Connect with us

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ 11ኛው እና አዲሱ የኢትዮጵያ ክልል!

Social media

ነፃ ሃሳብ

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ 11ኛው እና አዲሱ የኢትዮጵያ ክልል!

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ 11ኛው እና አዲሱ የኢትዮጵያ ክልል!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ዓመታት የነበረው ህዝባዊ አፈና ማሳያው በክልሎች የተፈጸመው ደባ እና የመብት ጥያቄ ረገጣ ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሶች ስል ነው የምኖረው የሚል መንግስት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአስተዳደር፣ በማንነትና መሰል የመብት ጥያቄዎች እስር ቤት ታጉረው አሳልፈዋል፡፡
ያ ወቅት ዛሬ ለነጻነት ለበቃው ቀጠና የጨለማ ብቻ ሳይሆን የመከራ ነበር፡፡

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከደቡብ ክልል የተሰጠውንና ከሀዋሳ የተቀበለውን አዲስ መኪና በየዞኑ ሲያደርስ ከመንገዱ ርቀትና ከመሰረተ ልማት ውድቀት የተነሳ እንደ ደረሰ ገራዥ የሚገባበት ልዩ የኢትዮጵያ ስፍራ ነው፡፡
ካፋ ቤንች ማጂና ሸካ ብዙ ሀብት እያላቸው ህይወትን በመከራ ያሳለፉ ወደ ዋና ክልላቸው ለመምጣት ሁለት ክልል አቋርጠው የሦስት ቀን መንገድ ተጉዘው የሚደርሱ ነበሩ፡፡ እንደ ኮንታና ዳውሮ ያሉ አካባቢዎችም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ያለ ሀብት እንዳላቸው ማወቅ የቻለው በዘመነ ብልጽግና ነው፡፡
ለውጡን ተከትሎ የዘመናት ጥያቄያቸው በትግላቸው እውን የሆነላቸው ሲዳማዎች የሚገባቸውን ክልል ከሆኑ በኋላ በልማትም በእድገትም እያሳዩ ያለውን የለውጥ ጉዞ መረዳት እውቀት አይፈልግም፡፡
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዎች በዘዴ ተሰባሰቡና እጅ ለእጅ ተያያዙ ያንን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት ራሳቸውን ችለው በክልልነት የተደራጁ እንዲሆኑ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀበለው፡፡ ከዚያም የህዝበ ውሳኔው ቀን ተቆረጠ፡፡ እውነት ለመናገር ጉዳይ የህዝብ ድምጽ የማይፈልግ የህዝብ ጥያቄ ነበር ያም ሆኖ ህግና ስርዓትን መከተል ስላለበት ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን አካሄደ፡፡
መስከረም ሃያ ቀን 2014 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልል ውስጥ የነበሩት አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ራስ አስተዳደር የክልልነት ጥያቄ በማቅረብ ያካሄዱት ህዝበ ውሳኔ በክልልነት መዋቀር እንፈልጋለን የሚለው በአብላጫ ድምፅ መወሰኑን በማስመልከት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በመዋቀሩ ከዚህ በፊት የነበረው አብሮ የመኖር እሴት ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ነባሩ ክልል አሁን በአዲስ መልክ ለሚዋቀረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልን ለማጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል፡፡ በተመሳሳይም የደቡብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤው አቶ ለማ ገዙሜም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ “በክልልነት እንዋቀራለን” የሚለው አብላጫ ድጋፍ በመገኘቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስላልፈዋል፡፡

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዲሱ የኢትዮጵያ ክልል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top