Connect with us

ወርቁ አይተነውም መስጠቱን አያቆም፤ እኔም ማመስገኔን አልተው፤ ደግነቱን ይዞ ወሎ ገብቶ ወጣ፡፡

አሚኮ

ነፃ ሃሳብ

ወርቁ አይተነውም መስጠቱን አያቆም፤ እኔም ማመስገኔን አልተው፤ ደግነቱን ይዞ ወሎ ገብቶ ወጣ፡፡

ወርቁ አይተነውም መስጠቱን አያቆም፤ እኔም ማመስገኔን አልተው፤ ደግነቱን ይዞ ወሎ ገብቶ ወጣ፡፡
ወርቁ በግርግር ላትርፍ ሳይሆን በግርግር ልክሰር ያለ ወገን ነው!

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
ባጠጋን ደጋግሞ ማመስገን ያሳማል እንዲል ብሂሉ አልታማ ብዬ እተዋለሁ ብለው ደግነቱን አይተው ይኼው በየቀኑ ያስጽፈኛል፡፡ መቼም ወርቁ አይተነው ፊቱን የዞረበት ጉዳያችን የቱ ነው ቢባል ተፈልጎ ማግኘት አበሳ ነው፡፡

የህልውና ዘመቻውን በስውር ሳይሆን በአደባባይ በጥሪቱም በወኔም ግፋ ያለ ባለሃብት ነው፡፡ ሀብቱ ሳያሳሳው ነገር ዓለሙን ጥሎ ሀገር ይቅደም ሲል ሰንብቷል፡፡ በእውነት የአማራ ባለሃብቶች በዚህ የከፋ ጊዜ ከሀገርና ከወገን ጎን በመቆማችሁ ልጆቻችሁ የሚኮሩበትን ስራ ሰርታችኋል፡፡
ወርቁ አይተነው እንዲሁ እዚህም እዚያም ሲሮጥ ከርሟል፡፡

ከወዳጆቹ ጋር ሆኖ አፋር ድረስ በመዝለቅ አለን ብሏል፡፡ ከማሰልጠኛ እስከ ግንባር በርቱ ሲል ሰንብቷል፡፡ አሁን ደግሞ አባ መስጠት ወሎ ድረስ መስጠትን ክህሎቱ ያደረገው ሰውዬ አለሁ ብሎ ገብቷል፡፡

እንዲህ ባለ ችግር ወቅት የሚገጥመንን እናውቀዋለን፤ ዋጋ ጨምሮ ማሳፈር የፈለገ አሽከርካሪ አይተናል፡፡ ዕቃ አንሮ መክበር የሚፈልግ ሆዳም አውግዘናል፡፡ ቤት ኪራይ ጨምሮ ይለፍልኝ ያለ ወገን መሳይ ሴጣን ታዝበናል፡፡ ግን ደግሞ የዚህ ሁሉ ስርየት የወርቁ አይነት ደጋግ ሰው ሰፊ ልብና ደግነት ነው፡፡

ወርቁ በግርግር ላትርፍ ባይ እንዳልሆነ ደጋግሞ አስመስክሯል፡፡ በዚህ የጭንቅ ወቅት የዘይትን ዋጋ ቀንሼ ገበያ አቀርባለሁ የሚለውን ዜና ሲነግረን በአንድ እጁ ለወሎ ወግኖ ቼክ እየፈረመ ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ሰው ዝም ብሎ ማለፍ አቃተኝ፤ ብዙ ጊዜ እናመሰግናለን ብያለሁ፤ ደግሞ ምስጋና እንዳይበዛ ብዙ ጊዜ ዝምታን መርጫለሁ፡፡ ወርቁ አይተነው ግን ዝም አያስብልም፤ ደግነቱን ይዞ ወሎ ገብቷልና፤

አቶ ወርቁ ለደሴ ተፈናቃዮች ከለገሰው 25 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ ከነማው እንዳይጨልምበት አለሁ ብሎ በቀጣይም ከጎናችሁ እቆማለሁ በሚል ተመልሷል፡፡
መጠለያ ድረስ ሄዶ የወለደች አራስ ጠይቆ በሽልም ያውጣሽ ማለት መቼም ተጎጂን ሆኖ ሲያደምጡት፣ ተጎጂን ሆኖ ሲቀበሉት ትርጉሙ ተአምር ነው፡፡ ሰውዬው ያደረገውም ይሄንን ነው፡፡

እውነት ለመናገር ለሀገሬ የንግድና የኢንቨስትመንት ሰዎች ይሄ ወራት ከባድ ነው፡፡ ክረምት ነው፡፡ መከራው በዝቷል፡፡ ነግዶ ማትረፍን አልምቶ መሰብሰብን የማሰቢያ አይደለም፡፡ የዚያኑ ያህል እጁን የሚዘረጋው ወገን ብዙ ነው፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል ሳይጎድሉም ሰለቸኝ ሳይሉም አለሁ ብሎ መቀጠልና ከወገን ጎን መቆም ያኮራል፡፡ የሚያኮራ ተግባር ምስጋና ምኑም ነው፡፡

አንድ ቀን ሀገር ሰላም ሆኖ እንዲህ ያሉ ባለሃብቶች በጥሪታቸው ያቀኗት ሀገር በልጽጋ የውለታ ፍሬያቸውን የሚሰበስቡበት ቀን ይመጣል፡፡ ያኔ ስማቸው ኩራት ነው፡፡ የዛሬ ተግባራቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰው ስላላት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጀግናችን ሃይሌ በርሮ ወሎ ሲገባ እዚያ ወገን መሃል አዲስ ተስፋን ዘርቶ ነበር፤ ወርቁም ተከተል፡፡ ወገን ከየአለበትም መግባቱን ቀጥሏል፡፡ አብረን ከቆምን የቱም ክንድ አይጥለንም፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top