Connect with us

“ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንም ጥላ፤”

Social media

ነፃ ሃሳብ

“ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንም ጥላ፤”

“ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንም ጥላ፤”
የትህነግ ዲያቆን ዳንኤልን የማጣጣል ሴራ!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
ያው እንደምታውቁት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል አራት ኪሎ ለመግባት በርሃ ወርዶ አስራ ሰባት ዓመት ወንድሙን በመግደል ሀገርን በማድማት አላሳለፈም፡፡

ሀገር የማገልገል ጥሪ የምትወዱት ቦታ አስቀመጠውና አይናችሁ ቀላ፡፡
አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደ ህዝቡ ሁሉ ያሳደዳችሁት ገፋችሁትና ያደማችሁት ነው፡፡ ለእናንተ እንኳን ድፍን ኢትዮጵያ አደይ የምትሏት ትግራይና የትግራይ እናትም ከአንድ መለኪያ መጠጥ አትበልጥም፡፡

በተቃራኒው እዚህ ላለ ወገን ዳንኤል ክብረት ብዙ ትርጉም ያለው የሀገር ልጅ ነው፡፡

ዳንኤልን መቀየም ካለበትማ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቀየመው፤ ሴይጣን አድርጎት የማያውቀውን ድርጊት ለምትፈጽሙት ለእናንተ የሴጣን ስም ሰጥቷችኋልና፡፡ ሳጥናኤል የሚቀናበትን ግብር ይዛችሁ እሱ በሳጥናኤል እናንተን መመሰሉ እኛን ያስከፋ እንጂ ደግሞ እናንተ የሰራችሁትን በተናገረ ምን ቅር አሰኛችሁ?

እናት እያለቀሰች መስሎኝ ልጇን ለጦርነት የማገዳችሁት፤ ትናንት ወገናችን ያላችሁት በርሃብ እየረገፈ የተረዳውን ስንዴ ሸጣችሁ ጥይት የገዛችሁ እኮ ናችሁ፡፡ ባንክ መዝረፍን ተራራ ያንቀጠቀጥን እያላችሁ ለልጅ ልጅ ያስተማራችሁ፡፡

ሀገር መጥላት ጌጣችሁ መሆኑን በአደባባይ ሲዖል ወርደን ሀገር እናፈርሳለን ያላችሁት በድብቅ አይደል? በየሚዲያችሁ የምትደክሙበትን ነው ዳንኤል መልሶ የነገረን፡፡ ምን አዲስ ነገር ኖሮ ነው ዛሬም ለተጎዳው ከማዋጣት ለሚዲያ ጉቦ ከፍሎ ዳንኤልን ለማጣጣል ይሄ ሁሉ ርቀት መሄዳችሁ?!
ዳንኤል አሁን የተከበሩ ነው፡፡

በጥይት የረገጣችሁት አዲስ አበባ በካርድ መርጦ ፓርላማ አስገብቶታል፡፡ ታስታውሱ እንደሁ ኮሮጆ ገልብጦ የመመረጥ ምዕራፍ ሳላችሁ እንኳን ፓርላማ የመግባትን ክብር ስትነግሩን ነበር፤ ሰውዬው ተመርጦ ፓርላማ ገብቷል፡፡ የህዝብ እንደራሴው ለህዝብ የሚያስብ ህዝብ የሚፈልገው እንጂ መልእክተኛ ልካችሁ እንዳሰራችሁት ዘገባ ጥላቻ ቀስቃሽ አይደለም፡፡

ዳንኤልማ አይጠላችሁም ቢጠላችሁ ኖሮ በእናንተ ዓይን ደግ ከሚባለው ሳጥናኤል ባላመሳሰላችሁ ነበር፡፡ በሳጥናኤል የተደፈረች እናት አናውቅም፤

ያደረጋችሁትን ሁሉ ፎክራችሁ ፈጽማችሁ በሚዲያ ሰበር ዜናና ድል ብላችሁ በተግባር አውጃችሁ፤ ያን ማድረግ ነውር መሆኑን ከገለጸ ጋር እንካ ሰላንቲያ የሚገርም ነው፡፡

መርሃችሁ ኢትዮጵያን መጥላት ነው፤ በዓለም አደባባይ አዋርዳችሁ አንገቷን አስደፍታችሁ መቀመቅ ልትከቷት ያሰባችሁት ሀገር ጠባያችሁ ወደ ሆነው የሽፍትነት ህይወት ተባብራ ከትታችኋለች፡፡ ነገ ደግሞ ትጠፋላችሁ፡፡ ኢትዮጵያዊን መጥላት መርሃችሁ ስለሆነ በአሉባልታችሁ የምትከፍሉት ልብ የለም፡፡

እንዲህ አይነት ዜናዎች እንዲሰሩና የሀገርና የሀገር ወዳድ ሰዎች ስም እንዲጠፋ እንዲሁም እንዲዋከቡ ለማድረግ የምትሄዱበትን ርቀት ለተራበውና ወገናችን ላላችሁት አውሉት፡፡ በስሙ ነግዳችሁ ዘርፋችሁ ከመሮጥ ያተረፈው ነገር ስለሌለ በዚህ እንደ እሱ መከራ ውስጥ በገባችሁበት ሰዓት እንኳን ዶላሮችን የእርዳታ እህል ሸምቱባቸው እንጂ ሀሰተኛ ዘገባ መልቀቂያ መሳሪያ አታድርጓቸው፡፡

አሁን በመላው ኢትዮጵያ የትህነግ ጸሐይ ጠልቃለች፡፡ ከዚህ በኋላ አሉባልታም ብርቅ የሚሆንበት ውሸት ማውራት የሚናፈቅበት ወራት እየቀረበ ነው፡፡ ነውራችሁን ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል አወራው ብላችሁ አትገረሙ ገና ዓለም ይሰማዋል፡፡ ገና ዓለም ያየዋል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top