለውምና፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top